• በቅርብ የተጻፉ

    Tuesday 10 November 2015

    መልክዐ ተክለ ሃይማኖት ሰላም ለፅንሰትከ


       ክፍል ሁለት   መልክዐ ተክለ ሃይማኖት  ሰላም ለፅንሰትከ

    "ሰላም ለፅንሰትከ ወለልደትከ እምከርሥ።
    አመ ዕሥራ ውረቡዑ ለወርኃ ታኅሣሥ።
    ተክለሃይማኖት በኩሉ ወበውስተ ኰሉውዱስ ።
    ናሁ ወጠንኩ ወዕቤ ለስብሓቲከ ሐዲስ ።
    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።"

    ትርጉም
     ''ተክለሃይማኖት ሆይ አስቀድሞ በማህጸን ለተጸነስከው ጽንሰትህና በታህሳስ ሃያ ዐራት
     ቀን ለተወለድከው መወለድህም ሰላም እላለሁ በሁሉ ዘንድ የተመሰገንክ ተክለሃይማኖት ሆይ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ 
    ብዬ አዲስ የሚሆን ምስጋናህን እጀምራለሁ''

    በክፍል አንድ ጽሑፋችን '' ሰላም ለፅንሰትከ ወለልደትከ እምከርሥ። 

           አመ ዕሥራ ውረቡዑ ለወርኃ ታኅሣሥ።''የሚለውንየአባታችንን ፅንሰታቸውን እና ልደታቸውን የሚያወድሰውን ክፍልተመልክተን ነበር በዚህ ጽሁፋችን ደግሞ'' ተክለሃይማኖት በኩሉወበውስተ ኰሉውዱስ ። ናሁ ወጠንኩ ወዕቤ ለስብሓቲከ ሐዲስ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።"ትርጉም ፤ '' በሁሉ ዘንድየተመሰገንክ ተክለሃይማኖት ሆይ  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ ብዬ አዲስ  የሚሆን ምስጋናህን እጀምራለሁ''

                   በቅድስት ቤተክርስትያን ስርአት መሰረት የማንኛውምተግባር መጀመርያ ስመ ስላሴን መጥራት ነው የምታድርጉትን ሁሉበጌታ ስም አድርጉት ስለተባለ የጸሎትም መጀመርያ በስላሴ ስምማማተብ ነው ምእምናን ጸጋ የሚያግኙበት የእግዚአብሔር ልጆችየሚሆኑበት ምስጢረ ጥምቀተት እንኳን የሚፈጸመው በአብበወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው ማቴ ፳፰፤፲፱ ለዚህም ነውየአባታችን ምልክዐ ጸሎታቸው ሲጀመር በስመ አብ ወወልድወመንፈስ ቅዱስ የተባለው ። ይህም እያንዳንዱ ክርስትያን የግልምሆነ የማህበር ጸሎት ሲያደርግ በስላሴ ስም ማማተብ እንዲገባያስተምረናል ጌታም በወንጌል እንዲህ ብሎ ነግሮናል

    «ወደ አብ እሄዳለውና አብም ስለወልድ እንዲከበር በስሜየምትለምኑትን ሁሉ እኔ አደርገዋለሁ» ዮሐ ፲፬፡፲፫በተጨማሪም«በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ እኔም ስለናንተአብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም»ዮሐ፲፮፡፪፮

                      በስሜ የምትለምኑትን ማለት በስመ ተወላዲአምናችሁ ወልድን ተወላዲ ብላችሁ በስመ ወላዲ አምናችሁ አብንወላዲ ብላችሁ በስመ ሰራጺ አምናችሁ መንፈስ ቅዱስን ሰራጺብላችሁ የምትለምኑትን እኔ አደርገዋለው በማለት በስልጣን ከአባቱከአብ ከሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል መሆኑንም ጭምርአስግንዝቦአል ። እንግዲህ የቅዱስ አባታችን መልክዐ ጸሎታቸውበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ተብሎ መጀመሩ መጽሐፍቅዱስን ምሰረት ያደረገ መሆኑን እዚህ ላይ ልብ ይሏል። በሁሉዘንድ    የተመሰገንክ ቅዱሳን በሁሉ ዘንድ የከበሩ የተመሰገኑእንደሆኑ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ያስተምረናል በሁሉ ዘንድማለት በሰዎች በመላዕከትእና በእግዚአብሔር ዘንድ ማለት ነው ።እግዚአብሔር አምላካችን ለቅዱሳኑ ከሚሰጣቸው ጸጋ አንዱ በሁሉዘንድ መወደድ ፤ መፈራት፤ ግርማ ሞገስ እና በጸጋ መመስገን ነውይህንንም ለመረዳት የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችንመመልከት ይቻላል

                      '' የሚባርኩህንም እባርካለው'' ዘፍ12፡3 ርዕሰአበው ለሆነው ለአባታችን ለአብርሃም በተነገረው በዚህ ኃይለ ቃልእንደምንመለከተው ቅዱሳንን የሚባርክ የሚያመሰግን እርሱ እንደሚባረክ በረከተ ስጋ ወነፍስ እነደሚያገኝ ቅዱስ ቃሉ በግልጽያስቀምጣል ። ስለዚህም ከቅዱሳን አንዱ የሆኑትን አባታችንን ቅዱስተክለሃይማኖትን ማመስገን በረከተ ስጋ ወነፍስ የሚያሰጥ መጽሐፍቅዱሳዊ መሰረት ያለው እንጂ  የስጋና የደም ትምህርት አይደለም።ዛሬ ማንም ተነስቶ የአባታችንን ቃል ኪዳን አማላጅነትለማስተባበል ቢሞክር ፤የሚገባቸውንም የጸጋ ምስጋና ከማቅረብቸል ቢል ወይም የትዕቢት የጽርፈት ቃል ቢናገር ከሁሉ አስቀድሞየሚጎዳው ራሱን ነው ምክንያቱም በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ተብሎስለተጻፈ ''የሚረግሙህንም እረግማለው'' ዘፍ12፤3

                በተጨማሪም''ጻድቃንን የሚጠሉ ይጸጸታሉ''መዝ33፤21 እንዲሁም ጌታ ራሱ በወንጌል'' እናንተንም የጣለ እኔንይጥላል'' ሉቃ10፤16እንግዲህ በቅዱሳን ላይ የማይገባ የድፍረትንግግር መናገር የእርግማን ፤የውድቀት እና የዘላለማዊ ጸጸት ውጤትከሆነ አንዳንዶች ስለምን ወደዚህ ድፍረት ገቡ? በእርግጥ ሐዋርያውቅዱስ ጴጥሮስ በመልዕክቱ ''ደፋሮችና ኩሩዎች ሆነው ስልጣንያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም''2ጴጥ2፤11ብሎ እንደገለጸውካደረባቸው መንፈሰ ጽርፈት ተነስተው የስድብ መሳርያ ቢሆኑየሚደንቅ ነገር አይደለም። ለቅዱሳኑ ክብር የሚቆረቆርእግዚአብሔር ግን ዝም አይልም በቅዱሳኑ ላይ ስለምትሰነዘርእያንዳንዷ ቃል ይፈርዳል ለዚህም ማሳያ የሚሆነን በኦሪት ዘኁልቁምዕራፍ ፲፪ የተዘገበው ታሪክ ነው ። የሙሴ ወንድም ካህኑ አሮንእና እህቱ ማርያም በታላቁ ነቢይ ሙሴ ላይ እንዲህ በማለትየድፍረት ቃል ተናግሩ «በእውኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻተናግሮልን ? በኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን አሉ» ዝኁ፲፪፡፪ይህንንም የሰማ እግዚአብሔር በጣም ተቆጣ ሶስቱንም ወደቤተመቅደሱ እንዲመጡ ከጠራቸው በኋላ በሚያስፈራ ግርማበአምደ ደመና ወረደ ካህኑ አሮንንና እህቱ እንዲህ በማለትተቆጣቸው «ቃሌን ስሙ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር እኔእግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ ወይም በህልምአናግረዋለሁ ባርያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም እርሱ በቤቴ ሁሉየታመነ ነው እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለውበምሳሌ አይደለምየእግዚአብሔርንም መልክ ያያል በባርያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድስለምን አልፈራችሁም አለ» ዘኁ ፲፪፡፮ ፰ ወዲያውኑ ማርያም እህተሙሴ በለምጽ ነደደች አሮንም ካህን ስለንበር ከህዝባዊያኑ ጋርቅጣቱ ስላልተገለጸ እንጂ ተቀጥቶአል እግዚአብሔር አምላክምመልሳቸውን እንኳን ሳይጠብቅ ትቶአቸው ሄደ ። አዎን ዛሬምበቅዱሳኑ ላይ ማንኛውንም አይነት የድፍረት ንግግር የሚናገሩተጸጽተው ንስሃ ካልገቡ ቅጣቱ የማይቀር ነው። ለጊዜው በሕይወተስጋ ሳሉ በክህደት ለምጽ ሲነዱ ይኖራሉ በኋላም ዘላለማዊ እሳትእንደ ለምጽ ሲበላቸው ይኖራል። እንግዲህ ምን እንላለን ለቅዱሳኑየሚገባውን ክብር ከመስጠት ወደኋላ ብለን እግዚአብሔርንእናስቆጣውን ? አይደለም ተገቢውን ክብር ለወዳጆቹ እናቅርብእንጂ። ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስንዋቢ አድርጋ አባታችን ቅዱስ ተክለሃማኖትን በሁሉ ዘንድየተመሰገንክ እያለች ታወድሳቸዋለች ። አዎን በእውነት አባታችንቅዱስ ተክለሃይማኖት በሁሉ ዘንድ የተመሰገኑ ናቸው ለዚህም ገድልትሩፋት የፈጸሙባት ምድረ ኢትዮጵያ ቋሚ ምስክር ናት ።የአባታችን የቅዱስ ተክለሃይማኖት ሥራ በኢትዮጵያ ብቻ ያበራአይደለም ታሪካቸውን መርምረው የተደመሙበት አውሮፓዊያንሳይቀሩ በቤተ መዛግብቶቻቸው ከትበው አስቀምጠውታል ።

                 በቃልኪዳናቸው የታመኑ ግብጻዊያን ክርስትያኖች እንኳንበስማችው ቤተክርስትያን አሳንጸው በረከታቸውንይሳተፋሉ።በምድረ አሜሪካም ታላቅ የጸሎት ሰው ተብለውሰዕላቸው በቤተመዛግብቶቻቸው ሳይቀር ተቀምጦል።ታዲያ እኚንየመሰሉ የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ መገለጫ የሆኑ አባት በሁሉዘንድ የተመሰግኑ ቢባሉ በትክክል ቢገልጻቸው እንጂ ምንየሚያስተች ነገር አለው  

    ፡;
                              አምላከ ቅዱሳን  ጸጋውን ያብዛልን 
                                    ወስብሐት ለእግዚአብሔር   
                                      ወለመስቀሉ ክቡር
                                      ወለወላዲቱ ድንግል

    ከዚህ በፊት ያለውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ /

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: መልክዐ ተክለ ሃይማኖት ሰላም ለፅንሰትከ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top