በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርንመንግሥት ሊያይ አይችልም” ዮሐ. 3፡3
እንኳን ለጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ፤ በባሕርዩ ቸርና ሁሉን ቻይ የሆነ አምላቻችን አሁንም የንስሃ ጊዜን ጨምሮልን ለሚቀጥለው ዓመት በሰላም አድርሶን ይህንን በአል ለማክበርና ድንቅ ሥራውን ለመመስከር ያብቃን።
በዛሬው ትምህርታችን ስለ ገሀድ እንማራለን።
ገሐድ ፡ ከ7ቱ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። ገሐድ ማለት ሰዋስዋዊ ትርጉሙ ግልጽ የሆነ የሚታይ የሚታወቅ ያልተሰወረ፤ የማያጠራጥር ወዘተ ማለት ሲሆን ለምሳሌ “በገሐድ ንገረን! በገሐድ ንገሪኝ” ወይም በገሐድ የተነገረ ነገር” ወዘተ ማለት በግልጽ ሁሉም በሚሰማው መንገድ ማለት ነው።
ነገር ግን ሰዋስዋዊ ትርጉሙ ከይዘቱ ወይም ዛሬ ከምንማረው ማለትም በሰባቱ አጽዋማት ውስጥ የገሐድ ጾም ካለው የሥራ ድርሻ ትርጉም ጋር በቀጥታ አይመሳሰልም። ስለዚህ ገሐድ ማለት በዚህ ትምህርታችን ወይም ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ በመሆኑ በምንሰጠው ትርጉም መሠረት ተለዋጭ ማለት ነው።
የማን ወይም የምን ተለዋጭ ለሚለው ጥያቄ የረቡእና የአርብ ተለዋጭ የሚል ይሆናል። ማለትም የጥምቀት በአል ረቡእ ከሆነ የጥምቀት ዕለት መጾም ስለማይገባ በረቡዕ ፈንታ ማክሰኞን ሙሉ ቀን እንጾማለን፤ አርብ ከሆነም እንደዚሁ በአርብ ፈንታ ሐሙስን ሙሉ ቀን እንጾማለን ፤ ረቡእና አርብ ግን የፍስክ ቀናት ሆነው ይውላሉ ማለት ነው። ለዚህም ነው “ተለዋጭ ወይም ምትክ” በማለት ትንታኔ የምንሰጠው።
የጥምቀት በአል እሁድ ወይም ሰኞ ከዋለ ግንዕሁድና ሰኞ የጾም ቀናት ስላልሆኑ በነዚህ ቀናት ምትክ ቅዳሜና እሁድን መጾም የለብንም ምክንያቱም 1ኛ ቅዳሜና ሰኞ የጾም ቀን አይደሉም፤ በዚህም ምክንያት ተለዋጭ አያስፈልጋቸውም፤ 2ኛው ደግሞ በሰንበት ቀናት መጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን የተከለከለ ስለሆነ በእሁድና በሰኞ ፈንታ ቅዳሜና እሁድ ገሐድ ተብለው አይጾሙም።
የገሐድ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ስለሆነና በየአመቱ መቋረጥ ስለሌለበት ግን ቅዳሜን እና ዕሁድን ደግሞ መጾም ስለማይገባ በነዚህ ቀናት ጾመ ገሐድ ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ መሆኑን ለማሰብከሥጋና ከወተት ዘሮች ብቻ እንከለከላለን። ጾማችን ግን አንውልም። ከሦስት ቀናት በኋላ የምናከብረው የዘንድሮው የጥምቀት በአል ሰኞ ስለዋለ እሁድን አንጾምም፤ ከወተትና ከእኅል ዘሮች ግን እንከለከላለን።
0 comments:
Post a Comment