• በቅርብ የተጻፉ

    Saturday, 21 November 2015

    ጩጊ ማርያም- ከጸበሉ ጠጥተው ስጋቸው ያልፈረሰ ፍየሎች


    ❖❖❖ በስመ ሥላሴ ❖❖❖

    እነሆ ጌታ ፈቅዶ የሰማሁትን ያየሁትን እነግራቹ ዘንድ ጀመርኩ የዘንድሮዉን የሰኔ ጎሎጎታ ክብረ በዓል አከብር ዘንድ ወደ ቅዱሱ እና በጌታ ፍቅር በተጠመደዉ እና ከልጅነቱ ጀምሮ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ፀንቶ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን አፍርቶ በፀጋ ከፍ ወዳለዉ የነ አቡነ አምደሥላሴ ወዳጅ ወደነበሩት ወደ አቡነ ምዕመነድንግል ገዳም ነበር የተጓዝኩት ።

    የእነዚህ አባት ገዳም ልዩ መታወቂያ ስሙ ጩጊ ማርያም በመሰኘት ይታወቃል ። ከጎንደር 25 km ርቀት ያላት ሲሆን ኮሶዬ ከተባለች አካባቢ ሲደርሱ ለበረታ የ2 ሰዓት ለደከመ ከ 2ሰዓት በላይ የሚያሰኬደዉን መንገድ ይጀምራሉ ። አቡነ ምዕመነድንግል እንደ ቀደምት አበዉ ጠንካራ እና ለሃይማኖተ ክርስቶስ ቀናተኛ የነበሩና በዋልድባ ገዳም በአበምኔትነት ያገለገሉ ኀላም ውዳሴ ከንቱን በመሸሽ ከገዳሙ ርቀዉ አሁን ወዳሉበት ብዙ ፅድ እና ወይራ ወዳለባት /ጩጊ / መጥተዋል በዚህ ስፍራ ለረዥም ግዜ ተጋድሎ አርገዉበታል ።

    በዚህ ስፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያምና ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ተገልጦ ለአባታችን ቃል ኪዳን ሰጥቶአቸዋል፣ አንዲሁም እንደ ትንሽ ብላቴና አቅፎአቸዉ ስሞአቸዋል ፣እንዲሁም በጌታ አዳኝነት አምነዉ በቅዱሱ አቡነ ምዕመነድንግል ፀሎት ሚታመኑ ሁሉ ፈዉስ ይሆናቸዉ ዘንድ ሁለት ማየ ዮርዳኖስ አፍልቆላቸዋል ከዚ ማየ ዮርዳኖስ የጠጡ ሁሉ ከደዌ ከመፈወሳቸዉ በተጨማሪ በድን ስጋቸዉ አይፈርስም አይበሰብስም ለዚ እንደማሳያ የሚሆኑ 16 ፍየሎች ከዚ ማየ ዮርዳኖስ ጠጥተዉ አሁንም ድረስ ሰዉነታቸዉ ሳይፈርስ አሁንም በሕይወት ያሉ ይመስላሉ ። አባታችን አቡነ ምዕመነድንግል አካሄዳቸዉን በጌታ ቃል እና ትምህርት ስላፀኑ ሞትን ሳያዩ እንደነ ሄኖክ ፣ ኤልያስ ፣ አቡነ አረጋዊ ፣ቅ.ያሬድ ተሰዉረዋል ። 

    አምላከ አቡነ ምዕመነድንግል እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ይማረን ፣ ይባርከን ። አሜን !!

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ጩጊ ማርያም- ከጸበሉ ጠጥተው ስጋቸው ያልፈረሰ ፍየሎች Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top