መልክዐ አርሴማ ቅድስት (አማርኛ)
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንድ አምላክ ብልን እናምናለን፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
ይህንን መጽሃፍ ያነበበ የተረጎመ የሰማ የቅድስት አርሴማ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል፡፡
1-ሰላም ለጽንሰትኪ
በጳጳሳት አለቃ ጸሎት ለመጸነስሽ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድም ከእናትሽ ማህጸን ለመወለድሽ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ለዚህ ንግግር መግቻ የሚሆን የምስጋና መብራትን በአንቺ እሾምበት ዘንድ አንደበቴን አስማሚልኝ በጭንቄ ጊዜ ባለቤቱ አንቺ ነሽና፡፡
2-ሰላም ለዝክረ ስምኪ
በቃል ኪዳን መጎናጸፊያ ለተጠቀለለ ስምሽ መታሰቢያ ስላምታ ይገባዋል፡፡ የጥራቱ ህብር ለሚያበራ ጠጉርሽን ሰላምታ ይገባል፡፡ ትዕግሥትን የተሸለምሽ ገድልንም ለተጎናጸፍሽ ቅድስት አርሴማ ሆይ ረቂቅ የሚሆን የኃይልሽ ትርጓሜ መሸከሚያ በአንደበቴና በኔ ቃል ይጻፍ፡፡
3- ሰላም ለርዕሲኪ
ሃይማኖት ሽቱን ለተቀባ ራስሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የማሰተዋል ብርሀንን ተመልቶ ለነበረ መልክሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ ቅድስት አርሴማ ሆይ ጌታሽ የዕጽ መስቀል ላይ የወደቀ በግን እስከሚያገኝ ድረስ የተረሳ አዳምን በፈለገ ግዜ ከሰማይ ከብልጽግ ወደ ችግር ምድር ወረደ፡፡
4-ሰላም ለቀራንብትኪ
የመልክና የደም ግባት መውደድ ላላቸው ቅንድቦችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እንደ ብርሃን ክዋክብት ለሚያስደስቱ ዓይኖችሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ ቅድስት አርሴማ ሆይ ከሐዲስ ቃል ኪዳን ምንጭና ከለመለመ ፈለግ ጋራ ወደ ታመመችና ባህሪይዋ ውሃነት ወዳላት ሥራዬ የሕይወት መድሃኒት ውሃን ካንቺ ዘንድ ይፍሰስልኝ፡፡
5-ሰላም ለአእዛንኪ
የምሰራች ወርቆቹን ለተሸለሙ ጆሮችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡እንደ ሮማን ቅርፊት ቀዮች ለሚሆኑ ጉንጮችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ በደብረ ሲና አስርቱ ቃላት እንዳሉበት ታቦተ ጽዮን ቃል ኪዳን ያለሽ የዕውነት ኃይል ታቦት አርሴማ ሆይ ከይቅርታሽ ደመና የተነሳ የሚፈውስ የአማረ ህይወተ መናን ወደ ተራበ ሆዴ መግቢኝ፡፡
6-ሰላም ለአእናፊኪ
ንጹህ በሚሆን ወርቅ ተነብዩ አፍሽና ከንፈርሽ ጋር አንዱ እንደተመረጠ ሽቱ እቃ ለሚያስደስቱ አፍንጮችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ለተጨነቁና ውሃን ለተጠሙ የበረከት ጠበል አርሴማ ሆይ ከረድኤትሽ ሰማይ የነጠበ ዝናም ኃይልሽና ፍቅርሽ ውሃ በኔ ላይ ይፍሰስ፡፡
7-ሰላም ለአስናንኪ
እንደ እንቁ ለተደረደሩ ጥርሶችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡የጌታችንን መስቀል ነገር ለሚናገር ልሳንሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ የሰማእታት ምሰሶ የደካሞች ኃይል የምትሆኝ ቅድስት አርሴማ ሆይ የነበልባልና የእሳት ዲን ስቃይ በአንቺ ጠፋ የታመነ ታሪክሽ እንዲህ ይላልና፡፡
8-ሰላም ለቃልኪ
የተበተነ ልቡናን ለሚሰበስብ ቃልሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ደዌ ኃጢያትን ለሚያድን ሕይወት ትንፋሽሽም ሰላምታ ይገባል፡፡የምስኪኞች ተስፋ የደካሞች አረጋጊ አርሴማ ሆይ የሚያቃጥል እሳትና ከባድ በሚሆን ጨለማ ዘመን ጊዜ በሚጠቅም ቃልኪዳንሽ አድኝኝ፡፡
9-ሰላም ለጉርኤኪ
ምስጋና ወተትን ለጠባ ጉሮሮሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እንደ ስይፍ ስለት የወርቅ ገንቦን ለተሸለመ አንገትሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ልዩ በሚሆን በስላሴ ባህርይና የተዘጋጀ አንድነት ብርሃንን በመቀበል ከሰማዕታት ጋር ያለመ ወንጀል ቅድስት አርሴማ ሆይ ከተቀደሰ ቦታሽ እንዴት አየሽ፡፡
10-ሰላም ለመታከፍትኪ
የስቃይ ቀንበር ለተሸከመ ትከሻሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የስዕልሽ መንበር ለመገረፍ ንግስ ለሆነ ጀርባሽ ሰላምታ ይገባል፡፡በረሃውን ከእረፍት ጋር የሚያለመልም ዝናመ ምህረትን አርሴማ አሳስቢልን፡፡
11-ሰላም ለእንግድአኪ
የዓለም ወርቅን ለጠላ ደረትሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የመቅስፍትና የስቃይ መቀመጫ ለሚሆን ብብትሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ የመሰናክል ድንጋይ ድርጣድስ በተፈታተነሽ ጊዜ ስለሃይማኖትሽ ያዕቆባዊ መጽሃፍን ትገልጭለት ዘንድ ጣኦታትንም አጠፋሽ ባዕድ አምላክንም ሰበርሽ፡፡
12-ሰላም አአእዳውኪ
የህማማት ወርቅን ለተሸለሙ እጆችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የኃጢያት አለቶችንም ለአጠፋ ክንድሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ ስለፍቅርሽ ልቤ ተመስጧልና ስለነፍሴ ቁስል የጣፈጠ ሽቱን ትቀቢኝ ዘንድ ጥቂት አዘጋጂልኝ፡፡
13-ሰላም ለኳርናዕኪ
የትዕግስት ራስ ትራስ ለሚሆን ክንድሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ሀዲስ የሚሆን ተስፋ አካልን ለሚልክ ክንድሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ የይቅርታ አዳራሽ አርሴማ ሆይ ከወንጌላዊት መቅደስ በምሽት ጊዜ ከብስራታዊ መንበር ውስጥ እንደልመናዬ አገልጋይ ኃይልሽ ይሰዋልኝ፡፡
14-ሰላም ለእራኀኪ
ጸጋ ሀብትን ለሚስጥ መሃል እጅሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የጥበብ መብራቶችንም ለሚሆኑ ጣቶችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የቅዱሳን መመኪያ አርሴማ ሆይ እንደ ሰማዕታት አለቃ ጊዮርጊስ የሁሉ ጌጥ ራሶችና አራዊትን እረግጥ ዘንድ የአብ ሰልጣንን ለኔ ላኪልኝ፡፡
15-ሰላም ለአድፋረእዴኪ
ነጭነታቸው ለሚያስደንቁ ጥፍሮቸሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እንደ ትዕግስት ፏፏቴ ወተት ምንጭ ለሚሆኑ ጡቶችሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ ቅድስት አርሴማ ሆይ በረድኤትሽና በአንቺ ፍቅር ተደፋፋሪ ይውደቅ የጠላቴ ምክርም ከፊቴ ይበተን በሰማይና በምድር ተመጻድቆብኛልና፡፡
16-ሰላም ለገበዋትኪ
ስቃይን ለተጎናጸፈ ጎኖችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ትርጓሜ እህልን ለተመገበ ሆድሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ አፌ ስምሽን ባመሰገነ ጊዜ በመነሳት ጽኖም የተሰፋሽ ውሃን እስከማገኝ ድረስ በኔ ላይ ይቅርታ ዝናም ይፍሰስልኝ፡፡
17-ሰላም ለልብኪ
ጨለማና በቀልን ለተወ ልብሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እንደ አዲስ ወንጌል ምንቾች ንጹህ ለሚሆኑ ኩላሊቶችሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ ቅድስት አርሴማ ሆይ ሶስት ለሚሆኑ የስላሴ ስምን በመታመን በጠራሁሽ ጊዜ በኃይልና በረድኤት ቀን ዳጎን ጠፋ ጣኦቱም ፈረሰ፡፡
18- ሰላም ለህሊናኪ
የጌታ አገዛዝን ለሚያስብ ሕሊናሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ለትሩፋት ሰውነት ጋር አንድ ለሚሆኑ አንጀቶችሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ የጳውሎስ ሰይፍንና የጴጥሮስ አሳብን የተቀበልሽ አርሴማ ሆይ እየቀኑ ታረጋጊኝ ዘንድ የረድኤትሽ ባህሮች በላዬ ላይ ይስፋፉ፡፡
19-ሰላም ለንዋየ ለውስጥኪ
ከርኩሰት ንጹህ ለሚሆን ለውስትሽ ሰውነት ሰላምታ ይገባል፡፡ ሀዲስ የሚሆን ተስፋ ፍሬን ለአፈራ ጅማትሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ የትንቢትና የመጽሃፍ ምንጭ አርሴማ ሆይ በገነት ልቤ ዘወትር በለስ ያገኝ ዘንድ በጠብና በተንኮል ዘመን ጊዜ የፍቅር ውሃን አጠጪኝ፡፡
20- ሰላም ለኀንብርትኪ
ከሆድ መካከል ላይ ለሚኖር ማዕከላዊ መለያ ላለው ኀብርትሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የመድኃኒታችን ክርስቶስ ሙሽራ አርሴማ ሆይ ከተወደደ ጌታችን ጋር ሰማያዊ ከሚሆን ሰርግ ቤት ውስጥ በተቀመጥሽ ጊዜ በቃል ኪዳንሽ መክፈቻ ደጃፍን ለኔ ክፈችልኝ፡፡
21-ሰላም ለኃቌኪ
የኀማማት መታጠቂያን ለታጠቀ ወገብሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ቁመትን ለተጎራበቱ መንቶች ብብቶችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ መብራትን በአጣን በዚህ ዘመን መቋቋም ለኔ ብርሃን ጥበቃን ታበሪልኝ ዘንድ ከአለም አኩኋን ፈተና አንዲት ነፍሴን እለምንሻለሁኝ፡፡
22-ሰላም ለአብራክኪ
የእጅና የእግር መመላለሻ ከሚገለገልበት ስግደት ጸሎት አዳራሽ ለጉልበቶችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ክርስቲያናዊት አርሴማ ሆይ ጥርጥርና ክህደትን የተውሽ ብትሆኝ ከአደባባይ ስቃይን በአቆምሽ ጊዜ ከነጎድጓድና ከመብረቅ ማሰፈራት የተነሳ ምድር ተነዋወጠች፡፡ ቀስተ ደመናም እንደ ምሶሶ ተተከለ፡፡
23-ሰላም ለሰኮናኪ
በአሳላፊ ቤት ለሚያድጥ ተረከዝሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ከገስጋሽ ሰማዕት ቦታ ውስጥ ቀልጣፋ ለሚሆን ለእግርሽ ተረከዝም ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ ደግ ሰው ስምሽን በጠራ ጊዜ በአነሳሲታ ደምሽ የልቡና በድንን ዳሰሽ ዳግመኛም በህይወት ውሃ በደሉን አጥፊ፡፡
24-ሰላም ለአጻብእኪ
የእናሶስላ መነከርን ለለመዱ ነጮች ጥፍሮችሽ ለተሸለሙ ጣቶችሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ አንቺ አርሴማ ሆይ ከቆንጆ ቤት ምስክርነት ቦታ እንግዳ በሚሆን ረድኤትሽ ወዳጅሽን አድኝኝ የልብ በሽታ ህማም እንዳያስጨንቀኝ፡፡
25-ሰላም ለቆምኪ
የባለሟልነትና የማፈራት ምንጮችን ዘወትር የሚጠጣ የደጋ ዛፍ ለሚመስል ቁመትሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ በክፍ ዘመንም ከመውደቅ ደግፊኝ ከድካምም አድኝኝ፡፡ አርሴማ ሆይ የመጽሃፍሽ መቆለፊያን ዕከፍት ዘንድ ስምሽ የልመና ጸሎትን ሆነልኝ፡፡
26-ሰላም ለመልክዕኪ
ደመና ዝሙት የሸፈነው የወንጀለኛ ንጉስ ልብን በገደለ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ ቅዱስ በሚሆን መስቀል ምልክት አድኝኝ ወደ ምስጋናና ወደ ደስታ የፍቅርሽ ገመድ ልቤን ስቦታልና፡፡
27-ሰላም ለጸአተ ነፍስኪ
ወደ አዘነበለ አንገትሽ በሚያልፍ ሰይፍ ጊዜ ለነፍስሽ መውጣት ሰላምታ ይገባል፡፡ አርሴማ ሆይ መስዋዕትን በሚቀበል ጌታሽ ዘንድ የተረፈ ረድኤትሽ በኔ ላይ ይወርድ ዘንድ በከንፈርና በአፍ እለምንሻለሁኝ፡፡ የተቆጠሩ ሞትሽ ይህን ነገር አሳይቶኛል፡፡
28-ሰላም ለበድነ ሥጋኪ
ጨረቃን ለመሰለ ለሥጋሽ በድን ሰላምታ ይገባል፡፡ በምስጋና ወገንተኞች መላዕክት እጅ ለተቀደሰ መገነዝሽም ሰላምታ ይገባል፡፡
ቅድስት አርሴማ ሆይ ከጥልቅ ጥፋት ወደ ውስጥ ከግብጽ ከተማ ጠላቶችን በምስጋና ቃልኪዳንሽና ሙሴ ኃይልሥ ያሰጥማቸው ዘንድ ሰላምታ ይገባል፡፡
29-ሰላም ለመቃብርኪ
ከሰማዕታት ጋር ካረፍሽበት አርማንያ ቦታ ለመቃብርሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ በአርአያና በምሳሌ ከተናገርኩት ክብርሽ የተነሳ የሽንገላ እጅ ያልዳሰሰሽ የመነሳት ዕቃ አርሴማ ሆይ ከከንፈርና አፍ ምሳጋናን ይጥገብ፡፡
30-ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ
በፈጣሪ ቃል ለተመሰገነ ለስጋሽ መፍለስ ሰላምታ ይገባል፡፡ የዚህ አለም ኑሮን ላልፈለገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ብጽዕት አርሴማ ሆይ ችግርን እንዳላይ ከበረከተ ዕቃሽ መግቢያ ማረስን አልችልምና ጥቂት በረከትሽን ትሰጪኝ ዘንድ እለምንሻለሁኝ፡፡
31-ሰላም ለዘአእረፋ ምሰሌኪ
ከአንቺ ጋር ለአረፉ ለሀያ ሰባቱ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባል፡፡ ከብዙ ይቅርታ ጋር እና ቅድስት ከምትሆን ስምሽም ጋራ ሰማቸው ወደ አለበት ቦታ ረድኤታቸው በኔ ላይ ተወርድ ዘንድ አርሴማ ሆይ በሁሉ ዘመንና በሁሉ ዓመታት የሞትና የህማም በሽታ ዳግመኛ አይቅረብ፡፡
32- ሰብሃት ለአብ
ሰራችንን ላሳመረልን ለአብ ምስጋና ይገባል፡፡ ፈጥኖ ለረዳን ለወልድም ምስጋና ይገባል፡፡ ስልጣንን ለሰጠን ለመንፈስ ቅዱስም ሰላምታ ይገባል፡፡ ቃልኪዳንን የያዝሽ አርሴማ ሆይ የታመነ ምስጋናሽን አነበንባለሁ፡፡ ኃጥአንን ታማልጅ ዘንድ፡፡ የቅድስት አርሴማ አምላክ ሆይ ከነፍስና ከሥጋ መከራ አድነን፡፡ ጠብቀንም፡፡
0 comments:
Post a Comment