ክፍል ሶስት መልክዐ ተክለሃማኖት
፪ ሰላም ለዝክረ ስምከ በጥንተ ፊደሉ መስቀል
ስም ክቡር ወስምልዑል።
ተክለሃማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል
ከመእወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል።
ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕማርያም ድንግል።
ትርጉም <<የስምሀ መነሻ ፊደል የመስቀል ምልክት ለሆነው እና ክቡር ገናና ለሆነው ስምአጠራርህ ሰላም እላለው ። የወንጌል ተቀዳሚ ስም ማቴዎስ የተባልክ ተክለሃይማኖት ሆይ እንደችሎታዬ አመሰግንህ ዘንድ አንደበቴ ትፈታልኝ ዘንድ ድንግል ማርያምን እማልዳለሁ። >>
የአባታችን የቅዱስ ተክለሃማኖት የስማቸው መነሻ ፊደል‘’ተ’’ የመስቀል ቅርጽ ያለው ነው የስማቸውም ትርጉም ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው ይህም በስማቸው ላይ ስመ እግዚአብሔር እንዳለ ያስረዳናል በገድላቸው እንደተጻፈው ይህንን ስም አባታችን ያገኙት የመንፈሳዊ ተጋድⶀአችው የቅርብ ረዳት በሆነው በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት ነው ገድ ተክ፳፰ ፤፲፪ የቀድሞ ስማቸው ፍስሐ ጽዮን ነው ትርጉሙም የጽዮን የቤተክርስትያን ፤የእመቤታችን ደስታ ማለት ነው ። በአጠቃላይ የአባታችን የቅዱስ ተክለሃይማኖት ስም የእግዚአብሄርን ክብር የሚገልጽ ልዩ መንፈሳዊ መልክዕት የያዘ ስም ነው። ስለስማቸው ለመግቢያ ያህል ይህንን ካልን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዱሳን ስም ምን እንደሚል አንዳንድ ነገሮችን እንመልከት
፩. በቅዱሳን ስም ላይ የእግዚአብሔር ስም ይከብራል
« በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት» ዘጸ፳፫፤፳፩
፪ .የቅዱሳን ስም ከስም ሁሉ የሚበልጥ ነው
«……..ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚበልጥ መታሰቢያ ስም ………» ኢሳ፶፮፤፭
፫.የቅዱሳን ስም ዘላለማዊ እና የማይጠፋ ነው
«የማይጠፋም ዘላለማዊ ስም እሰጣቸዋለሁ» ኢሳ፶፮፤፮
፬. በቅዱሳን ስም የእግዚአብሔር ቤት እና ቅጽሩ በመታሰቢያነት ይሰየማል
«በቤቴ እና በቅጽሬ ውስጥ……. የዘላለም ስምእሰጣቸዋለሁ» ኢሳ፶፮፤፭
፭. በሰማያዊት ቤተ መቅደስ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ስምቀጥሎ የቅዱሳኑ ስም ተጽፎአል
«በእነርሱም የአስራ ሁለቱ የበጉ ሃዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር» ራእይ ፳፩፤፲፬
፮. በቅዱሳን ስም ዝክር ማዘከር ፤ በጎ ሰራ መስራት ሰማያዊዋጋ አለው
«ከነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻበደቀመዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋባትም ።» ማቴ፲፤፵፪
እንግዲህ የቅዱሳኑ ስም ይህን ያህል የከበረ ከሆነ ለከበረው ስማቸው ሰላምታ መስጠት ምን ነውርነት አለው ? ስማቸው የእግዚአብሔር ስም የሚገለጥበት ከሆነ ለስማቸው ክብር መስጠት የእግዚአብሔርን ስም ማክበር አይደለምን ? ስማቸው በሰማያዊት ቤተ መቅደስ በክብር ከተጻፈ በስማቸው የእግዚአብሔር ቤት የሚሰየም ከሆነ ለስማቸው ክብር ሰላምታመስጠት እንዴት ሊገርመን ይችላል ? ? በስማቸው የሚሰራ በጎስራ ሰማያዊ ዋጋ ካለው የቅዱሳኑን ስም በማወደስ ጸጋና በረከትአይገኝምን ? በአባታችን በቅዱስ ተክለሃይማኖት መልክዐ ጸሎታቸውም ላይ ለስማቸው ሰላምታ እና በጸጋ ምስጋና ቢቀርብላቸው መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያድረገ ነው ከላይ እንደተዘረዘርው እግዚአብሔር አምላክ የወዳጆቹን ክብር በስማቸው ቀርቶ በለበሱት ልብስ ፤ በረገጡት መሬት ፤በጥላቸውስ እንኳን ሳይቀር ይገልጽ የለምን ? ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ እራፊ ጨርቅ ድውያንን ይፈውስ ነበር፤ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ድውያንን ይፈውስ ነበር (የሐዋ፭፤፲፭ የሐዋ፲፱፤፲፪) ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን በቅዱሳኑ ስም እግዚአብሔር ድንቅስራዎችን እንደሚሰራ ያምናሉ በስማቸውም የቅዱሳንን አምላክ ይማጽናሉ ስለዚህም ነው የአባታንን ስም እያነሱ መጸለይ ተግቢ መሆኑን ከመልክዐ ጸለታቸው የተመለከት ነው።
፫. ሰላም ለስእርተ ርእስከ በኅሊና አምላክ ዘተፈቅዳ ።
እንተ ቦን ግልባቤ አምሳለ ሠላስ ደቂቀ ይሁዳ።
ተክለ ሃይማኖት ማርቅስ ጸሐፌ መንክራት ውስተ ሰሌዳ ።
አበውእ ለከ እግዚኦ ዘስብሐተ ጋዳ።
ህየንተ ወርቅ ወብሩር ጸዐዳ።
ትርጉም እንደ ይሁዳ ልጆች መጎናጸፍያ ለሆኑትና የቁጥራቸው ብዛት በአምላክ ዘንድ ለሚታወቅ በራስህ ላይ ለሚገኝ የጸጉርህ ብዛት ሰላም እላለሁ ። እንደ ቅዱስ ማርቆስ ድንቅ የምትሆን ወንጌልን የጻፍክና የሰበክ ተክለሃይማኖት ሆይ በወርቅ በብር ፈንታ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርብልሃለሁ። ይህ ሰላምታ ከአባታችን ተክለ ሕዋሳት መካከል የጸጉራቸውን ክፍል የሚያወድስ ክፍል ነው ከንባቡ እንደምንረዳው የአባታችን የጸጉራቸው ብዛት በአምላክ ዘንድ እንደሚታወቅ ይገልጻል ።ይህም እውነት ነው ጌታ በወንጌል ሲያስተምር እንኳንስ የአባታችን የእያንዳንዳችን የጸጉር ብዛት በእግዚአብሔር የተቆጠረ መሆኑንገልጾልናል
«የእናንተ የራሳችሁ ጸጉር ሁሉ እንኳን የተቆጠረ ነው» ሉቃ፲፪፤፯
ስለዚህም በመልክዐ ጸሎታቸው ላይ የአባታችን የራሳቸው ጸጉር ብዛት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሚታወቅ መገለጹ ትክክል ነው ማለት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ልዑል እግዚአብሔር በመረጣቸው ቅዱሳን በጸጉራቸውም ሳይቀር ኃይሉን እንደሚገልጽ ስለ ጸጉራቸው በተለየ ሁኔታ የተነግረላቸውን መስፍኑ ሶምሶንን እና መጥምቁ ዮሐንስን ማንሳት ሃሳቡን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል። በሶምሶን ላይ የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጸው በጸጉሩ ነበር ለዚህም ነው ሶምሶን እራሱ እንዲህ በማለት የተነገረው
«እኔ ከናቴ ማህጸን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየው ሰው ነኝበራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም የራሴንም ጸጉር ብላጭ ኃይሌ ከኔ ይሄዳል እደክማለሁም እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ» መሳፍ ፲፮፤፲፯
አዎ ቅዱሳንን እግዚአብሔር ከማህጸን ጀምሮ ይመርጣል በተለያዩ የህዋሳት ከፍሎቻቸውም ኃይሉን ይገልጻል አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም በፈቃደ አምላክ በብስራተ መልአክ ከማህጸን የተመረጡ ጻድቅ ናቸው ከራስ ጸጉራቸው አንስቶ መላ ህዋሳቶቻቸውን ለእግዚአብሄር የተለዩ ናቸው ስለዚህም በመላአካላቸው ሊወደሱ ሊመሰገኑ ይገባል።
ሌላው በዚህ ክፍል ላይ የተገለጸው አባታችን ልክ እንደ ቅዱስ ማርቆስ ግሩም ድንቅ የምትሆን ወንጌልን እንደጻፉና እንደሰበኩ ነው። በዕርግጥም አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት ሐዲስ ሐዋርያ የወንጌል ሰባኪ ናቸው በሰው ልብ ላይ ወንጌልን ስለጻፉ ’የወንጌም ጸሐፊ ናቸው። ቅዱስ ተክለሃይማኖት ወንጌልን አልሰበኩም የሚል ተከራካሪ ቢነሳ ግን ገድላቸውን አንብበህ ፍረድ ከማለት ውጭ ምንም ሊባል አይቻልም። በምድረ ኢትዮጵያንደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተዘዋውረው ብዙዎችን ከአምልኮተ ጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ የመለሱ ቅዱስ ተክለሃይማኖት አይድሉምን ? ከዚህ በላይ ወንጌልን መስበክ አለን ? ቅዱስ ማርቆስ ከግብጽ ጣኦታት ጋራ ብዙ መከራ እየተቀበለ ተጋድሎ ወንጌልን እንደሰበከ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም በአገራችን ይተለያዩ ስፍራዎች በመዟዟር ብዙ መከራ እየተቀበሉ አምልኮተ ጣኦትን እያጠፉ ወንጌልን ሰብከዋል ለዚህም ነው በወንጌላዊው በማርቆስ የተመሰሉት። የአባታችንን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ትሩፋትንና ገድልን አልመስከር ለኢትዮጵያ ምድር ከቶ አይሆንላትም በምድሪቱ ላይ የተከተቡ የታሪክ አሻራዎች በሙሉ አባ ተክለ ሃይማኖት አባተ ክለሃይማኖት እያሉ ይጮሃሉና።
ይቆየን
0 comments:
Post a Comment