• በቅርብ የተጻፉ

    Monday, 16 November 2015

    ቅድስት እንባመሪና


    የቅድስት እንባመሪና እናት ማርያም ትባላለች ገናም ህጻን እያለች ነበር በሞት የተለየቻት ከዛም አባቷ ለአቅመ ሄዋን እስክትደርስ ድረስ በጎ ትምህርቶችን ሲያስተምራት አሳደጋት በኋላም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ አጋቧት::እርሱ ወደ መነኮሳት መኖሪያ ሄዶ ሊኖር እንደወደደ ሲነግራት እጂግ አልቅሳ "አባቴ ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ማጥፋት እንዴት ይሆንልሃል ?" አለችውና አባቷም እኔ የምሄደው ወደ ወንድ መነኮሳት ነው አንቺን ደግሞ ሴት ነሽ አያስገቡሽም ሲላት እንደወንድ ሱሪ አድርጌ ጸጉሬን ተቆርጬ ወንድ መስዬ ካንተ ጋር ሄዳለው አለችውና::ያላቸውን ንብረት ሁሉ ሽጠው እና ለደሃ መጽውተው ተያይዘው ገዳም ይገባሉ:: በዚያም ገዳም እጅግ እየተጋደሉ ኖሩ:: በኋላም አባቷ በጸና ስለታመመ አበ ምኔቱን አስጠርቶ ልጄን አደራ በምንም መልኩ ከገዳም እንዳይወጣብኝ ይልና አበ ምኔቱን አደራ ይለውና ያርፋል::ቅድስትእንባመሪናም ተጋድሎዋን ከቀድሞ እጅግ አብዝታ ትተጋ ጀመር:: ከረጅም ግዜ በኋላም የገዳሙ መነኮሳት ይሄ መነኩሴ ከኛ ጋር ለምንድን ነው ከገዳም ውጪ ለተልኮ የማይወጣው እያሉ አበ ምኔቱን አስጨነቁት በኋላም አበ ምኔቱ ከመነኮሳቱ ጋር አብሮ ይሰዳት ጀመር የሚሄዱትም የገዳሙን ምግብ በየግዜው ከሚሰበስብላቸው አንድ ሰውዬ ቤት ነበር: እንዳስለመዱት በየግዜው ሲሄዱ አንድ ቀን ምግቡን የሚሰጣቸው ሰውዬ አንዲት ልጅ አለችውና ጎረቤት የሆነ አንድ ጎረምሳ ተደብቆ ይገባና የሰውዬውን ልጅ ድንግልናዋን ያፈርሳል በኋላም አባትሽ ማነው እንዲ ያደረገሽ ብሎ ከጠየቀሽ እንባመሪና ነው በይ ይላትና ይሄዳል:: ልጅቷ ታረግዛለች በኋላም አባትየው ከማን እንዳረገዘች ሲጠይቃት ከመነኩሴው ከእንባመሪናነው አለችው::

    ከዛም ያ ሰውዬ ወደ ገዳሙ ይመጣና ባአደባባይ መነኮሳቱን ይረግማቸው ጀመር ከዛ አበ ምኔቱ መጣና ምን ሆነህ ነው ቢለው ልጄን ያንተ መነኩሴ ደፍረብኝ ሲለው ታድያ ባንድ ሰው ጥፋት እነዚን ሁሉ ቅዱሳን ለምን በአደባባይ ትረግማለህ አለውና እንባመሪናን አስጠራት:መጣችና አቤት አባቴ ስትል ሁሉም ይሰድቧት ጀመር ለምን እንደሚሰድቧት ባታቅም ሰይጣን የሰራባት ነገር እንዳለ ገባት እና ዝም አለች:: በኋላም ነገሩን ነገሯት እና አበ ምኔቱ "እንባመሪና ይህ የመነኩሴ አይደለም የአለማውያን ባህሪ አይደለም የሴጣን እንጂ ይህን ለምን አደረክ?"ብሎ ቢጠይቃት እርሷም አባቴ ይቅር በለኝ ወጣትነት አታሎኝ ነው አባቴ ይቅር በለኝ ብላ አበ ምኔቱ እግር ስር ወደቀች:: 
    በኋላም አበ ምኔቱ ከገዳሙ አባረራት እና ከገዳሙ ውጪ ሆና ትጋደል ጀመር ያቺም ልጅ ስትወልድ አባቷ ልጁን አምጥቶ ለእንባመሪና ሰጣት እንባመሪናም ለልጁ የሚሆን ወተት እና ምግብ በአካባቢው ያሉትን እረኞች እየለመነች አሳደገችው::
    ከ3 አመት በኋላም መነኮሳቱ አበ ምኔቱን ለመኑት ባይሆን ከባድ ቀኖና ይሰጠውና ወደ ገዳም ይግባ አሉት:አበ ምኔቱም ልመናቸውን ተቀብሎ ከባድ ቀኖና ሰጣት እና ስትጨርስ ወደ ገዳሙ ተቀላቀለች ከዛም ገዳሙ ውስጥ ያሉትን ከባድ ስራዎች ያሰራት ጀመር ከዛም በኋላ ገዳም ውስጥ ጭንቅ የሆኑ ስራዎችን ያሰሯት ጀመር የመነኮሳቱን ቤት ጠርጋ ተሸክማ ወስዳ ከገዳም ውጪ አውጥታ ትጥላለች: ያም የተወለደ ልጅ አድጎ እዛው መነኮሰ 40 አመትም ከተፈጸመ በኋላ ቅድስት እንባመሪና 3ቀን ታማ አረፈች:: ከዛም የገዳሙ መነኮሳት ተሰብስበው ደውል ደውለው ተሰበሰቡ ሊገንዟትም ፈልገው ልብሷን ሲያዎልቁት ሴት ሆና ሲያገኟት እጅግ አዝነው አበ ምኔቱን አስጠሩት:አበ ምኔቱም የተፈጠረውን አይቶ እጅግ አዝኖ አለቀሰ ያለበደሏ የሰጣትን ቅኖና እና የተናገራትን ተግሳጽ እያሰበ አምርሮ ያለቅስ ጀመር:: ከዛም ያን የልጅቷን አባት አስጠርቶ የሆነውን ሁሉ ነገረው ከዛም በድንዋን ተሸክመው አቤቱ ይቅር በለኝ እያሉ ዋሉ ማምሻውን ላይ የቅድስት እንባመሪና አስክሬን "እግዚአብሔር ይቅር ይበላቹ" ሲላቸው አውርደዋት በታላቅ ክብር ከስጋዋም ተባርከው ቀበሯት ከመቃብሯም እጅግ ብዙ የሆነ ድንቆች ተአምራት ተደረጉ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ጻድቅ ጸሎት ይማረን: ይቅርም ይበለን የቅድስት እንባመሪና በረከት አይለየን አሜን !!!

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ቅድስት እንባመሪና Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top