የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
መግቢያ ፡-
መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ እንደሚያመለክተው “መጽሐፍ”እና “ቅዱስ” የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ነው ፡፡በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ(byblos) ከደንገል በተሠራወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለትበትሮች የሚጠቀለል መጽሐፍ ያመለክታል ፡፡ቢብሎስ በእንግሊዘኛው ባይብል ተብሎ ሲተረጎምበአማርኛው ደግሞ መጽሐፍ በሚለው ቃልተተረጐመ ፡፡ የግሪኩ ቃል ቢብሎስ(byblos) እራሱቢብሎስ(byblos) ከተባለ ከተማ ስም የተገኘ ነው፤ እርሱም ከኒቂያ ወደቦች መካከል በቤይሩት 25ማይል ያህል ርቆ የሚገኝ አገር ነው ፡፡ ለመጽሐፍያገለግል ዘንድ ፓፒረስ (ደንገል) የተባለውን ተክልእንደ ወረቀት አድርገው ይሠሩበት የነበረ ቦታ ነው ፡፡
ሁለተኛው ተጠማሪ ቃል “ቅዱስ” የሚለው ሲሆንትርጓሜውም የተለየ ማለት ነው ፡፡ ሰው ወይምማንኛውም ነገር ለእግዚአብሔር አገልግሎት ሲለይቅዱስ ይባላል ፡፡ ሰዎች (ዘጸ 28, 41) ፣ እንስሳት(ዘጸ13, 2) ፣ ቦታዎች (ዘጸ 3, 5) ቀኖች (ዘፍ 2, 3)፣ ማናቸውም ነገር ቅዱስ ሊባል ይችላል (ኢያሱ 6, 19) ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥምረት ወደሆነው“ቅዱስ” ወደሚለው ቃል ስንመጣ ደግሞ ይህመጽሐፍ እንደማንኛውም ተራ መጽሐፍ የሚታይሳይሆን የተቀደሰና የተለየ መሆኑን ከማሳየቱምአልፎ የጻፉት ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይልተሞልተውና ተመርተው እንደነበር ያስገነዝባል ፡፡በእርግጥም የጻፉት ሰዎች ከራሳቸው ልቦናፈጥረው ወይም አንቅተው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስአነሳሽነትና በእግዚአብሔር እየተመሩና እየታዘዙየጻፉት ነው (ዮሐ 14, 26) ፡፡
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርህልውናውንና ፈቃዱን ረቂቅ ባሕሪውን በተወሰነመልኩ የምንረዳበትንና ፈቃዱንም ምን እንደሆነማወቅ የምንችልበት በእግዚአብሔር በራሱ መንፈስመሪነት የተጻፈና ለሰው ልጆች የተሰጠ(የተገለጸ)ቅዱስ ቃል ነው ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚለው “ከመጀመሪያውስለነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን ፤ ይህየሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይኖቻችን ያየነውየተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው ነው ፡፡ ይህሕይወት ተገልጦአል ፤ እኛም አይተነዋል ፤እንመሰክራለንም ፡፡ በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛምየተገለጠውን የዘላለም ሕይወት እንነግራችኋለን ፡፡ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንናየሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን ፡፡ኅብረታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስጋር ነው ፡፡ ደስታችንም ሙሉ እንዲሆን ይህንእንጽፍላችኋለን” (1 ዮሐ 1, 1-4) ፡፡
በአጠቃለይ መጽሐፍ ቅዱስ “ዘላለማዊ ሕግ”ሲሆን ዓላማውም ሰዎችን ለሰማያዊ መንግሥትማብቃት ነው ፡፡ ስለዚህ ከሌሎች የሳይንስ ፣የልቦለድና የፍልስፍና መጽሐፍት ፈጽሞ ይለያል ፡፡ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔርመንፈስ መሪነት ከመጻፉ አልፎ የሚያነቡትናየሚሰሙትን የሚመክር ፣ የሚገስጽ ፣ የሚያረጋጋናወደ ደኅንነት ሊያደርስ የሚችል ጥበብ ያለውበመሆኑ ነው (2 ጢሞ 3, 14-17 ፣ ሐዋ 13, 16) ፡፡ከዚህም በላይ መጽሐፍ ቅዱስ ጣፋጭ የሆነየሚበላ ሰማያዊ ስንቅ (ሕዝ 3, 1-3) ፣ ብርሃን ሆኖየሚመራ (መዝ 119, ቁ. 105) ፣ አጽናኝና መካሪመሆኑን በተለያዩ ቦታዎች ተገልጾ ይገኛል ፡፡ ስለዚህመጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የተገኘና እርሱበመረጣቸው ቅዱሳን ሰዎች በራሱ መንፈስ መሪነትየተጻፈና ከሰው ልጅም ጋር ቃል ኪዳን ያጸናበትቅዱስ ቃል ነው ፡፡
በጥንት ዘመን ግን (እስከ 100 ዓ. ም ድረስ)የቅጠል ዓይነት መጽሐፍት (አሁን ያለው ዓይነት)ስላልነበር መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ቃል “ጥቅልል”በሚል ስም ይታወቅ ነበር ፡፡ የጥቅልል ርዝመትዐሥር ሜትር ሊደርስ ይችል ነበር፡፡ ጽሕፈቱምበዐምዶች ላይ ነበር (ኢሳ 34, 4 ፣ ኤር 36, 2 እና20-23 ፣ ሕዝ 3, 1-3 ፣ ሉቃ 4, 17-19 ፤ 2ዮሐ 12፣ ራእ 5, 1 ፣ 2ጢሞ 5, 13)፡፡ ባጠቃለይ መጽሐፍቅዱስ የተጻፈበት ዘመን በወረቀት ወይም በብራናየተጻፈውን ሲያመለክት የጥቅልል መጽሐፍ እንጂበቅጠል ላይ የተጻፈ መጽሐፍ አልነበረም ፡፡
በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ የቅዱሳት መጻሕፍትመዝገብ ነው ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብሉይኪዳንና አዲስ ኪዳን ናቸው ፡፡ ብሉይ ኪዳን ከ1400 - 400 ከክ.ል.በ በልዩ ልዩ ቦታዎች አርባ በሚያህሉልዩ ልዩ ጸሐፊዎች እንደተጻፈ ይነገራል ፡፡ አዲስኪዳን ከ45-96 ዓ. ም በስምንት ሰዎች ተጻፈ ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የእግዚአብሔርመንፈስ ለምን አስፈለገ ?
የእግዚአብሔር መንፈስ ካስፈለገባቸው ጥቂትምክንያቶች ውስጥ ለመጥቀስ ያህል ፦
· የሰው ልጅ አስቦ ሊደርስባቸው የማይችላቸውንእጅግ በጣም ጥልቅና ረቂቅ የሆኑ ነገሮችን የያዘመጽሐፍ በመሆኑ
· ያለ ስህተትና ምንም ዐይነት ልዩነት ሳያንጸባርቅእንዲጻፍ (የዘር ፣ የቀለም ፣ የጎሳ ፣ የጾታ )
· አንድ ዓይነት የሆነ የሃይማኖት የሥነ ምግባርሥርዐት እንዲኖር ለማድረግ
· እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚፈልጋቸውን ጉዳዮችእንዲጻፉና የማይፈልጋቸው ጉዳዮች እንዳይጻፉለማድረግ ፤ ይህም ማለት በመንፈሱ በመመራትትክክለኛውን ቃሉ መጻፍ እንዲቻል
· የሰው እውቀትና ችሎታ እጅግ በጣም የተወሰነናየተገደበ ነው ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ምስጢራዊ፣ ከሰው አእምሮና ጠቅላላ ችሎታ በላይ ስለሆነይህንን ቃል ለመጻፍ የእግዚአብሔር መንፈስ ድጋፍእጅግ በጣም ያስፈልግ ነበር ፡፡
· ሐዋርያው ጳውሎስ ሲናገር “ለእኛ ግንእግዚአብሔር በመንፈሱ አማካኝነት ምስጢሩንገልጦልናል ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ዕቅድ እንኳሳይቀር ሁሉን ነገር ይመረምራል ፡፡ ስለ ሰው የሆነእንደሆነ ከገዛ ራሱ መንፈስ በቀር በእርሱ ያለውንአሳብ የሚያውቅ ሌላ ማንም የለም ፤ እንዲሁምከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርንአሳብ የሚያውቅ ማንም የለም” (1 ቆሮ 2, 10-11)፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር የተናገረውን ተረድቶለመጻፍ የራሱ መንፈስ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በምን ዐይነት መልክ ነው እግዚአብሔርቃሉን ወደ እነሱ እንዲደርስ ያረገው?
እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ቃሉን ወደሚያደምጡት ቅዱሳኖች አስተላልፏል ፡፡ ቃሉለእነሱ ከመግለጹ በፊት ግን የእነሱ በጎ ፈቃደኝነትይጠይቃል ፡፡ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ተገዶናነጻነቱ ተነፍጎ አይደለም የሚጽፈው ፡፡ ጸሐፊው በበጎፈቃደኝነቱና በነጻነት ራሱን ያዘጋጃል ፤ ከዚያምእግዚአብሔር የገለጸለትን ቃል በራሱ ቋንቋ ፣ባሕልና የአጻጻፍ ዘይቤ መሠረት ቃሉን ይጽፋል ፡፡እግዚአብሔርም ቃሉን በሚከተሉት መንገዶችለጸሐፊዎች ይገልጻል ፦
· 1/ ቃል በቃል በማነጋገር ፦ ሙሴን አንዳነጋገረውእግዚአብሔር ቃሉን በንግግር መልክ ይገልጻል ፡፡ለምሳሌ “በድንገትም እግዚአብሔር ሙሴን ፣አሮንና ሚርያምን እናንተ ሦስታችሁ እኔ ወደምመለክበት ድንኳን ኑ አላቸው ፤ እነርሱም ሄዱ ፤እግዚአብሔርም በደመና ዐምድ ወርዶ በድንኳኑደጃፍ በመቆም አሮን ሚርያም ብሎ ጠራቸው ፤ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ ፤ እግዚአብሔርም እንዲህአለ እነሆ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ…..እኔከእነርሱ ጋር ቃል በቃል በግልጥ እነጋገራለሁ” (ዘኁ12, 4-8) ፡፡
· 2/ በሕልም በመግለጽ፦ (ዘፍ 37, 5)
· በትንቢትና በራእይ ራሱን በመግለጥ ፦እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል “እኔ እግዚአብሔርበራእይ እገለጥለታሁ” (ዘኁ 12, 6) ፡፡ “የምታየውንበመጽሐፍ ጽፈሕ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተክርስቲያናት ላክ አለኝ” (ዮሐ 1, 10-11) ፡፡
· ያዩትንና የሰሙትን ልብ ብለው አስተውለው ያንኑእውነታ ብቻ እንዲጽፉ በማድረግ ፦ ቅዱስ ዮሐንስእንደጻፈው “ገና የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ ፤የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉይመራችኋል ፤ ምክንያቱም እርሱ የሚናገረውየሰማውን እንጂ የራሱን አይደለም ፡፡ እርሱ ወደፊትየሚሆኑትን ነገሮች ይነግራችኋል” (ዮሐ 16, 12) ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ዋና ዓላማውምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፉባቸው ዓለማዎች እጅግበጣም ብዙ ናቸው ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በጥቂቱለመግለጽ ያህል ፦
· የእግዚአብሔርን ማንነት ለማወቅና ለመረዳትእንዲሁም እውነተኛና ዘላለማዊ አምላክ መሆኑንተገንዝበን እንድናመልከውና ፈቃዱን ፈጽመንበሕይወት እንድንኖር (1 ዮሐ 1, 1-4 ፣ ማቴ 28, 20፣ ሮሜ 15, 4) ፡፡
· ሥጋን ለብሶ የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅጌ.ኢ.ክ እግዚአብሔር እንደሆነ አምነን በስሙምዘላለማዊ ሕይወትን አንድናገኝ (ዮሐ 20, 30-31 ፣1 ዮሐ 5, 13) ፡፡
· “እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማናበላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው” (ዮሐ 5, 24) እንዳለው በእግዚአብሔርና በልጁበጌ.ኢ.ክ አምነን የዘላለም ሕይወት እንድንወርስ ፡፡
· የሰው ልጅ በጥሩ ሥነ ምግባር ማደግ ወይምመታነጽ እንዲችል የተጻፈ ነው ፡፡ የሰው ልጅሊፈጽማቸው የሚገቡ ሥነ ምግባራት በብሉይምሆነ በአዲስ ኪዳን ተገልጸዋል (ዘጸ 20, 7-17 ፣ማቴ 5, 21) ፡፡ ባጠቃላይ የሰዎች ሥነ ምግባርጥሩ መሆን ብቻ ሳይሆን ከክፋት መራቅና ፈተናንማለፍ የሚችለው በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸውእግዚአብሔርን በማወቅና እርሱን በመፍራት ላይሲመሠረት ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን እንዴት አድርጋ ነውእነዚህ መጻሕፍት ሁሉ አግኝታ በአንድመጽሐፍ ውስጥ የሰበሰበቻቸው?
· ከመጀመሪያ ጀምሮ ቤ∕ክ አይሁድ ያወቁአቸውንየብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ተቀበለች፡፡ ቀጥላምበሐዋርያት ወይም በሐዋርያት ሥልጣን የተጻፉትንመጻሕፍት ሰብስባ እንደ እግዚአብሔር ቃልተቀበለቻቸው ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶች የአዲስኪዳን መጻሕፍት እየጠቀሱ አስተማሩ ፡፡ ቅዱስአትናቴዎስ በ367 ዓ.ም በጻፈው በፋሲካ ዕለት ቃለበረከት ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትሃያ ሰባት ብቻ መሆናቸውን ተናግሯል ፡፡ እንደዚሁምበ397 ዓ.ም በሰሜን አፍሪካ በካርታጎ (በካርቴጅበቱኒዚያ) የተደረገው ሲኖዶስ ሃያ ሰባቱን መጻሕፍትአጸደቀ፡፡
· በሌላ መልኩ በዕብራይስጥ የተጻፉ ብዙ የብሉይኪዳን ቅጂዎች የነበሩ ቢሆንም የመጀመርያው ቅጂበ200 ከክ.ል.በ ገደማ ተጻፈ ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትበጥንት ዘመን በጥቅልል እየተጻፉ በልዩ ልዩምኩራብና ቤ∕ክ ይሰበሰቡና ይነበቡ ነበር ፡፡ቅደም ተከተላቸውም ልዩ ልዩ ነበር ፡፡ ለምሳሌአትናቴዎስ ሰባቱን መልእክታት ከጳውሎስመልእክታት አስቀድሟል ፡፡ የካርታጎ ሲኖዶስ ግንየመጻሕፍቱን ተራ እንደ አሁኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ተራአድርጎ አጽድቋል ፡፡
ይቀጥላል.....
0 comments:
Post a Comment