· እሩቅ ነው……………………....ጥበቡ አይታወቅምና
· ቅርብ ነው………………………ቶሎ ይሰማልና
· መኮንን ነው………………… ቶሎ ይፈርዳልና
· እንግዳ ነው…………..……….ቶሎ ወሬ ይሰማልና
· ትሁት ነው………………..….ሰውን አይንቅምና
· መሐሪ ነው ……………..…..ይቅር ይላልና
· ባለጠጋ ነው……………..…. ለሁሉ ይመግባልና
· ሃኪም ነው……………..…….ሁሉን በጥበብ አድርጓልና
· ምስጉን ነው……………..…. ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሯልና
· ረቂቅ ነው…………………… አይጨበጥምና
· ግዙፍ ነው …………………….በዓለም ሁሉ ሞልቷልና
· ብሩህ ነው……………………….ጨለማ የለበትምና
· ኃያል ነው………………………የሚቋቋመው የለምና
· እሳት ነው…………………….. ሁሉን አስፈሪ ነውና
· መካር ነው……………………..መጻሕፍትንና ነቢያትን እንዲሁም ሐዋርያትን ሰጥቶናልና
· አባት ነው……………………. በፍቅር አሳድጎናልና
· ወንድም ነው………….……. ሰው ሆኖ ወንድሞቼ ብሎናልና
· ወዳጅ ነው……………….….. የሆዱን ሁሉ ነግሮናልና
· አገር ነው ……………….……..እንኖርበታለንና
· ገናና ነው…………………….. የሚቋቋመው የለምና
· ታላቅ ነው………………….. ስፍራ አይበቃውምና
· ጥልቅ ነው………………….. የሰው አእምሮ አይደርስበትምና
· ፋሲካ ነው………………….. ለሁሉ ታርዷልና
· ጨው ነው…………………... ሁሉን ያጣፍጣልና
· እንግዳ አይደለም………… ከጥንት የነበረ ዘላለምም የሚኖር ነውና
0 comments:
Post a Comment