በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በክርስቶስ ክረስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊያን የተሰችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም የአሥራት የበርከት ልጆች በወደደንና በመረጠን በአምላካችን በልዑል እግዚአብሔር ሰላምታ እንደምን ሰነበታችሁ አመላካችን ቢወድና ቢፈቅድ ወቅቱን በተመለከተ ስብከት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ የምናስተውሉበትን ልቦና ልዑል አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈሱን ለሁላችን ያድለን፡፡
ቃሉን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንቀጸ ብፁዓን ተብሎ በሚጠራው በተራራው ስብከቱ ነው፡፡ የቃሉን ፍቺ ስንመለከት ስለ ጽድቅ የሚስደዱ ብፁዓን ናቸው ማለት ስለ እግዚአብሔር ፍቅር፣መንግሥት፣ በረከት፣ ረድኤት ብለው ከትውልድ ሀገራቸው ተለይተው ከከተማ ከሕዝብ ርቀው በምድር የላመ የጣመ ምግብ ሳይመገቡና ሣይጠጡ ለቁመተ ስጋ ብቻ ያገኙትን ቅጠል የሚመገቡ ይህችን ዓለም የጠሉ አባቶች እናቶች እነሱ የተመስገኑ ቅዱሳን፣ የተመረጡ ቡሩካን፣ የተለዩ ምስጉኖች ማለት ነው፡፡
1.1 ሰደት መቼ ተጀመረ ?
በዓለመ መላዕክት ነው፡፡ እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ከፈጠራቸው ከሰባቱ ሥነ-ፍጥረታት ውስጥ መላዕክት ናቸው፡፡ ከፈጠራቸው በኋላ የተሰወረባቸውም የእርሱን አምላክነት ምሀሪነት ሁሉን ቻይነቱን ይረዱ ያውቁ ዘንድ ተሰወረባቸው፡፡ የመላእከት አለቃ የነበረ ሳጥናኤል እኔ ፈጠርኳችሁ በማለት ብዙዎችን አሳተ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሚካኤል ሃይማኖታችንን እስከ ምናውቀው ባለንበት እንቁም(ንቁም በበህላዊነ እሰከ ንረክቦ ለአምላክነ) ብለው መላዕክትን አጽናኑ፡፡ ሳጥናኤልና ከሰማይ ወደዚህ ዓለም(ምድር) ተሰደዱ ስደትም በእዚያን ጊዜ ተጅመረ፡፡
1.2 ሰዎች የሚሰደዱበት ምክንያት
ሀ/የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመተላለፍ፡- የሁላችን አባት አዳም አትበላ ተብሎ ከተከለክለው ከዕፀ በለስ በመበላቱ ገነት ከሚያህል ቦታ እግዚአብሔርን ከመሰለ አምላክ ተሰደደ፡፡ ዘፍ 3፥8
ለ/ረሀብ ቸነፈር ሲመጣ ፡- አንደ አባታችን ቅዱስ ያዕቆብ በሀገሩ ለአመስት ዓመት ረሀብ ሆነ እግዚአሔርም ያዕቆብን በሕልም አነጋገረው ወደ ግብፅ ሀገር ሂድ ብሎ ነገረው እርሱም ተሰደደ ዘፍ 46፥11
ሐ/የሰውን ነፍስ በማጥፋት የሚሰደዱ ፡- ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ አደገ ወደ ወንድሞቹም ወጣ መከራቸውንም ተመለከተ የግብፅ እና አንድ ዕብራዊ ሲጣሉ አገኛቸው ለዕብራዊውም በማገዝ ግብፃዊውን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ቀበረው፡፡ በሁለተኛ ቀንም ወጣ ሁለት ዕብራዊያን ሲጣሉ አየ ሙሴም በዳዩን ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ አለው፡፡ ወንደሙን ሚበድለውን ያም ሰው በእኛ ላይ አንተን አለቃ ዋስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብጻዊውን ትናንት እንደገደለኸው ልትገድለኝ ትሻለህን? አለው፡፡ሙሴም በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን ብሎ ፈራ፡፡ ፈርዖንም ይህን ነገር ሰማ ሙሴንም ሊገለው ፈለገ ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ በምድያም ምድር ተቀመጠ፡፡ ዘጸ 2፥11-16
መ/ለሰው ልጆች ሰላም አብነት ለመሆን የሚሰደዱት ስደት ነው፡፡ ይህ ስደት የጌታችን እና የእመቤታችን ሰደት ነው፡፡ ሰለ ጌታችን እና ሰለ እመቤታችን ሰደት ከመነጋገራችን በፊት ስለ ጌታ ልደት ትንሽ ልበል ጌታችን በቤተልሔም ሲወለድ ቤተልሔም በእሳት አጥር ታጠረች አጋንንትም ሄደን እናያለን ብለው ቢቀርቡ የብርሃን መላዕክት በእሳት ፍላጻ እያቃጠሉ ሊያስቀርቧቸው አልቻሉም፡፡ አጋንንትም ለአለቃቸው ለዲያብሎስ ነገሩት ዳያብሎስም በትዕቢት በኪሩቤል አምሳል 4 ተሸካሚዎችን አዘጋጅቶ ተሸክመውት ቤተልሔም ደረሱ ወደ ጌታም መቅረብ አልቻሉም፡፡ ከዚች ሰዓት ጀምሮ ዲያብሎስ በስልጣኔ ላይ ችግር የፈጠረብኝ ማነው? ብሎ ፈርቶ እየተንቀጠቀጠ ለአጋንንት ከእኔ የሚሰወር የለም ዓለምን ዙሬ ነገሩን መርምሬ ውጤቱን እስክነገራችሁ ታገሱኝ አላቸው፡፡ ሁሉን ቦታ አሰሰ ግን አልቻለም፡፡ መጨረሻ ላይ እነድህ በማለት ተናገረ አስከ ዛሬ ድረስ ከተሰራው ታአምር የሚበልጥ ታላቅ ተአምር ነው አለ ፡፡ ነቢያት ስለ እርሱ ትንቢት የተናገሩለት በቤተልሔም ተወልዶ ከሆነ መንግሥቴን እነደሚቀማኝ አልጠራጠርም እያለ ተጨነቀ አሁንም ኑ ሄደን ጠይቀን እንረዳ ብሎ ሠራዊቱን ይዞ ወደ ቤተለሔም መጣ እረኞች እና መላዕክት በአነድነት ‹‹በሰማይ ለእግዚአበሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ለሰው የሰላም መሠረት ተጣለ›› እያሉ ሲያመሰግኑ ሰምቶ ደነገጠ ፡፡ ሉቃ 2፥12-16
ጌታ ሰለመወለዱ ይነግሩት ዘንድ የእስራኤል የኦሪት ምሁራንን አነሳስቶ ጌታ ከድንግል እስኪ ወለድ ድረስ አትሞትም በአልጋ ላይ ተጣብቀህ ትኖራለህ ተብሎ ከእግዚአብሔር መላዕክት ትንቢት ወደ ተነገረለት ወደ ካህኑ ስምዖን ሄደው ስምዖን ሆይ አንተ ተስፋ የምታደርገው የዓለም መድኃኒት የሆነው ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጫው ደርሷን? በማለት ጠየቁት፡፡ ስምዖንም አዎን መምጫው ደርሷልን አላቸው እርነሱም ጊዜው መድረሱን በምን አወቀህ? አሉት ሰምዖንም ቀድሞ ነቢዩ ኢሳይያስ 7፥14‹‹ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች በድንግልናም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች›› ፡፡ ተብሎ የተነገረውን ትንቢት ተጠራጥሬ ነበር እና ታስሮ የነበረው እጁ ሰለተፈታ መወለዱን በዚህ አውቃለሁ አላቸው፡፡
ሰይጣንም የእስራኤልን የኦሪት ምሁራንን ቆሞ ይሰማ ነበርና ፈጽሞ ታወከ የተንኮል ባሌቤት የሆነው ዲያብሎስም በሄሮድስ ልቡና አድሮ ሄሮድስ! የእኔንና የአንተን ስልጣን የሚቀማን ንጉሥ ተወልዷልና ከተወለዱ 2 ዓመት እና ከእዚያም በታች እደሜ ያላቸውን ሕፃናትን አስገድላቸው አለው፡፡ ሉቃ 2፥25-27 ጌታችን፣ አመቤታችን ፣ሰሎሜ እና ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተሰደዱ፡፡ ‹‹የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሳ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ እሰክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ›› ማቴ2፥13 የሰላም ባሌቤት አምላካችን ለእኛ ሲል የግብፅን በረሃ እንደ ጋለ ብረት የሚያቃጥለውን አሸዋ እየረገጠ አሳቹን ዲያብሎስን ረጋግጦ ከእግራችን በታች ጣለልን፡፡ በእርሱ ስደት የእኛ ስደት ተባረከልን ተቀደሰልን፡፡ ፍጥረታት ሁሉ በመንቀጥቀጥ የሚሰግዱለት እነግሣለው አይል ንጉሥ በሄሮድስ ተሰደደ፡፡
1.3 የጌታችንና የእመቤታችን መሰደድ ምክንያቶች (ነጥቦች)
1/ የአዳምን የ5500 ዓመት ስደት ለመሰደድና ለመባረክ ነው ፡፡
2/ ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደግጽ ይመጣል ፣የግብጽ የእጆቻቸውን ስራውች በፊቱ ይዋረዳሉ ››፡፡ ኢሳ 19፥1 ከግብጽ መመለሱን አስመልክቶ የተነገረውም ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው ፡፡ ‹‹ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ›› ፡፡ሆሴ 11፥2 አንሁም ከግብጽ ወደ ናዝሬት ሄደ ናዝራዊ ይባል ዘንድ ወደ ናዝሬት ሄደ፡፡ ‹‹በኒቢያት ልጄ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደ ምትባል ከተማ
3/ ጌታ ባይሰደድ ሕፃናቱ ሲገደሉ እሱ ከሞት ቢተርፍ ትስብእቱ (ጌታ ሰው መሆኑ) ምትአት ነው ብለው እንዳይሰናከሉ ነው ፡፡
4/ አበነት ለመሆን ለጻድቃን ለሰማዕታት ሰደት ለመጀመር እና የእነሱንን ሰደት ለመባረክ ለመቀደስ ነው፡፡ ሰማዕትነት በሰይፍ መቀላት በእሳት መቃጠለ በመጋዝ መተርተር ብቻ አይደለም ዓለምን ንቆ ወደ ምድረ በዳ መሰደድም ሰማዕትነት ነው፡፡
ዕብ 11፥37-38 በመጋዝ የሰነጠቁአቸው በድንጋይ የወገሯቸውን በሰይፍም ስለት የገደሉአቸው አሉ ማቅ፣ ምንጣፍና ሌጦ ለብሰው ዞሩ፣ ተጨነቁ፡፡ ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናችው፡፡ ዱር ለዱር ተራራ ለተራራ፣ ዋሻ ለዋሻ ፈርኩታ ለፍርኩታ ዞሩ፡፡
5/ የጌታችን የእመቤታችን መሰደድ የቅዱሳን ሰደት ተባርኮላቸዋል የሕይወት እርካታን አገኝተዋል፡፡ ጌታችን በስጣ በምትባል ሀገር እመቤታችን ውኃ እና ቁራሽ እንጀራ ለመነች የሚሰጣት አንድም ሰውም አላገኘችም ሁሉም አባረሯት፡፡ ጌታችን በዓለት ላይ በመስቀል አምሳል ባርኮ ውኃን አፈለቀ ይችም ውኃ ሁለት ጠባይ ሆነች በእዚያች ሀገር ለሚኖሩ ሰዎች መራራ ከሩቅ ለሚመጡ ነጋደውች ከማር የበለጠች ጣፋጭ ሆነችላቸው፡፡ የሕይወትን ውኃና ምግብን ዳግመኛ የማያስርበውን የሚሰጠውን ጌታችን ከለሉት እነዚህ ሰዎችም 2 ጠባይ ካላት ጠጥተው መረራቸው፡፡ ራዕ 21፥6-7 ‹‹ባለማውቅ ጠጥተው ዳግመኛ የሚያስጠማውን ውኃ የዚች ሀገር ሰዎች ከለከሉት››
እርስ በእረሳችን እንከባበር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ እንሠራ ርኅራኄን በጎነትነን ሀበቶቻችን እናድርጋቸው በረከትን ለማገኘት እግዚአብሔርን እንፈልገው ት.ሶፎ 2፥3 እግዚአብሔርን ፈልጉ ፍርድንም አድርጉ ጽድቅንም ፈልጉ፡፡ ዕብ 12፥4 ‹‹ኃጢአትን ተጋደሏት አሸንፏትም ፣ተስፋችሁንም የምታሰጣችሁን ትምህርት ውደዷት››፡፡
- ‹‹ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች ››ት..ሕዝ 18፥4
0 comments:
Post a Comment