• በቅርብ የተጻፉ

    Sunday, 25 October 2015

    ቅዱስ ጳውሎስ

    የቀደመ ስሙ ሳዉል ነበር፥የተጠራው ከደማስቆ ጐዳና ነው።ከሊቀ ካህናቱ የትእዛዝ ደብዳቤ ተቀብሎ ክርስቲያኖ ችን እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት ይተጋ ነበር። ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ፥በእርሱ ዙሪያ በድንገት ከሰማይ ብርሃን አን ጸባረቀበትና ወደቀ።ከሰማይም፡-"ሳዉል፥ሳዉል ለምን ታሳድደኛለህ?" የሚል ድምፅ በመስማቱ፥ "ጌታ ሆይ፥አንተ ማን ነህ?"ሲል ጥያቄውን በጥያቄ መለሰ።እርሱም፡- "አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤የመውጊያውን ብረት ብትቃወም በአንተ ይብስብ ሃል፤"አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀም፡-"ጌታ ሆይ፥ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?" ብሎ እጅ ሰጠ፥ በድምፁ ተማረከ፥ በኃይሉ ተሸነፈ።ጌታም፡- "ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን እነርሱ ይነግሩሃል፤" አለው። በመንገድ የነበሩ ሰዎች፥ድምፁን እየሰሙ ማንነቱን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ሆኑ። ሳዉል ከወደቀበት ሲነሣ ማየት ስለተሳነው እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት። ሳያይም ሦስት ቀን ቆየ፥አልበላምም፥አልጠጣምም።                      

              ጌታ በደማስቆ፥ ሐናንያ ለሚባለው ደቀመዝሙር በራእይ ተገልጦ፡- ሳዉልን ፈልጐ እንዲያገኘው፥እርሱም በጸሎት ተጠምዶ ሳለ፥ ሐናንያ የሚባል ሰው እጁን ሲጭንበት እንደ አየ ነገረው።ሐናንያ ግን፡- "ጌታ ሆይ፥ይህ ሰው በኢየሩሳሌም በቅ ዱሳንህ (በክርስቲያኖች) ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ሰምቻለሁ፥ ስምህን የሚጠሩትን ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው፤" አለ። ጌታም፡- "ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲሚያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና፤" አለው። ሐናንያም፡- ሄዶ እጁን ከጫነበት በኋላ፥ "በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ያድርብህ  ዘንድ ላከኝ፤" አለው። ወዲ ያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀለትና አየ፥ተነሥቶም ተጠመቀ፥ መብልም በልቶ በረታ። ወደ ምኵራብም ገብቶ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መሰከረ። የሰሙትም የቀድሞ አሳዳጅነቱን እያስታወሱ በመለወጡ ተደነቁ።እርሱ ግን እየበረታ ሄደ። አይሁድ ሊገድሉት በፈለጉ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ በሌሊት ወስደው፥ በከተማው ግንብ ላይ በቅርጫት አወረ ዱት። ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ደግሞ ስላላመኑት ፈሩት።በዚህን ጊዜ በርናባስ፥ ወደ ሐዋርያት አስገባውና እንዴት ወደ ክርስትና እንደተመለሰና በኢየሱስም ስም ደፍሮ እንደሰበከ ተረከላቸው።በዚያም አይሁድን እየተከራከረ ስላስቸገራቸው ሊገድ ሉት ፈለጉ። ወንድሞች ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ከዚያም ወደ ጠርሴስ ወሰዱት። የሐዋ፡፱፥፩-፴።

              

            ሳዉል፡- "ጳውሎስ" የሚለውን ስም ያገኘው፥ ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለ ሀገረ ገዥ ነው። ይህ ሰው አስተዋይ ስለነ በረ፥ ሳዉልን እና በርናባስን ጠርቶ የወንጌልን ቃል ለመስማት ፈለገ። በቤቱ የሚኖር ኤልማስ የተባለ ጠንቋይ ግን ሀገረ ገዢ ውን ከማመን ለማጣመም ፈልጐ ተቃወማቸው።ሳዉል ግን አድሮበት በሚኖር መንፈስ ቅዱስ፡-"አንተ ተንኰል ሁሉ፥ ክፋ ትም ሁሉ የሞላብህ የዲያብሎስ ልጅ፥የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ (ወንጌልን) ከማጣመም አታርፍምን? እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፥ዕውርም ትሆናለህ፥ እስከጊዜውም ፀሐይን አታይም፤" አለው።ወዲያውም ታወረና የሚመ ራው ፈለገ። ሀገረ ገዢው የተደረገውን ተአምራት ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ አመነ። የጠንቋዩን ዓይነ ሥጋ በተአምራት ሲያጠፋበት፥ የእርሱን ደግሞ ኅሊናውን በትምህርት ሲያበራለት ተመልክቶ፥" ጳውሎስ (ብርሃን)" የሚለው ስም የሚገባው ለአንተ ነው " ብሎ ስሙን ሰጠው። የሐዋ፡፲፫፥፮-፲፪።ከሁሉም በላይ ጌታችን "ምርጥ ዕቃ" ብሎታል።"ምርጥ ዕቃ" የሚባ ለው ሰባቱን ማዕድናት ቀጥቅጦ አንድ የሚያደርገው መዶሻ ነው።እርሱም ሰባቱን መስተፃርራን (ጠላቶች፣ጠበኞች) ሰውና እግዚአብሔርን፥ ሰውና መላእክትን፥ ሕዝብንና አሕዛብን፥ ነፍስንና ሥጋን፥ አስታርቆ አንድ የሚያደርግ ነው። አንድም ምርጥ ዕቃ የሚባሉት ወርቅና ብር፥ለዕቃዎች ሁሉ ጌጥ እንደሆኑ፥ እርሱም የቤተክርስቲያን ጌጥ ነው። አንድም ጳውሎስ ማለት፡- አመስጋኝ፥ደስታ፥ ምዑዝ ነገር የሚናገር፥ ልሳነ ክርስቶስ፥ ሰላም ፍቅር ማለት ነው።           

              ሳዉል የተወለደው ጠርሴስ ከተማ ነው፤ የሐዋ፡፳፩፥፴፱።በዚያም ድንኳን መስፋትን ተምሯል፤ የሐዋ፡፲፰፥፫። የሮሜ ዜግነትን የወረሰው ከአባቱ ነው፤ የሐዋ፡፳፪፥፳፮። አባቱ ከብንያም ወገን የሆነ ፈሪሳዊ ነው፥ይህንንም፡- "በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤ ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ፥ ቤተክርስቲያን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ።" በማለት አስረድቷል። ፊል፡፫፥፭-፮። በፍርድ ሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም፡ -እኵሌቶቹ ሰዱቃውያን፥ እኵሌቶቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን አይቶ፥ "ወንድሞቼ ሆይ፥ እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና  ስለ ሙታን መነሣት ይፈርዱብኛል፤" ብሎ አሰምቶ ተናግሮአል። የሐዋ፡፳፫፥፮።                                                                   

           ሳዉል ሕገ ኦሪትን የተማረው ለከፍተኛ ትምህርት ኢየሩሳሌም ተልኰ ነው።የሙሴን ሕግና የአይሁድን ወግ፥ ከታላቁ መምህር ከገማልያል ተምሮአል። የሐዋ፡፳፪፥፫። የተማረውም ለ፲፭ ዓመታት ነው፥ በዚህም ምክንያት በ፴ ዓመቱ የአየሁድ ሸንጎ አካል ሆኖአል።በመሆኑም በቅዱስ እስጢፋኖስ መገደል እርሱም ተስማምቶ ነበር። የሐዋ፡፯፥፶፱። የወንጌል መምህር የሆነው ከዚህ ሕይወት ውስጥ ወጥቶ ነው። በኃይልና በሥልጣን የጠራውም ታሪኩን ከላይ እንዳየነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ጌታ ሲጠራው ገና የሠላሳ ዓመት ጐልማሳ ነበር።                                                         

           ቅዱስ ጳውሎስ፡-"ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ፤....... ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤" እያለ ወንጌልን በትጋት ሰብኳል። ሮሜ፡ ፩፥፲፬፣፩ኛ፡ቆሮ፡፱፥፲፮።ወንጌልን የሰበከው በብዙ መከራ፥በትህትና እና በፍጹም ትእግሥት ነው። ፩ኛ፡ቆሮ፡፬፥፲፬፤ ፪ኛ፡ቆሮ፡ ፲፩፥፳፪፤ ፲፭፥፭፣ኤፌ፡፫፥፰።ፋታ የማይሰጥ የራስ ምታትና የጎን ውጋ ትም ነበረበት።ከሕመሙ ጽናት የተነሣም ደዌውን ሰይጣን ብሎታል። ፪ኛ፡ቆሮ፡፲፪፥፮። ሐዋርያው፡- የደረሰበትን እጅግ ብዙ መከራና ሥቃይ ሳይሆን፥ የተጠራለትን፥ የተመረጠለትንና ከዓለም የተለየለትን አገልግሎቱን ብቻ ይመለከት ነበር። "የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብደኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው፤" ያለው ለዚህ ነው። ትምህርቱ በተአምራት ስለጸናለት ፥በሽተኞችን ይፈውስ ሙታንንም ያስነሣ ነበር። የሐዋ፡፲፬፥፰፤፳፥፱።                                    

           የቅዱስ ጳውሎስ አገልግሎት የተፈጸመው፥ እንደ ኤልያስ ነቢይ እና እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በድንግልና ሕይ ወት ነው። ፩ኛ፡ቆሮ፡፯፥፰። እስከ ሦስተኛው ሰማይ እየወጣም፥ በሰው አንደበት ሊነገር የማይገባውንና የማይነገረውን ቃል ይሰማ ነበር። ፪ኛ፡ቆሮ፡፲፪፥፬።ይህን ሁሉ ጸጋ ተሸክሞ ዓለም አልራራችለትም፤ ዓይኗን ጨፍና፥ጆሮዋን ደፍና፥ ልቧንም አደንድና ታገለችው። "እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለን፥ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለን፥እንንከራተታለን፥ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓ ለም ጥራጊ የሁሉም ጕድፍ ሆነናል። "ያለው ለዚህ ነው። ፩ኛ፡ቆሮ፡፬፥፲፩-፲፫።                                    

        በመጨረሻም፡- "በጉባኤም፥ በየቤታችሁም፥ አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አላስቀ ረሁባችሁም።.... በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤.... መንፈስ ቅዱስ፡-በዚያ እስራትና መከራ ይቆይሃል፥ ብሎ ኛል።.... ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንደማታዩ አውቃለሁ፤" ብሎ ምእመናንን ተሰናበታቸው።ጳጳሳትንም፡- "በገዛ ደሙ የዋጃ ትን የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።" ሲል መከራቸው። የሐዋ፡፳፥፲፱-፳፰። እያለቀሱ ስላስቸገሩትም፡- "እያለቀሳችሁ ልቤንም እየሰበ ራችሁ ምን ማድረጋችሁ ነው?እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት እንኳ ተሰናድቻለሁ እንጂ ለእስራት ብቻ አይደለም።" አላቸው። የሐዋ፡፳፩፥፲፫። ቅዱስ ጳውሎስ ጸሐፊ ስለነበር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ፲፬ መልእክ ታትንም ጽፏል።                                                                                                                 

            የቅዱስ ጳውሎስ አካላዊ ቁመናው፡-ጭንቅላቱ ተለቅ ያለ ሆኖ ራሰ በራ ነው፥የቅንድቦቹ ጠጉር የተጋጠሙ ናቸው፥ የዓይኖቹ ቀለም ሰማያዊ ሆኖ ብሩሃን ናቸው፥ አፍንጫው ትልቅና ቀጥ ብሎ የወረደ ነው፥ ጽሕሙና ሪዙ ረጃጅም ናቸው፥ አንገቱ አጠር ያለ ሆኖ ትከሻው ክብና ጐባባ ነው፥ ቁመቱ አጠር ያለና ደንዳና ሰው ነበር።ይህ ሐዋርያ፡- ወንጌልን ለማዳረስ፥ በ፵፮ዓ.. በ፶ዓ.. እና በ፶፬ዓ.. ሦስት ታላላቅ ጉዞዎችን አድርጓል። በተለይም በመጀመሪያው ጉዞ ከ፪ሺ .. በላይ በእግሩ ተጉዟል።                                                                                                        

              ጊዜው ሲደርስ፥ በትምህርቱ የተበሳጩ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ፥ ሐዋርያውን ኢየሩሳሌም ሲያገኙት ተቃውሞ አስነሥተውበት አሳሰሩት። የሐዋ፡፳፪፥፳፱። ከብዙ መከራና ሥቃይ በኋላ ታሥሮ ሮም ገባ፥ የቁም እሥረኛ ሆኖ ለሁለት ዓመታት ወንጌልን ሰበከ። ከዚያም ኔሮን ፍርድ ቤት ቀርቦ በነፃ ተለቀቀ።ከዚህ በኋላ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያልተመዘገበውን አራተኛውን ጉዞ ለአራት ዓመታት አደረገ። በ፷፬ዓ.. ኔሮን ቄሣር፡- "ሮምን ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ፤"ብሎ ካቃጠላት በኋላ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በሮም መቃጠል የተበሳጨውም ሕዝብ አያሌ ክርስቲያኖችን ጨፈ ጨፈ። ቅዱስ ጳውሎስም ከሚያስተምርበት ከኒቆጵልዮን ከተማ ተይዞ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ከታሠረ በኋላ ሐምሌ ቀን ፷፯ .. በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ፥አንገቱን ተሠይፎ በሰማዕትነት ዐረፈ። በረከቱ ይደርብን፥ በአማላጅነቱም አይለየን፥አሜን።

     

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ቅዱስ ጳውሎስ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top