የመንፈስ ፍሬዎች (8ኛ የውሃት)በመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሣኤየውሃት ራስን ዝቅ ማድረግ አለመመካት እሺ ባይነት ከራስ ይልቅ ለባለንጀራ ማሰብ ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ የውሃት የመንፈስ ፍሬ ነው፡፡ ጌታችን ስለተባረኩ ከተናገረው ዓረፍተ ነገር ግንባር ቀደም መሆኑን ሲገልጽልን "የዋሆች ብፁዓን ናቸው ምድርን ይወርሳሉና"ሲል አስተምሮአል ማቴ. 5፡23፡፡አንዳንድ ቅዱሳን አባቶች በየዋህነት በመኖር አገልግለው አሳልፈዋል፡፡ የውሃት ወይም ደግነት ጌታ ከእርሱ እንማረው ዘንድ የጠየቀን እጅግ ጠቃሚ ምግባር ነው፡፡ ማቴ.11፡29"ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና"፡፡ከእርሱ ስብከትን፣ ተአምራትን፣ መምህርነትን፣ ትህትናን፣ ፍቅርን፣ አገልግሎትን፣ ምህረትን፣ ጥበብን እና ሌሎች ምግባራትን እና ፍጹምነትን ሁሉ እንድንማር ጠይቆናል፡፡ ፍጹምነትን እና ምግባርን ሁሉ ይወክላልና ነገር ግን በየውሃት እና ቸርነት ላይትኩረት ያደርጋል፡፡ ይህንን ለሚማሩትም ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁ ብሏቸዋል፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ኤፌ.4፡11"እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግስትም እርስ በራሳችሁ በፍቅር ታገሡ"ገላ.6፡1"ወንድሞች ሆይ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ"፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው?በመልካም አነዋወሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ ያዕ.3፡13 እንዲህ ያለ የዋህነት ከመራራ ምቀኝነት ለራስ ከመፈለግ ግራ ከመጋባት እና ከማንኛውም ክፉ ነገር እንዴት የነጻ እንደሆነ አስረድቶአል፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ ስለከበረው የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ውበት ተናግሮአል፡፡ 1ጴጥ.3፡4"በእናንተ ሰለላ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን"የዋህነት ክርስቲያኖች የሚለዩበት ጠባይ ነውና፡፡ከቸርነት ወይም ከየዋህነት ጥቅም የተነሣ መጽሐፍ ቅዱስ ገር እና የዋህ የሆነ ሰውን ያመሰግናል ሁለቱም ምግባራት እርስ በርሳቸው ግንኙነት አላቸውና፡፡ መዝሙረኛው ገሮችም ሰምተው ደስ ይላቸዋል፡፡ መዝ. 34፡2 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉበብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል መዝ. 36፡11፡፡እግዚአብሔር የዋህን ያነሳል ኃጢአተኞችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል መዝ.146፡6፡፡የየዋህ ሰው ጠባይስለ የዋህነት እና ስለየዋህ ይህን ሁሉ ካወቅን የዋህነት ምንድን ነው? የዋህ ወይም የገር ሰው ባህርያት ምንድን ናቸው? የሚሉትን እንመልከት፡-የዋህ ሰው መልካም ጠባይ ያለው እና ሰላማዊ ሰው ነው፡፡ እርሱ ሁል ጊዜ በነገሮች ሁሉ የተረጋጋ ነው፡፡ በጠባዩ የረጋ ነውንግግሩ ስሜቶቹ እንዲሁም አጠቃላይ እንቅስቃሴው ሰላማዊ ነው፡፡ ወጪያዊ ገጽታው ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ እሱነቱም እርጋታ የተሞላበት ነው፡፡ ልቡና ስሜቶቹ የረጉ ናቸው፡፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚያደርጋቸው ውይይቶች እና ንግግሮች የረጋ ነው፡፡ ዳግመኛም ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበር ዘኀ.12፡3 ተብሎ እንደተገለጸው እንደ ነቢዩ ሙሴ ትሑት ነው፡፡የየዋህ ሰው ድምፅ ሁል ጊዜ የዋህ ነውድምጹ ፈጽሞ ከፍተኛና ኃይለኛ አይደለም ንግግሮቹ ጐጂም፣ አስቸጋሪም አይደሉም የረጋ እና አነስተኛ ድምጽ የየዋህ ሰው ጠባይነው፡፡ይህም የየዋሁ ጌታችን ድምጽ የሚመስል ነው፡፡ እግዚአብሔር ነብዩ ኤልያስን ከአጭበርባሪዋ ከንግስት ኤልዛቤል ሲሸሽ ባገኘው ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ነፈሰ እግዚአብሔር ግን በነፍሱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ከነፍሱም በኋላ በምድር መናወጥ ሆነ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም፡፡ ከምድር መናወጥ በኋላም እሳት ሆነ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ ድምፁም ኤልያስ ሆይ በዚህ ምን ታደርጋለህ? የሚል የእግዚአብሔር ድምፅ ነበር 1ኛ.ነገ.19፡11፡፡ጌታ ክርስቶስም በየዋህነቱ አይከራከርም አይጮህምም ድምጹንም በአደባባይ የሚሰማ የለም.....የተቀጠቀጠን ሸንበቆ አይሰብርምየሚጤስንም የጥዋፍ ክርም አያጠፋም ማቴ. 12፡19፡፡የየዋህ ሰው ችሎታ ምንድን ነው?የየዋህ ሰው ችሎታዎች ተብለው የሚገለጹ አሉ የዋህ ሰው ሁከት አይፈጥርም አይከራከርም አይጮህምም ድምፅንም በአደባባይ አይሰማም፡፡ ንግግሮቹ እርካታ ያላቸውና ጣፋጭ ናቸው፡፡ቃላቱ እጅግ ትሑት እና ጥሩ መሆናቸው የተረጋገጠ ነው፡፡ የአንድ ሰው ጠባይ ምንም ይሁን ምን የማንንም ስሜቶች ፍጹም አይጎዳም ይህን ሁሉ የሚያደርገው ደካማ ከመሆኑ የተነሣ ሳይሆን ከየዋህነቱ የተነሣ ነው፡፡እስቲ ትንሽ ስለጠባዩ እንመልከት፡-የዋህ በስሜቱ ኃይልና ቁጣ የለበትምየዋህ ራሱን እንደታዛቢ አድርጎ በሌሎች ላይ አያስቀምጥምየዋህ እና ቅን ሰው ልቡ ሰፊ እና ትዕግስተኛ ነውየዋህ ሰው ሁል ጊዜ ደስተኛ ነውየዋህ ሁል ጊዜ ለቁጣ የዘገየ ነውየዋህ ሰው በየምክንያቱ አይናደድምሁለት አይነት የዋህነት አለ1.የዋህ ሆኖ የሚወለድ ገና ከልጅነቱ የሚጀምር ነው2.በትምህርት፣ በትግል በመልካም ሥራውና በውስጡ ባለ ጸጋ የዋህ የሚሆን ሰው ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ "እያንዳንዱ ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ" ፊል. 2፡3 ተመልከት፡፡ይህ ሁኔታ በአብርሃምና በሎጥ መካከል ተፈጽሞአል ዘፍ. 13፡5 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዋህ መሆኑን ሐዋርያታት ከማስተማራቸው ሌላ ራሱም ገልጾታል እንዲያውም የዋህነትን በተግባር በስቅለቱ ወቅት በግልጽ አሳይቶአል፡፡የዋሆች ስንሆን1.እግዚአብሔር ጸሎታችንን አይንቅም መዝ. 50፡172.ብንበደል እግዚአብሔር ይፈርድልናል መዝ. 25፡13.አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርን እንወርሳለን ማቴ. 5፡5የቀደምት ቅዱሳን ይህንን ሁሉ ያገኙት በሰው ሁሉ ፊት የዋሃን ሆነው በመመላለሳቸው ነው 1ተሰ.2፡7፣ 1ቆሮ.10፡ 1 ፣ ቲቶ. 3፡1 እኛም ዛሬ ምናልባት አንድ ሰው በማናቸውም በደል ቢገኝ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ ልናቀናው ይገባል፡፡ ገላ.6፡1፡፡ ክርስትና ሳይገባው ብዙ የሕይወት ጥያቄዎች ቢኖሩት ወይም ልቡን አጠንክሮ ቢከረከርም በቂ መልስ የምንሰጠው በየዋህነት ሊሆን ይገባል፡፡ 1ጴጥ. 3፡15 "በእናንተ ስለላ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን ይለናል"፡፡ በየዋህነት ፀጋ ሕይወታችን ይባረክ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Monday, 19 October 2015
- የተሰጡ አስተያየቶች
- በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
0 comments:
Post a Comment