• በቅርብ የተጻፉ

    Monday, 19 October 2015

    የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ዘጠኝ

    የመንፈስ ፍሬዎች 9ኛ (ራስን መግዛት)በመጋቤ ሐዲስ መኰንን ወ/ትንሣኤበመንፈስ የሚኖር ሁሉ የመንፈሳዊ ሕይወት ፍሬ የሆነው ራስን መግዛት ይኖረዋል፡፡ ታዲያ ራስን መግዛት ምንድን ነው? ከውስጣችን ሊወጣ የሚታገለንን ማናቸውንም የስጋ ፍላጎትና ምኞትን መቆጣጠርና መግዛት ራስን መግዛት ይባላል፡፡ ለቁጣ፣ ለቂምለበቀል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለስካር ወዘተ... በውስጣችን የሚሰማንን ግፊት በእግዚአብሔር ቃልና በመንፈስ ቅዱስ ሆነን ልንቆጣጠር ያስፈልገናል፡፡ራሳችንን ለመግዛት የምንችለው እንዴት ነው?1.ለበጎ እንኳን ዝም እስከማለት ድረስ የሌላውን ቁጣ በትዕግስት በማሳለፍያዕ.1፡19 ፤ 2ሳሙ. 16፡5 ፤ መዝ. 38፡12.በጾምና በጸሎት ስጋችንን በመስገዛትመዝ. 108፡24 ፤ ሉቃ. 2፡37 ፤ 2ቆሮ. 6፡63.በአርምሞና ራስን ለተወሰነ ጊዜ ከሰዎች በመሰወርሉቃ. 1፣25 ፤ ገላ. 1፡15ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጴላጦስና በሄሮድስ ፊት ተከሶ በቀረበ ጊዜ ያ ሁሉ የሐሰት ክስና ስድብ ሲደርስበት በዝምታ ማየቱ ራስን መግዛት እንዴት እንደሆነ ለማስረዳትና ለማስተማር ነው፡፡ ሉቃ. 23፡1ቅዱስ ጳውሎስ በፊልክስ ፊት ተከሶ በቀረበ ጊዜ ራስን ስለመግዛት ተናግሮአል፡፡ ሐዋ. 24፡25 . . .በ1ቆሮ. 9፡27 ላይ ሌሎችን ከሰበክሁ በኃላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጐሰምሁ አስገዛዋለሁ በማለት ራሱንእንደሚገዛ ገልጿል፡፡ በዚህ መሠረት ክርስቲያን ይልቁንም አገልጋዮች ዝግተኛ ሆነው ራስን መግዛት መልካም ሕይወትን መምራት እንደሆነ እንድናውቅ አስተምሮአል 1ጴጥ. 1፡6 ፤ 1ጢሞ. 3፡24.የአንደበት ንጽሕና፡- ከማንኛውም መጥፎና ከንቱ ቃል ከመናገር ራስን መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ጌታ "ሰዎች ስለሚናገሩት ስለከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል" ማቴ. 12፡36ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው ማቴ. 15፡11በእርግጥ ንጹሕ ሰው በምንም ቃል አይረክስም ንጹሕ አንደበት የስድብ ወይም የፌዝ ቃል አይስማማውምንጹሕ ሰው ሌሎችን ያከብራል ማንንም በጐጂ ቃል ወይም የንቀት በሆነ በሚያዋርድ ወይም በፌዝ ቃል አይጎዳም፡፡ንጹሕ አንደበት ትሁት፣ ሰው አክባሪ፣ ከመናገሩ በፊት እያንዳንዱን ቃል የሚመዝን የተከበረ አንደበት በመሆኑ በምንም ምክንያት የማንንም ስም አያጠፋም ወይም አያስደነግጥም፡፡ከዚህ በተጨማሪ ተፈጥሮ በመሆኑ ንጹሕ ቃልን ይጠቀማል እንጂ ለመናገር ምንም ዓይነት ጥረት ሳያደርግ ይናገራል፡፡5.የጽሑፍ ንጽሕና የአንደበት መገለጫ ይሆናል፡- መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ሰው ከላይ የተገለጹትን ነገሮች ሁሉ በጽሑፍ ሥራው ላይም ትኩረት ይሰጣል ማለት ነው፡፡ የማንንም ሰው ስም ለማጥፋት አይዘጋጅም ሰው የሚያስቀይም የሐሰት ውንጀላአያቀርብም ለሰው ክብር መጠንቀቅ እንደሚገባው ያውቃልና በጽሑፍ ውስጥ ከመልካምና ሰውን ከሚያስተምር መልዕክት ውጪ ሰውን በማዋረድ የሚያገኘው ትርፍ አይኖረውም ዛሬ ግን ይህ አሠራር በብዙዎች መካከል ጐልቶ እንደሚታይ ይታመናል፡፡ አንዳድ ሰዎች ስም ማጥፋትን ሥራቸው አድርገው ይዞውታል ኃጢአት መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ "በሐሰት የሰውን ስም ከማጥፋት አምላክ ይጠብቀን" እጅግ ትልቅ ኃጢአት ነውና፡፡6.የአንደበት ኃጢአት ራሱ ኃጢአት መሆኑን ያውቃል፡- ንጹሕ ያልሆነ አንደበት ኃጢአት ይህን የሚያስከትለው የሌላ ኃጢአት ውጤት ነው እርሱም የልብ ንጹሕ አለመሆን ጌታ "መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል" ሉቃ. 6፡457.የሥጋ ንጽሕናን ገንዘብ በማድረግ፡- የሥጋ ንጽሕና ሥጋን መጥፎ ከሆነ ሥጋዊ ደስታ እና ከዚህ ዓለም ጋር ግንኙነት ካላቸው ደስታዎች መለየትን ያጠቃልላል፡፡ "ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ .... በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት" 1ዮሐ. 2፡15 ሲል በመልዕክቱ ተናግሮአል፡፡ንጹሕ ልብ ለአካል ንጽሕናም መሠረት ነው፤ የአካል ንጽሕና በትሕትና የታጀበ ነው፡፡1ጴጥ. 3፡4 "በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለው ነው፡፡"የአረማመድ ወይም የአነጋገር ዘይቤ ንጽሕናን የሚጻረር ይሆናል፡፡ቅዱስ ጳውሎስ "እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንንም ደስ እንዳናሰኝ ይገባናል"፡፡ ሮሜ. 15፡1የራሳችንን ንጽሕና እንድንጠብቅ ብቻ ሳይሆን በእኛ ምክንያት ንጽሕናቸውን እንዲያጡ ለሌሎችም ንጽሕና እንድንጠነቀቅ ጭምር ተጠይቀናል፡፡ይህን በተመለከተ ጌታ "መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይለቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይቀላል" ማቴ. 18፡78.የማየት ንጽሕና፡- የማየት ንጽሕና ማንኛውንም ምኞታዊ እይታ በማስወገድ እውን ይሆናል፡፡ ምን አልባት ይህ ቅዱስ ዮሐንስ "የዓይን አምሮት" 1ዮሐ.2፡16 በሚል የገለጸውና ጻድቁ ኢዮብ "ከዓይኔ ጋር ቃልኪዳን ገባሁ እንግዲህስ ቆንጆይቱን እንዴት እመለከታለሁ፡፡" ኢዮ. 31፡1 በሚል ቃል የገለጸው ዓይነት ነው፡፡ጌታ ራሱ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያንጊዜ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሯል፡፡ ማቴ. 5፡28የልብ ንጹሕ አለመሆን የዓይን ንጹሕ አለመሆንን ያስከትላል በማንኛውም ሴት ላይ የንጹሕ ሰው እይታ ንጽሕ ነው እይታው ኃጢአታማ የሚሆነው ልቡ ሲረክስ ነው፡፡ ይህ በጴጥፋራ ሚስት ላይ ተከስቷል እርሷ "በዮሴፍ ላይ ዓይኗን ጣለች" ዘፍ. 39፡7 ያለምንም ጥርጥር የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍን ሁል ጊዜ ታየዋለች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን በተለየ ዓይን በምኞት በተሞላ ልብ በዓይኗ ትመለከተው ጀመር፡፡ /በሥጋ ፈቃድ ማለት ነው፡፡/መልካሙንና ክፉን የምታሳውቀውን ዛፍ በተመለከተ በእናታችን በሔዋን ላይም እንዲሁ ተከስቷል፡፡ ያ ዛፍ በገነት መካከል ነበርዘፍ. 3፡3 ሔዋንም በአጠገቡ ሁል ጊዜ ትመላለስ ነበር ታየውም ነበር ነገር ግን ምኞት የሌለበት በንጽህ ልብ ነበር ታዲያ ችግሩ መቼ ተጀመረ? እባብ ለሔዋን ሞትን አትሞቱም... ዓይናችሁ ይከፈታል እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ ዘፍ. 3፡4 ባላት ጊዜ በእባቡ ፈተና የሴቲቱ ልብ ሊለወጥ ተጀመረ ሴቲቱም በዚህ ጊዜ ዛፉ ለመብላት ያማረ ... ለዓይንም እንደሚያስጐመጅ.... ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች ዘፍ. 3፡6 ዛፉን ምኞት ባለበት ክፉ እይታ መመልከት ከየት መጣ? ከልብ የውስጥ ንጽህና መለወጥ የመጣ አይደለምን?የንጹሕ ሰው እይታ በምኞት የተሞላ ሳይሆን ዓይን አፋር ነው፡፡9.የጀሮ ንጽሕና፡- ንጹሕ ጆሮ የሰው ወሬ በድብቅ የሚሰማ አይደለም፡፡ የሰው ወሬ በድብቅ የሚሰማ ጀሮ ያውቀው ዘንድ መብት የሌለውን ምሥጢር ለማወቅ ይሞክራል፡፡ የሌሎች ሰዎችን ግላዊ ጉዳዮች የሚሰርቅ እንዲህ ዓይነት ሰው መልካም ጠባይ ያለው አይደለም፡፡ አንዳንድ ጆሮዎች ሐሜት ወይም ስለጠላቶቻቸው ውድቀት የሚወራ ወሬ በመስማት ደስታ ያገኛሉ፡፡ ይህ ንጽሕናን የሚቃረን የደስታ አይነት ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህሐሴት አያድርግ እግዚአብሔር ያንን አይቶ በዓይኑ ክፉ እንዳይሆን" ምሳ. 24፡1710.የእጁ ንጽሕና፡- ንጹሕ እጅ በመስረቅም ይሁን ከኪስ በማውጣት ወይም በጉልበት በመጠቀም በመቀማት፣ በማስገደድ የሌላውን ሰውነት በመደብደብ በእጁና በጉልበቱ አይመካም፡፡ሌላው በሕገ ወጥ መንገድ በተገኘ ልዩ ትርፍ የሚደሰት እጅ በእርግጠኝነት ንጹሕ አይደለም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "ገንዘብ የሚወድ" 1ጢሞ. 3፡3 ተብሎ ተገልጿል፡፡ይህም አረጣ አበዳሪ በድሆች ላይ የሚጥለውን አራጣ ማበደርን በገበያ ውስጥ የተወሰኑ የፍጆታ እቃዎችን መቆጣጠርን፣ ገዢዎችንሊጎዳ የሚችል ከፍተኛ ዋጋ መጨመርን ለባሰ ቀን ብሎ መደበቅን ያጠቃልላል፡፡ በእንደነዚህ ዓይነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች እጆች በድሆች የድካም ፍሬ የተሞሉ ናቸው፡፡ንጹሕ እጅ የልብ ንጽሕናን ይጠይቃል ንጹሕ እጅ ያለው ሰው ለመጠየቅ በጣም ጠንቃቃ ነው ከተሰጠውም ለመቀበል ዓይን አፋር ነው እስቲ የጠፋው ልጅ ታሪክን እንመልከት ሉቃ. 15፡1 ከተመለሰ በኋላ ምን ዓይነት ጠባይ ነበረው?በምን ዓይነት ትሕትና የተሞላ እንደሆነ ከታሪኩ በሚገባ መማር እንችላለን፡፡ማጠቃለያ፤በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ማንኛውም ክርስቲያን ሊኖረው የሚገባ ነገር ቢኖር ይህ የመንፈስ ፍሬ ነው፡፡ ይህ የመንፈስ ፍሬየሌለው ሰው ምን ዓይነት መንፈስ እንዳለው ራሱን ሊመረምር ይገባል፡፡ ሉቃ. 9፡52ይህን የመንፈስ ፍሬ ማፍራት የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ብቻ ነው፡፡ አንድ የብርቱካን ፍሬ ማፍራት የሚፈልግ ሰው የብርቱካን ዘር መዝራት አለበት እንጂ የቲማቲም ዘር ቢዘራ የብርቱካን ፍሬ ቢጠብቅ አያገኝም፡፡ስለዚህ የመንፈስን ፍሬ ለማፍራት መንፈስ ቅዱስ ራሱ በሕይወታችን ሊገባና ሊያዘን ያስፈልገዋል አለበለዚያ ግን በሥጋችን ይህንን ፍሬ እናፍራ ብለን ብንታገል እንኳ ሥጋ የራሷ ዘር /ፍሬ/ ይህ ስላልሆነ ልናፈራ አንችልም፡፡ ገላ. 5፡16-23የዚህ ፍሬ አመራረት ለውበትና ለእይታ ማራኪነት ተብሎ ሳይሆን አፍርቶ እንዲበላ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የፍቅር፣ የደስታ፣ የሰላም እጦት ችግር የመንፈስ ጸጋዎች ረሀብተኞች ናቸው፡፡ መልካም ፍሬ በኛ ላይ የሚያዩ ሰዎች በሕይወታቸው የጎደላቸውን ከእኛ ያያሉ ማለት ነው፡፡እኛ ፍሬ የምናፈራው እኛው እንድንጠቀምበት ብቻ ሳይሆን ሌሎች እንዲመገቡትና እርዳታ እንዲያገኙበት ጭምር ነው፡፡በአጭሩ ለዚህ ሁሉ ምስጢሩ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ከኃጢአትና ከክፋት ነጻ መውጣት የሚያስችለውን በረከት፣ እውቀት ጸጋ ሊሰጠን የሚችል እርሱ ብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት የፍቅርን ሕግ እንድንፈጽም ሥጋን እንድናሸንፍና ፍሬ እንድናፈራያስችለናል፡፡ታዲያ ራሳችንን ለእርሱ በመስጠት መልካም ፍሬ እንድናፈራ ሁለንተናችንን ለመስጠት ምን ያህል ዝግጁ ነን?የዘርና የመልካም ፍሬ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር በመንፈስ ፍሬዎች ሕይወታችንን ለመምራት እንድንችል ይርዳን፡፡ወስብሐት ለእግዚአብሔር

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ዘጠኝ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top