• በቅርብ የተጻፉ

    Sunday, 18 October 2015

    መስቀል

      ከጌታችንና  ከአምላካችን  ከመድኃኒታችን  ከኢየሱስ  ክርስቶስ  በፊት  መስቀል  የመቅጫ  መሣሪያ  ነበር።  ሰውን  በመስቀል  ላይ  መቅጣት  የተጀመረውም  በፋርስ  ነው።  ፋርስ  የዛሬዋ  ኢራን  ናት።  የፋርስ  ሰዎች “ ኦርሙዝድ ”  የተባለ “ የመሬት  አምላክ ”  ያመልኩ  ነበር።  ከዚህም  የተነሣ “ ወንጀለኛው  ቅጣቱን  በመሬት  ላይ  የተቀበለ  እንደሆነ  አምላካችን  ይረክሳል፤ ”  ብለው  ስለሚያምኑ  ወንጀለኛውን  ከመሬት  ከፍ  አድርገው  በመስቀል  ላይ  ይቀጡት  ነበር።  ይህም  ቅጣት  ቀስ  በቀስ  በሮማ  ግዛት  ሁሉ  የተለመደ  ሕግ  ሆነ።  ከዚህም  ሌላ  በኦሪቱ  ሥርዓት  ቅጣታቸውን  በመስቀል  ላይ  የሚቀበሉ  ሰዎች  ርጉማንና  ውጉዛን  ነበሩ። 

    ይህንንም  እግዚአብሔር  ለሙሴ “ ማንም  ሰውለሞት  የሚያበቃውን  ኃጢአት  ቢሠራ  እንዲሞትም  ቢፈረድበት ፥ በእንጨትም  ላይ  ብትሰቅለው፥  በእንጨት  ላይ  የተሰቀለ  በእግዚአብሔር  ዘንድ  የተረገመነውና  ሬሳው  በእንጨት  ላይ  አይደር፤ ”  ሲል  ነግሮታል። / ዘዳ .  ፳፩፥፳፪ - ፳፫ / ። 

    ከጌታችንና  ከአምላካችን  ከመድኃኒታችን  ከኢየሱስ  ክርስቶስ  በፊት  መስቀል  የመቅጫ  መሣሪያ  ነበር።  ሰውን  በመስቀል  ላይ  መቅጣት  የተጀመረውም  በፋርስ  ነው።  ፋርስ  የዛሬዋ  ኢራን  ናት።  የፋርስ  ሰዎች “ ኦርሙዝድ ”  የተባለ “ የመሬት  አምላክ ”  ያመልኩ  ነበር።  ከዚህም  የተነሣ “ ወንጀለኛው  ቅጣቱን  በመሬት  ላይ  የተቀበለ  እንደሆነ  አምላካችን  ይረክሳል፤ ”  ብለው  ስለሚያምኑ  ወንጀለኛውን  ከመሬት  ከፍ  አድርገው  በመስቀል  ላይ  ይቀጡት  ነበር።  ይህም  ቅጣት  ቀስ  በቀስ  በሮማ  ግዛት  ሁሉ  የተለመደ  ሕግ  ሆነ።  ከዚህም  ሌላ  በኦሪቱ  ሥርዓት  ቅጣታቸውን  በመስቀል  ላይ  የሚቀበሉ  ሰዎች  ርጉማንና  ውጉዛን  ነበሩ።  ይህንንም  እግዚአብሔር  ለሙሴ “ ማንም  ሰውለሞት  የሚያበቃውን  ኃጢአት  ቢሠራ  እንዲሞትም  ቢፈረድበት ፥ በእንጨትም  ላይ  ብትሰቅለው፥  በእንጨት  ላይ  የተሰቀለ  በእግዚአብሔር  ዘንድ  የተረገመነውና  ሬሳው  በእንጨት  ላይ  አይደር፤ ”  ሲል  ነግሮታል። / ዘዳ .  ፳፩፥፳፪ - ፳፫ / ። 

    የውርደት  ምልከት  የነበረው  መስቀል  የድል  አርማ  ሆኗል  ።  እንዴት  ቢሉ -  ፡  መድኃኒታችን  በመስቀል  ላይ  ባፈሰሰው  ደሙ  ሰላምን  ስላደረገ ( ቆላ 1 ፣ 20)  መድኃኒታችን  እኛን  ለማዳን የውርደት  ሞት  ያውም  በመስቀል  ላይ  ሞቶ  ሞትን  ድል  የነሳበት  የድል  አደባባይ  ስለሆነ ( ፊሊ 4 ፣ 18)  ነው።  ስለ ዕፀ  መስቀል  በተጨማሪ ( ማቴ 27 ፣ 32 ፣ዮሐ 19 ፣ 21) ይመልከቱ። 

    መስቀሉን  የምናከብረው  ኢየሱስ  ክርቶስ  ሊቀካህናተ  ሆኖ  ያገለገለበተ  መቅደስ፣  በግ  ሆኖ ሰለእኛ  እራሱን  ለአንዴና  ለመጨረሻ  ጊዜ  የሰዋበት  ምስዋዕ ( መንበር )  የጽድቅ  ማዕከል  ሰማያዊ  ሊቀካህናት  የክህነት  አገለግሎተ  ያጠቃለለበት  ደብተራ  መስቀል  ሰለሆነ  ደሙ  ሰለፈሰሰበት  መርገማችን  ሰለተሻረበት  እንደሆነ  አሰተውል። ቅዱሰ  አትናቴዎስ " በምደር  ላይ  ኃጢአትን  አሳፈረ፣በሲዖል  ሞትን  አሸነፈ  በመሰቀል  ሳለ  መረገምን  ሻረ፣  በመቃብረ  ውስጥ  ፈርሳ  በስብሶ  መቅረትን  አሰቀረ "  ብሎ  እንደተናገረ። 

    ስለዚህ  መስቀለ  ክርሰቶስ  ዲያብሎስን  ድል  የነሳበተ  መሳሪያ፣  ጠላታችን  የሞተበት  መሳሪያና  የድላችን  ምለክት  ነው።  መስቀል  እነዴት  ኃይል  ያደረጋል  ቢባል  ምላሰሹ  የሙሴ  በትር  ቀይ  ባሕርን  ከከፈለ ( ዘዳ 14 ፣ 20) ፣  የኤልያስ  መጠምጠሚያ  ዮርዳኖስን  ከከፈለ (2 ኛ  ነገ 2 ፣ 19) ፣ የቅዱስ  ጳውሎስ  ጨርቅ  ጋኔን  ካወጣ ( የሐዋ 19 ፣ 11-20) ፣ የጌታችን  ቀሚስ  ደም  ካቆመ  ደሙ  የፈሰሰበተ  መስቀል  ዕወር  ቢያበራ  ሙት  ቢያስነሳ  ለእግዚአብሔር  የሚሳነው  ነገር  እንደሌለውና  በሁሉ  የሚሠራ  አምለክ  አንደ  መሆኑን  ያስረዳናል። 

    ነገር  መስቀል  ሲዘከር  መስቀል  የሚለው  ቃለ  ሲነገርም  ሆነ  ሲሰማ  በክርሰቲያኖች  ልብ  ውስጥ  ልዩ  መንፈስ  ይፈጥራል።  መስቀል  በእርሱ  ላይ  የተሰቀለውን  እግዚአ - ኃይላት  ክርሰቶስን  ያሳሰባልና  የእሾህ  አክሊል  ደፈቶ  ጎኑ  በጦር  ተወግቶ  በብዙ  መከራና  ስቃይ  በቀራንዮ  የዋለውንም  ጌታ  በውስጣችን  ይስላልና።  የሲዖል  መሠረት  የተናወጠበት፣ሰውና  እግዚአብሔር  ለዘመናት  ለያይቶአቸው  የነበረው  የጠብ  ግድግዳ  የተናደበት  ሞት  ድል  የሆነበት  የትንሣኤ  መንገድ  የተከፈተበት  ልዩ  ምንፈሳዎ  መሣሪያ  መስቀል  ነው።  ስለዚህ  መስቀል  ለምዕመናን  የነፃነታቸው፣ የዕርቃቸውና  የሰላመቸው  ምልክት  በመሆኑ  ለመስቀል  ልዩ  ክብርን  ይሰጣሉ፣ይሰግዱለታልም። ማ  ንኛውንም  ተግባር፣ጸሎተን  ምግብን፣ጉዞን  ከመጀመር  በፊትና  ከጨረሱ  በኃላ  በትእምርተ  መስቀል  ያማትባሉ።  በፈተና  ፣በሐዘንና  ከፉ  ሐሳብ  በሕሊናቸው  በተፈጠረ  ጊዜ  ሁሉ  ያማትባሉ።  በከበረ  ደሙ  መስቀሉን  የቀደሰ  ጌታቸው  በኃይለ  መሰቀሉ  ሁሉን  ሊያደርግላቸው  እነደሚችል  በመታመን  ይህን  ያደረጋሉ። 

    እግዚአብሔር  አምላክ  ዓለምን  ከፈጠረበት  ጥበቡ  በሚበልጥ  ጥበብ  ዓለምን  ሁሉ  ያዳነበት  ከጥበብ ሁሉ  በላይ  የሆነ  ጥበብ  ይህ  ቅዱስ  መስቀል  ነው።  ለዚህም  ነው  ሊቃውንተ  ቤተክርስቲያን " መስቀል  መልዕልተ  ኩሉ  ነገር "  መስቀል  ከሁሉ  ነገርበላይ  ነው  ያሉት።  ይህ  የመስቀሉ  ነገር  አምላክ  ሰው  እስከ  መሆንና  እስከ  መሪር  ሞት  ያደረሰውን  ለሰው  ልጅ  ያለውን  ፍቅር  ከማነከር  በስተቀር  ለመረመርና  ድረሰ - ነገሩ  ሊስተዋል  የማይቻል  ረቅቅ  ነው።በመሆኑም  ነገር  መስቀሉ  ለአንዳንዶች  ፈተና  ለሌሎችም  ስንፍና  ሆኖባቸዋል።  ለሚያሚኑ  ምዕመናን  ግን  ከፈተናእነደ  ወርቅ  ነጥረው  የሚወጡበት ነው። 

    መስቀል  ህይወትን  ሊያጠፉ  በተነሱ  ጠላቶች  ቢዘጋጅም  ቅሉ  በእርሱ  አዲስ  ዘላዓለማዊ  ህይወት  ተዘጋጀቷል።  በእውነት  ጣለቶች  እውነትን  ለማጥፋት  ቢዘጋጁም  በእርሱ  ለዓለም  እውነት  ተሰብኳል።  አይሁድ  ሰዎችንና  ክርስቶስን  ለማራራቅ  የምዕመናንን  ራስ  ክርስቶስን  በመስቀል  ቢሰቅሉትም  በመስቀል  ያፈሰሰው  ክቡር  የሚሆን  ደሙ  ዓለሙን  ሁል  ወደ  እርሱ  አቅረቧል። " እምከም  ተለዓልኩ.... ጊዜ  ሁሉን  ወደ  እኔ  አስባለሁ "  በማለት  ጌታችን  ራሱ  እነደገለጸው  በመስቀል  የሰውን  ልጅ  ወደ  ራሱ  አቅርቦታል። በተመሳሳይ  መንፈስ " ዘበመስቀልከ  አቅረብከን  ኀበ  አቡከ  በመሰቀልህ  በፈጸምከው  መስዋዕትነት  ወደ  ባህረይ  አባትህ  ወደ  እግዚአብሔር  አቀረብከን  ከእርሱም  ዕርቅንና  ሰላምን  እንድናገኝ  አደረከን  እንዳል  ሊቁ " ። 

    የነቢያት  ሁሉ  ዋናው  የትንቢታቸው  ዓለም  ወልደ  አብ  ወልደ  ማርያም  ክርስቶስ  በህማመ  መስቀል፣በሞተ  መስቀል  ዓለምን  ሁሉ  እንደሚያድን  መግለጽ  ነበር።  የሐዋርያትም  ስብከት " ንህነስ  ንስብከ  ክርስቶስሃ  ዘተሰቅለ "  እኛስ  የተሰቀለውን  ክርስቶስን  እንሰብካለን "  የሚል  ነበር (1 ኛቆሮ 1 ፣ 23)  ለዚህ  ነው  ሊቁ  ዮሐንስ  አፈወርቅ  ስለ መስቀል  ኃይል  ሲናገር " መስቀል  የክርስቲያኖች  ተስፋ  ነው፣መስቀል  ተስፋ  ቅቡጻን  ነው "  ካለ  በኃላ " መስቀል  ክብረ  ሰማዕት  ነው፡  መስቀል  የጻድቃን  ሞገስ  ነው፣  መስቀል  የመነኮሳት  ጽሙና  ነው፤መስቀል  የደናግል  ንጽሕና  ነው፣ መስቀል  የቤተክርስቲያን  መሠረት  ነው፣  መስቀል  የዓለም  መረጋጋት  ሰላምም  ነው። "  ያለው ( ግብረ  ዮሐንስ  አፈወርቅ  ቅፅ 2)  ይህ  ሊቅ  በሌላ  ክፍል " ክፉ  መንፈስ  የተመታበትንና  የቆሰለበትን  ሰይፍ  ካየ  ወደ  ባለ  ሰይፉ  ሊቀርብ  አይችልም . . . 

    ስለዘህ  በቤታቻን፣በግድግዳ  ችን  የመስቀል  ምልክት  ይኑረን።ምክንያቱም  መስቀል  ድላችን  ነውየቤተክርስቲያን  ጌጥ  ነው  በመሆንም  መስቀሉን  በኣእምሯችሁ  እንድ  ማህተም  አትሙት  ። ( ግብረ  ዮሐ . አፈወርቅ  ቅፅ 7)  በማለት  ይመክራል። 

    ይህን  ሁሉ  በማሰብ  ቤተክርስቲያን  ቅዱስ  መሰቀሉ  የራሷ  የክርስቶስ  አካል  በቀኖት የተቸነከረበት፤  ደሙ  የነጠበበት፣  ታላቅም  ኃይልየተፈጸመበት  ሰለሆነ  ትስመዋለች  ታከብረዋለች።  በዓመት  ሁለተ  ገዜ ( በመጋቢት 10  እና  በመስከረም 17)  ልዩ  ሥነ - በዓል  አድርጋ  ብታከብረውም  በየዕለቱምና  በየሰዓቱም  ነገር  መስቀሉን  ታስባለች።  ነገር  መስቀሉ  የማይዘከርበት፣ የመስቀል  ክብሩ የማይነገርበት  ሥርዓተ  አምልኮት፤  ሥርዓረ  ማኀሌትና  ሥርዓተ  ጸሎትም  የላትም።  በመስቀል  የሰው  ልጅ  የበደል  ካሳ  አግኝቶበታልና።  በዓሉም  የሚከበረው  መስቀል  ከተቀበረ  ከሦስተ  መቶ  ዓመታት  በኋላ  መገኘቱን  ምክንያት  በማደረግ  ነው። 

    ንግሥተ  ዕሌኒ  ኪራኮስ  በሚባል  ሽማግሌ  በተነገራት  መሠረት  መስከረም  ዐሥራ  ስድስትቀን  ደመራ  ዕጣን  አስጭሳ  በእግዚአበሔር  አመልካችነት  የተቀበረበትን  ቦታ  አገኘች። በዚህም  መሠረት  መስከርም  ዐሥራ  ሰባት  ቀን  ቁፋሮ  አሰጅምረ  መጋቢት  ዐሥር  ቀን  ተገኝቶ  ወጥቷል።  በኋላም  ለመስቀሉ  መታሰቢያ  አሠርታ  ተመርቆ  የገባው ( ቅዳሴ  ቤቱ  የተከበረው )  መስከርም  ዐሥራ  ሰባት  ቀን  ስለሆነ  ሁለቱም  ዕለታት  ተከብረዋል።  በደማቅ  ሁኔታና  በመጀመሪያ  ደረጃ  መስከርም  ዐሥራ  ሰባት  ቀን  እንዲከበር  ያደረገው  ምክንያት  ግን  መጋቢት  ዐሥር  ቀን  ሁልጊዜ  በዐብይ  ጾም  ወቅት  የሚውል  መሆኑና  ይህንንም  ተከትሎ  እዚያው  መስቀሉ  የተገኘበት  ቦታላይ  ለመስቀሉ  የተሠራው  ቤተ  መቅደስ  የከበረው  መስከረም  ዐሥራ  ሰባት  ቀን  መሆኑ  ነው።

    ይህንንም ስንክሳሩ <<  የከበር መስቀልም  ዳግመኛ  የተገለጠበት  መጋቢት  ዐሥር  ቀን  ነው። ዜናውንም  በዚሁ  ቀን  ጽፈናል። ምዕመናንም  በታላቁ  ጾም  መካከል  በዓሉን  ማክበር  ሰላልተቻላቸወ  በዓሉን  ቤተ ክርስቲያኑ  በከበረችበት  ቀን  አደረጉ  ይህም መስከርም  ዐሥራ  ሰባት  ቀን  ነው።  በዚህም  ቀን  አስቀድሞ  ከከበረ  መቃብር  በንግሥት  ዕሌኒ  እጅ  የተገለጠበት  ነው። >>  በማለት  ያስረዳል።  ስንክሳሩ  እንደሚገልጸው  ክርስቲያን  ሁሉ  የትንሣኤውን  በዓል  በኢየሩሳሌም  ተሰባስበው  ያክብሩ  እንደነበሩ  ሁሉ  የመስቀሉንም  በዓል  ከዚያ  ጊዜ  ጀምሮ  በአንድነት  ያከብሩ  ነበር።  የእኛ  ግን  ከዘመን  መለወጫችንና  ከጥቢ  ወራት  ጋር  የተገናኘ  መሆኑ  የበለጠ  እነዲከበር  አድርጎታል። 

    የበዓሉን  ሃየማኖታዊና  በሕላዊ  አከባበር  በአቡነ  ጎርጎርዮስ  የታረክ  መጽሐፍ  ላይእና  በሌሎቹም  ሰነዶች  ላይ  መመልት  ይቻላል። በኃይለ  መስቀሉ  ይጠብቀን ወስብሐት  ለእግዚአብሔር  ወለወላዲቱ  ድንግል  ወለመስቀሉ  ክቡር  አሜን

    ምንጭ፡-  ማኅበረ ቅዱሳን

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: መስቀል Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top