የጋብቻ ዓላማ ምንድነው
አንድ ልንፈጽመው ያልነው ነገር ዓላማ ሊኖረነው ይገባል እግዚአብሔር ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣ ዓላማ አለው አዋቂ እንደመሆኑ ሁሉን በዕውቀቱ አድርጓል፡፡ ኋላ ስለሚሆነው ሳያውቅ የሆነ ነገር የለም በዕውቀቱ ወሰን ገደብ የለበትም ስለዚህም ነው ከፈጠረው በኋላ አንኳን መልካም እንደሆነ አየ ብሎ ሙሴ የገለጠልን፡፡
ሰው በእግዚአብሔር አርአያ አምሳል እንደመፈጠሩ በስሜት በደመነፍስ የሚጓዝ ሳይሆን የሥጋው የደመነፍሱም ገዥ የምትሆን ሕያዊት ነፍስ አለችው ሲበድል፣ ከእግዚአብሒር የሚለየውን እኩይ ተግባር ሲፈጽም ‹‹ ሰው ግን ክቡር ሲሆን አላወቀም ልብ እንደሌላችው እንስሶቸ ሆነ መሠላቸው ‹‹መዝ48፥ 20 ይባላል ከገዥነት ወደ ተገዥነት ከአዋቂነት ወደ አላዋቂነት ወጣ የሥጋው የደመነፍሱ ገዥ የነበረው ለሥጋዉ ለደመነፍሱ ተገዢ ሆነ ነዉ የሚያስኘው፡፡ በዕውቀት ያለ ፥ ከዕውቀት ያልወጣ ግን ሁል ጊዚ የሚያስበው የሚፈጽመው ሊያደርገው የሚመኘውነገር ሁሉ ዓላማ ያለውነው፡፡ ለሰው ልጅም ጋብቻን ከመምራቱ በፊት ስለጋብቻ ዓላማ ሊገባው ይገባል እንደው በደመነፍስ የሚመሠረት አይደለም ይህ ሲባል ግን ደመነፍስዊ ዕዉቀት የለውም ማለት አይደለም ለምሳሌ ውሻ ደመነፍስ ያለው ፍጥረት ነው ወንዱ ሴቷን የሚፈልጋት ሲቷ ዘር ለመቀበል ዝግጁ በሆነችበት ጊዜ ነው በሌላ ጊዜ ይህ ዓይነት ፍላጓት አይኖራቸውም ሰው ግን ምንም እንስሳዊ ጠባይ ቢኖረውም ፍጹም እንደ እንሰሳዊ ተግባር ወይም አንሶ የሚፈጽምመው ተግባር አይደለም ሰው ከእንሰሳ ልዩ መሆኑን በዕውቀት ለያደርገው የሚገባ መሆኑን ለእንሰሳ አታመንዝር፣ የሌለውን ሚስት አትመኝ አትሰስን፣ከአንድ በላይ አታግባ የሚያምን ከማያምን አይጋባ ፣ባል በሚስቱ ሚስት በባልዋ የታስረች ናት(ነው)፣እግዚአብሄር አንድ ያደረገውን እንግዲህ ሰው አይለይ፣ሰው አባቱንና አናቱን ትቶ ሚስቱን ይከተላል የሚለው ሁሉ ለእንስሳት ለአራዊት ለአእዋፋት የተሰራላቸው ሕግ አይደለም ቢተላለፉም የሚቀጡበት ሁኔታ የለም ይህ ሕግ ለሰውልጆች የተሰራ ሕግ ነው ሚስት ባልዋ ለእሷ ብቻ እንዲሆን እንጂ ለሌላ እንዲሆን አትፈቅድም ወንዱም እንደሁ ስለዚህ ከሌላው ፍጥረት በተለየ በዕውቀት የምንፈጽመው መሆኑን ያመለክታል ከዚህም አንፃር ጋብቻ አላማ ያለውና በእውቀት የሚፈጸም ነው፡፡
ስለዚህ የጋብቻ አላማ፡-
ለመባዛት ነው ወይም ዘር ለመተካት ‹‹እግዚአብሄር ባረካቸው እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዓት ግዙዋትም ››ዘፍ1፥28 እግዚአብሔር ባረካችው ብሎ ጋብቻ በእግዚአብሔር በረከት የሚመሠረት እና ፍቃድ እንደሆነ ያመለክታል ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉዓት በማለት ጋብቻ የሚመሠረተው መብዛት መባዛት በምንደርስበት ዕድሜ የሚመሠረት መሆኑን ከዚያ በፊት የማይፈጸምመብዛት በምንደርሰበት ዕድሜ የሚመሠረት መሆኑን ከዚህ በፊት የማይፈጸም እንደሆነ በሌላ በኩል ይህ ቃል የሚያስገነዝበን መባዛት የማይችሉበት ዕድሜ ያለፋቸውን ጋብቻን የማይፈቅድ መሆኑን እንዲሁም መብዛት መባዛት የሊለበት ጋብቻ የማይፈቅድም መሆኑን በተጨመማሪም ለተመሣሣይ ፆታ ላላቸዉ ለሚፈጽሙት እግዚአብሔር ያልባረከው ርኩስ መሆኑን የሚገለጽ ነው፡፡
ይህ መባዛት ምንም እንሰሳትከሚባዙት መባዛት ጋር ቢያመሳሰለውም ይህ የተለየ ነው ለምን ቢባል?
በስሜት ብቻ ሳይሆን በዕውቀት የሚመሠረት ነዉ፡፡
በእግዚአብሄር መባረክ የሚመሠረት ነው ዘፍ1፥28
እግዚአብሔር አንድ የሚያደርገው ስለሆነ ማቴ19፥5
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች በመሆናችው መዝ126
የሚወለዱትም የእግዚአብሔር ገንዘቦች በመሆናችው የእግዚአብሔር ገንዘቦች ሲል የእግዚአብሔር አርኣያ አምሳል ስለሚኖራቸውና የክብሩ የመንግስቱ ወራሾች የሚሆኑት የሚገኙበት ተጨማሪም እርሱ ቅዱስ እንደሆነ የቅድስናው ተካፋይ የሚሆኑ እሱ ንፁሕ እንደሆነ የንጽሕና ተካፋይ የሚሆኑ ባጠቃላይ የመንግሥተ ሰማያት የሚሆኑትን የምናባዛበት ነው፡፡ ከመንግሥተ ሰማያት በኃላ ይህ መብዛት መባዛት አለመኖሩ በዚህ ምድር መባዛታችን ይህን ያመለክታል በዚህ ምድር ሌላ የምንኖርበት ዓለም ስለሌለ የዚያ ባለቤት የሚሆኑትን ለመገኘታችው ምክንያት እንሆናለን፡፡በመንግሥተ ሰማያት ሌላ የምንኖርበት ከመላእክት ጋር አንድ ሆነን በምሰጋና የምንተባበርበት እንጂ፡፡ ስለዚህም የእኛ መብዛት ምድራዊ ሳይሆን በዕውቀት እራሰን በመግዛት የሚመሠረት ነዉ፡፡
ሁለተኛው የጋብቻ ዓላማው ለመረዳዳት ነው፡-አንደኛው መረደዳት ከላይ ያለውን ሲያመለክት ማለትም ለመውለድ ሲሆን ወንድ ብቻ ቢሆን መወለድ አይችልም እንዲሁም ሴት በመወለድ የሚተባበሩበት ወይም አንድ የሚሆኑበት ነውበሌላ በኩል ደግሞ፡-
የአፍአ መረዳዳት ነው ይኸውም እሱ ለፍቶ ጥሮ ግሮ ደክሞ ለሚስቱ አምጥቶ ሲያሰረክብ እሷደግሞ የቤቱን በመሥራት የሥጋ ድካመቸውን የሚያቀሉበት ነው፡፡ የውጭውንም የቤቱንም አንዱ ብቻውን ከማከናወን የሚረዳዱበት ነው ይህ ማለት ግን ሚስት የውጭውን በመሥራት አትረዳውም ማለት ኣይደለም እሱም በቤት ዉስጥ ያለውን አይረዳትም ማለት አይድለም፡፡ ነገር ግን የቤት ውስጥ ሥርአት በማስያዝ በኩል ከወንዱ ይልቅ ሚስት ትሻላለች ሓዋርያውቅዱስ ጳውሎስም ለቲቶ በላከው መልእክት እንደህ በማለት ‹‹--- ጠባያቸውንና የቤታቸውን ሥርዓት እንዲያሳምሩ ለባሎቻቸውም እንዲታዘዙ ይምከሯቸው››ቲቶ2፥5 በማለት ገልፆታል፡፡ በሌላ መልክቱም ‹‹እንግዲህ እኔ ቆንጃጅት እንዲያገብ ልጆችንም እንዲወልዱ ቤተሰቦቻችውንም እንዲያስነቅፉ እፈቅዳለሁ›› በማለት ቤት ውስጥ ያለውን የቤተሰብ ማስተዳደር ድርሻ በበለጠ ለሴት (ለሚስት)ሲሰጣት እናያለን፡፡ ባጠቃላይ ጋብቻ መረዳዳት የተባለበት ሁሉን ነገር ሚስት ብቻ እንድትሸከም ወይም ወንዱ ብቻ እንዲሸከም ሳይሆን የሥጋ ድካማቸውን በመደጋገፍ የሚረዳዱበት ጥንከሬ የሚያገኙበት ነው፡፡ ወንዱ ብር ሰላመጣ የበለጠ ሚስት ብር ስለሌላት የወንዱ እጅ ስለምትጠብቅ ያነሰች አይደለችም ያነሰችም መስሎ ሊታያት አይገባም ሰራውን በመከፋፈል የጋራ አደረጉት እንጂ፡፡ ወንዱም ብሩን ስላመጣ የተለየ ክብር የተለየ ብልጫ ያለው አይደለም እንዲህ ያለ አስተሳሰብ ያለው ከሆነ የዘቀጠ አመለካከት ያላቸው ናቸዉ፡፡ በሌላ ብኩል ደግሞ ሚስት ውጪ ወጥታ ስለሰራች ገንዘብ ስላመጣች ለባልዋ የነበራት አክብሮት ተገዥነት የሚቀንስ ከሆነ የትዳር የመረዳዳት አላማ አልገባትም ተገዥነትዋ ለብር በማድረጓ የተገነባውን ቤት ለማፍረስ ለመናድ የምትሯሯጥ እንጂ ቤቷን ለማጠናከር ለማጽናት የምትፋጠን ባለ አእምሮ ሚስት አይደለችም ማለት ነው፡ ባል በውጪ ባሪያ ሚስት በማጅት በሪያ ባልም ሚስትም በሳሎን ጌታ እመቤት ናችው፡፡
ቢወድቅ ልታነሣው ብትወድቅ ሊያነሣት ቢታመም ልታስታምመው ብትታመም ሊያስታምማት መውደቁ መውደቅዋ መወደቅዋ መውደቁ መታመሙ መታመሟ መታመሟ መታመሙ ልታድረግ ሊያድረግ በስሜት በሃሳብ በፍቃድ አንድ ሆነው የሚረዳዱበት ነውለዚህስ አይደል ወንድ የሴት ራስ የተባለው ለአንድ አካል ሁለት ራስ የለም ባልና ሚስትም አንድ አካል ይሆናሉ የተባለው የቃል አይደለም ባልና ሚስት በተግባር ይህ ከልታየባቸው ወይም በሕይወታቸው ከልተገለጠ ምኑን አንድ አካል ናቸው ያሰኝል?
ለውስጥ መረዳዳት ነው፡-
0 comments:
Post a Comment