• በቅርብ የተጻፉ

    Sunday, 11 October 2015

    ኑኀሚን ማን ናት?

    ኑኀሚን በቤተልሔም ይሁዳ ትኖር የነበረች አቤሜሌክ ለሚባል ሰው ሚስት ስትሆን መሐሎንና ኬሌዎን የሚባሉ ሁለት ልጆችም ነበሯት፡፡ ‹‹አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለት ልጆች ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ በቤተልሔም ይሁዳ ተነሣና ሄደ፡፡
    የርሱም ስም አቤሜሌክ የሚስቱም ስም ኑኀሚን፤ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ የቤተልሔም ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ፡፡›› ሩት.1÷1-2

    ኑኀሚን በስደት ሃገር ሳለች ባሏ አቤሜሌክን በሞት፤ ከአሥር ዓመት ቆይታ በኋላም ሁለቱ ልጆቿን ወደ ሃገረ ከመመለሷ በፊት በዛው በስደት ሳለች በሞት ተነጠቀች ‹‹በዚያም አሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ፡፡ መሐሎንና ኬልዎንም ሁለቱም ሞቱ ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች፡፡›› መጽ.ሩት.1÷5
    ‹‹ኑኀሚን›› ማለት ደስተኛ ዕረፍት ያገኘች ማለት ነው፡፡

    የኑኀሚን ምሳሌነት

    ኑኀሚን በስደት ሳች ሁለት ልጆቿ ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አግብተው ነበር፡፡ ‹‹የኑኀሚን ባል አቤሜሌክ ሞተ፤ እርስዋና ሁለት ልጆቿ ቀሩ፡፡ እነርሱም ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፤ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም ሩት ነበር፡፡›› ፣መጽ. ሩት 1÷3-4 ከጊዜያት በኋላ ግን ሁለት ልጆቿን በሞት አጣች፡፡ ወደ ሃገሯም ለመመለስ በተነሳች ጊዜ ሁለቱ ምራቶቿ (የልጆቿ ሚስቶች) አብረዋት ሊሄዱ መንገድ ጀመሩ፡፡ ኑኀሚን ግን ባል አልባ ሁነው የቀሩት ምራቶቿ ደግሞ ለእነርሱ ባዕድ በሆነ በኑኀሚን ሃገር በይሁዳ ስደተኛ ሆነው እንዲኖሩ አልፈቀደችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኑኀሚን የቀረ ሃብት በሃገሯ የሚጠብቃት ስላልሆነ ነው፡፡ በመሆኑም ችግርን ብቻዋን ለመታገል በበጎ አስተሳሰብ ወደ እናታቸው ቤት እንዲመለሱ ነገረቻቸው፡፡ ‹‹እርሱዋም ከሁለት ምራቶቿ ጋር ከተቀመጠችበት ሥፍራ ወጣች ወደ ይሁዳም ምድር ሊመለሱ በመንገድ ሄዱ፡፡ ኑኀሚንም ምራቶችዋን፤ ሂዱ ወደ እናታችሁም ቤት ተመለሱ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችሁ፤ እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችሁ፡፡›› መጽ.ሩት 1÷7-8 ስትል በምርቃት ጭምር ምራቶችም እንዲመለሱ ማለትም እንደርስዋ በችግር እንዳይማቅቁ ያዘነች ታላቅ እናት ነች፡፡

    ኑኀሚን ለሰው በማዘን ብቻ አልነበረም ታላቅነቷ የተገለፀው፡፡ ይልቁን ሃዘኗንና ችግሯን በትዕግስት በማሳለፍም ሆነ በእምነት በመቀበል ለብዙዎች ምሳሌ የምትሆን ሴት ናት፡፡ ‹‹የሚያዝኑ ብጽአን ናቸው፤ መጽናናት ያገኛሉና፡፡›› ማቴ.5÷4 ተብሎ እንደተፃፈ የእምነት ጥንካሬዋን ያሰበላት እግዚአብሔር አምላክ መጨረሻዋን አሳምሮላታል የምራቷን የሩት ልብ ሰብሮ አብራት ወደ ቤቷ እንድትመስ አድርጓል፡፡ ‹‹ሩትም፡- ወደ ምትሄጂበት እሄዳለሁና፤ በምታድሪበትም አድራለሁና… ሕዝብሽ ሕዝቤ፤ አምላሽም አምላኬ ይሆናልና..ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች፡፡ ኑኀሚን ከእርሷ ጋር ለመሄድ እንደ ቆረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች፡፡›› መጽ.ሩት 1÷16-18 ከስደት ወጥታ ከእርሷ ጋር ወደ ሃገር ስትጓዝ ከከተማ በደረሰች ጊዜ ሕዝቡ ይህች ኑኀሚን አይደለችምን እያሉ በደስታ በተናገሩ ጊዜ እርሷ ግን ራሷን ዝቅ አድርጋ ፍፁም በመንፈስ ድሃ በመሆን ‹‹በመንፈስ ድሆች የሚሆኑ ብጽዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡›› ማቴ.5÷3 የሚለውን ቃል በተግባር ያስተማረች ታላቅ እናት ነች፡፡

    ኑኀሚን ለምራቷ ለሩት መልካሙን በመመኘትና በምክርም ጭምር እንድትለወጥና እግዚአብሔር አምላክን እንድታውቅ ያደረገች ሴት ናት፡፡ ይህም ሌላው ታላቅነቷ ነበር፡፡ ሩት ‹‹አምላክሽ አምላኬ ይሆናል›› ብላ በእምነት ከቤቷ ወጥታ ተከትላ ነበረና ከመልካም ሰው ላይ እንድትወድቅ ስትል ኑኀሚን ሩትን አጥብቃ ትመክራት ነበር፡፡ ከባሏ ዘንድ ማድረግ የሚገባትን ነገር ሁሉ ታስተምራት ነበር፡፡ ‹‹አማትዋ ኑኀሚንም አለቻት፡- ልጄ ሆይ፤ መልካም እንዲሆንልሽ ዕረፍት አልፈለግሽምን? አሁን ከአገልጋዮቹ ጋር የነበርሽበት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፤ እርሱ ዛሬ ሌሊት በዓውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል፡፡ እንግዲህ ታጠቢ፤ ተቀቢ፤ ልብስሽን ልበሺ፤ ወደ ዓውድማውም ውረጂ፤ ነገር ግን መብሉንና መጠጡን እስኪጨርስ ድረስ ለርሱ አትታይው፡፡ በተኛም ጊዜ የሚተኛበትን ሥፍራ ተመልከቺ፤ ገብተሸ እግሩን ግለጬ፤ ተጋደሚም፤ የምታደርጊውን እርሱ ይነግርሻል፡፡›› መጽ.ሩት 3÷1-5 ሩትም አመቷ ኑኀሚንን እጅግ ታከበራት ነበርና እንዳለቻት አረገች፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር ቦኤዝ ሩትን ሚስት ያደረጋት፡፡ ‹‹ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፤ ሚስትም ሆነችው ደረሰላትም፤ እግዚአብሔርም ጽንሱን ሰጣት፤ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡›› መጽ.ሩት 4÷13-15 በዚህም ሴቶች ኑኀሚንን አከበሯት፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፡፡

    ኑኀሚን ከራሷ አልፋ ከሞዓባውያን ወገን ለሆነችው ሩት ትልቅ ምሳሌ በመሆን ሩት ከደጋግ እናቶች መሀል እንድትመደብ ያደረገች ናት፡፡ ‹‹መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡›› ማቴ.5÷16 ፡፡ እን

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ኑኀሚን ማን ናት? Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top