• በቅርብ የተጻፉ

    Sunday, 11 October 2015

    ራሔል

    ራሔል ማን ናት?

    ራሔል የያዕቆብ አጎት የላባ ልጅ ናት፡፡(ዘፍ-29፤6) ላባ የያዕቆብ እናት የርብቃ ወንድም ነው፡፡ ዘፍ. 29፤1
    ራሔል የአባቷ የላባን ከብቶች በመጠበቅ ታገለግለው ነበር፡፡ እነሆ የላባ ልጅ ራሔል የአባቷን በጎች ይዛ ደረሰች፤እርሷ የአባትን በጎች ትጠብቅ ነበርና፡፡”ዘፍ.29፤9
    ራሔል የያቆዕብ ሚስት ዘፍ 29፤28፤ የዮሴፍና የብንያም እናት ነች፡፡ ዘፍ.30፤23፤ዘፍ-35፤18

    ራሔል እጅግ ውብ ነበረች፡፡ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች፤ፊቷም ውብ ነበር፡፡ዘፍ29፤17 ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው ስለታናሺቱ ልጅህ ሰባት ዓመት እገዛልሀለሁ ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እሷን ስጠኝ አለው ዘፍ.29፤18

    የራሔል ስህተት

    ራሔል የያቆዕብ የመጀመሪያ ሚስቱ አልነበረችም ያቆዕብ የመጀመሪያ ምርጫው እርስዋ ብትሆንም ነገር ግን ላባ ያቆዕብን በማታለል ቃሉን አፍርሶ ከሰባት ዓመታትን አገልግሎ በኋላ ሚስት ትሆነው ዘንድ የሰጠው ታላቂቱ ልያን ነበረ፡፡ከዚህ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ሰባት ዓመታትን አገልግሎ ያዕቆብ ልቡ የፈቀዳትን ራሔልን ሚስቱ ሊያደርግ ችሏል፡፡ እግዚአብሕርም የልያን ማህፀን ከርቶ ልጆችን ለያዕቆብ አስገኘለት፡፡ ራሔል ግን መካን ነበረች፤ በዚህም ቅናት አደረባት፡፡”ራሔል ግን መካን ነበረች፡፡” ዘፍ.29፤31 “ራሔልም ልጅ እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእህቷ ላይ ቀናችባት፤ የራሔል ስህተት በእህቷ ላይ መቅናቷ ብቻ አይደለም ነገር ግን ሁሉ የሚቻለው የአባቶቿ አምላክ እግዚአብሔር መኖሩን ዘንግታ የማህፀኗ መዘጋትን የያቆዕብ ስራ አድርጋ መናገሯ ነበር እንጂ፡፡ ያቆዕብንም ”ልጅ ስጠኝ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው፡፡ዘፍ. 30፤1
    ራሔል ልጅ ስጠኝ ብላ ያቆዕብን በመለመን ብቻ ሳትወሰን ካልወለድኩ ግን ሞቼ እገኛለሁ በሚል በነፍሷ ላይ ስልጣንን ልታደርግ ተበገረች፡፡ ማዳንም መግደልም የሚቻለውን አምላክ ረሳች፡፡ ያቆዕብ ግን የአምላኩን አድራጊነት ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና የማህፀንሽን ፍሬ የምከለክልሽ እኔ እንደ እግዚአብሔር ነኝን ብሎ ተቆጥቷታል፡፡ዘፍ.30፤2

    ያቆዕብ ከላባ ቤት ወጥቶ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር በኮበለለ ጊዜ ከላባ ቤት ይዞ የወጣው ልጆቹንና ሚስቶቹን እንደዚሁም የራሱ የሆኑትን ከብቶችና ንብረትን ብቻ ነው፡፡ነገር ግን በእግር እንጂ ከአባቷ ቤት የባዕድ አምልኮ ልቧን አጸድታ/ይዛ የእግዚአብሔር ሰው ባሏ ያቆዕብን መከተል ያቃታት ራሔል በቤቷ የነበረውን የአባቷን ጣዖት ደብቃ ይዛ መውጣቷ ሌላው ትልቁ ስህተቷ ነበር፡፡ ራሔልም የአባቷን ጣዖቶች ሰረቀች፡፡ዘፍ 31፤17-21 በዚህም ምክንያት ራሔል ሰውራ የያዘችውን ያላወቀው ያቆዕብ በመንገድ ላይ ከላባ ጋር ቅራኔ ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆናለች፡፡ዘፍ.31፤22-32 በዚህም ላይ ያቆዕብን አምላኮቼን ለምን ሰረቅህ/ ብሎ ሊወቅሰው ተገዷል፡፡ያቆዕብ ሚስቱ ራሔል እንደሰረቀቻቸው አያውቅም ነበር፡፡ዘፍ.32፤22-52

    የራሔል መልካምነት

    ራሔል ልጅ መውለድ በተሳናት ጊዜ ያቆዕብን ከአገልጋይዋ(ከገረዷ)ከባላ እንዲወልድላት ወደ ባሪያዬ ግባ ስትል በጠየቀችው መሰረት እርሱም ከባላ ዘንድ ገብቶ ሁለት ልጆችን ወለደላት፡፡ዘፍ. 35፤24 ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች ወደ እርስዋ ግባ በእኔ ጭን ላይም ትውለድ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ፡፡ ዘፍ.30፤33 ታዲያ ራሔልን መልካም ያሰኛት ባሪያዋን ባላን ሚስት አድርጋ ለያቆዕብ መስጠቷ ብቻ ሳይሆን የተወለዱትን ልጆች በተናገረችው መሠረት እንደ ልጆቿ አድርጋ ማሳደጓ ጭምር እንጂ፡፡

    ራሔል እግዚአብሔርን በመፍራትና በእውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይነቱ የሚታወቀውን ዮሴፍን በመልካም ሥነ-ምግባር ያሳደገች እናት ናት፡፡ይህም ምንም እንኳን ወንድሞቹ በቅናት ለይስማኤላውያን በሃያ ብር ቢሸጡትም እርሱ ግን ምንም ቂም ሳይዝ በችግራቸው/በረሃባቸው ጊዜ መልካሙን ሁሉ አድርጎላቸዋል በዚህም ዮሴፍ መልካም አስተዳደግ እንደነበረው እንረዳለን፡፡ ዘፍ.37፣ዘፍ-39
    ራሔል አባቷን በሥራ የምታገለግል ታዛዠ ልጅ ነበረች፡፡ የአባቷን ከብቶች በመጠበቅ(በእረኝነት) ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል በውጪው ሥራም የተሰማራች ሴት ነበረች፡፡ዘፍ.29፤6-9

    ከራሔል ምን እንማራለን?

    ሴት ልጅ በቤት ውስጥ ብቻ ሳትወስን በውጭም ባላ ማንኛውም ሥራ በመሳተፍ ራሷንና ቤተሰቧን ለመለወጥ መታገል እንዳለባት(እንደ ዘመኑ የሚተረጎም ነው፡፡) ዘፍ.29፤6-9
    ለችግራችን መፍትሔ ሊሰጠን የሚችለው ማን እንደሆነ ለይተን ማወቅ፤ ሰዎች እስከ ምን ያህል ርኅቀት ችግሮቻችንን ሊፈቱልን እንደሚቻላቸው ጠንቅቀን መረዳት እንዳለብን፡፡ዘፍ.30፤1-2

    አምላካችን እግዚአብሔርን ስንከተል የነበርንበትን ክፍት ሙሉ ለሙሉ ትተን በንጹህ ልቡና እና በንስሃ ሊሆን ይገባል፤በማመንታት ወይም በእግር ብቻ በመከተል ሁሉን የሚመረምር አምላክን ማታለል እንደማይቻል፡፡ እርፍ ይዞ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አይገባምና፡፡ዘፍ.31፤17-32
    ከአፋችን‹‹እናደርጋለን›› ብለን ያወጣነውን ቃል በመተግባር ታማኝነታችንን ማሳየት እንሳለብና፡፡ዘፍ.30፤3

    ልጆች ታማኝ ሆነው እንዲያድጉና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲያድርባቸው ቁልፍ ሚና እናቶች መጫወት እንደሚገበቸውና እንደሚችሉ፡፡ዘፍ-37
    (ይቆየን

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ራሔል Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top