• በቅርብ የተጻፉ

    Tuesday 10 November 2015

    ዓመታዊ እና ወርሃዊ መታሰቢያ በዓላት




    መስከረም

    መስከረም 1. ቅዱስ ራጉኤል (ርእስ አውደ ዓመት/

     መስከረም  2. ቅዱስ ዮሀንስ /አንገቱ የተቆረጠበት ቀን/

    መስከረም  10. ፀደኒያ ማርያም

    መስከረም 15  ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሾመበት) (ይህ በዓል ከመስቀል በዓል ጋር የሚታሰብ ነው)

    መስከረም 17 ቅዱስ እስጢፋኖስ /በዓለ መስቀል/

    መስከረም 21. መናገሻ ማርያም ፡ግሼን ማርያም ፡እንጦጦ ማርያም

    መስከረም 29. ቅድስት አርሴማ

    ጥቅምት

    ጥቅምት 5. አቡነ ገብረመንፈስ

    ጥቅምት 9. አባ አትናስዮስ(እፍቱ)

    ጥቅምት 12.አባ ዲሜጥሮስ(እረፍቱ)

    ጥቅምት 13.አባ ዘካርያስ(እረፍቱ)

    1.   ልደታ፣ዮሐንስ ፣ራጉኤል ፣እዮብ ፣ኤልያስ ፣ ሶስና2.   በርቶሎሚዎስ ፣ጴጥሮስ ፣አባ ጉባ ፣መሪና3.   በአታ ማርያም ፣ፋኑኤል ፣ዜና ማርቆስ4.   ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፣አባ መቃርዎስ፣ አባ አብርሐ5.   ጴጥሮስና ጳውሎስ ፣ገብረ መንፈስ ቅዱስ6.   ቁስቋም ፣ኢየሱስ ፣አርሴማ ቅድስት ፣እያሱ7.   አጋዕዝተ አለም ስላሴ ፣ዲዎስቆሮስ8.   ኪሮስ ፣ማቲዮስ፣ ኪሩቤል አርባእቱ እንስሳ፡ ዘካርያስ9.   ሰልስቱ ምዕት፣ ቶማስ ፣እስትንፋሰ ክርስቶስ ፣አትናትዮስ10. መስቀለ ክርስቶስ ፣ናትናኤል ሐዋርያ ፣ፀደንያ ማርያም11. ሐና እና ኢያቄም ፣አቡነ ሐራ12. ሚካኤል፣ አባ ሳሙኤልና ፣ ናትናኤል ሐዋርያ13. ፀጋ ኢየሱስ/ ዘርአ ብሩክ/ ፣ሩፋኤል ፣እግዚአብሔር አብ14. አቡነ አረጋዊ ፣ገብረ ክርስቶስ/ገብረ መርአዊ/ ዘሚካኤል ፣ሙሴ ፀሊም15. ቂርቆስና እየሉጣ ፣ሚናስ16. ኪዳነ ምህረት ፣ኤልሳቤጥ17. እስጢፋኖስ ፣ገሪማ ፣ወለተ ጴጥሮስ ፣አቡነ በትረ ማርያም ፣ ያዕቆብ ወልደ ዘብዲዮስ ፣ሙሴ18. ማዕቀብ አልፋ ፣ኢዩስጣቲዮስ ፣ፊሊጶስ19. ገብርኤል ፣ስልስቱ ደቂቅ፣ ይመርሐነ ክርስቶስ20. ፣ዮሐንስ  ሀፂር ፤ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን21. ቅድስት ድንግል ማርያም22. ሉቃስ ፣ደቅስዮስ ፣ኡራኤል ፣ ብስራተ ገብርኤል23. ቅዱስ ማር ጊዮርጊስ24. ተክለ ሐይማኖት ፣ጎርጎርዮስ ፣24ቱ ካህናተ ሰማይ፣ ክርስረቶስ ሰምራ25. ቅዱስ መርቆሬዎስ ፣አቡነ ሀቢብ26. ዮሴፍ፣ ቶማስ ዘህንደኬ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም27. መድሐኔአለም ፣አቡነ መባዓ ፅዮን ተክለ አልፋማርያም28. አማኑኤል ፣ .አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ  29. በዓለ እግዚአብሔር (በዓለወልድ)፣ቅዱስ ላሊበላ ፣ቅድስት አርሴማ30. ቅዱስ ማርቆስ ፡ ዮሐንስ መጥምቅ

    ጥቅምት 14. አቡነ አረጋዊ (የተሰወሩበት)፡ በገብረክርስቶስ(እረፍቱ)፡ ኢትዮጰያዊውን ጀንደረባ ያጠመቀውን ዲያቆኑ ፊሊጶስ (እረፍቱ)

    ጥቅምት 17. ቅዱስ እስጢፋኖስ(የተሸመበት)

    ጥቅምት 20. ዮሐንስ ሐፂር(እረፍቱ)

    ጥቅምት 21.ነቢየ እግዚአብሔር ኢዩኤል (እረፍቱ)

    ጥቅምት 22. ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (እረፍቱ) ጥቅምት 25  አቡነ ሀቢብ አረፈ

    ጥቅምት 27. መድሐኔአለም: አባ መብዓ ፅዮን (እረፍታቸው)

    2ጥቅምት 8. ቅዱስ አማኑኤል

    ጥቅምት 30. ቅዱስ ማርቆስ /ልደቱ/


    ህዳር 

    ህዳር 6. ቁስቋም ማርያም እመቤታችን ስደቷን ጨርሳ የገባችበት

    ህዳር 7. ሕንጻ ቤቱ ለጊዮርጊስ/ አጥንቱ ተሰብስቦ መቃብር ቤት የገባበት/

    ህዳር 8.  በዓል አርባዕቱ እንስሳ /ክሩቤል ሱራፌል/አባኪሮስ

    ህዳር 11. ዕረፍተ ቅድስት ሀና

    ህዳር 12. ቅዱስ ሚካኤል፡

    ህዳር 13. እግዚአብሔር አብ/የአእላፍ መላእክት ቀን

    ህዳር 14. አባ ዳንኤል እረፍቱ

    ህዳር 15. ቅዱስ ሚናስ እረፍቱ

    ህዳር 18. ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ እረፍቱ ከ12ተ ሐዋርያት አንዱ

    ህዳር 21. ፅዮን ማርያም/የእመቤታችን በዓል/

    ህዳር 24. ሀያአራቱ ካህናተ ሰማይ /ደብረ ሊባኖስ/

    ህዳር 25. ቅዱስ መርቆሪዎስ ሰማዕቱ /እረፍቱ/

    ህዳር 26. አቡነ ሀብተማርያም /ደብረሊባኖስ/፡ አባ ኢየሱስ ሞአ(እረፍቱ)

    ህዳር 27. አባ ተክለሃዋርያት ፡ ሐዋርው ቅዱስ ያዕቆብ በሰማዕትነት አረፈ

    ህዳር 29. ተፈፃሚ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ(እረፍቱ)

    ታህሳስ

    ታህሳስ 1.ነቢዩ ኤልያስ የተወለደበት ቀን

    ታህሳስ 3. በአታ ለማርያም እመቤታችን በሶስት አመቷ ቤተመቅደስ የገባችበት፡ አቡነ ዜና ማርቂስ(እረፍቱ)

    ታህሳስ 4. ሐዋርያው እንድርያስ በሰማዕትነት ያረፈበት

    ታህሳስ 6. ቅድስት አርሴማ(ቅዳሴ ቤቷ)

    ታህሳስ 12. አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

    ታህሳስ 13. ቅዱስ ሩፋኤል

    ታህሳስ 15. አባ ጎርጎርዮስ (እረፍቱ) ዘሀገረ አርማንያ

    ታህሳስ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል

    ታህሳስ 22. ብስራተ ገብርኤል /እመቤታችን ክርስቶስን እንደምትወልድ ያበሰረበት/

    ታህሳስ 24. አቡነ ተክለሀይማኖት /ልደታቸው/

    ታህሳስ 28. ቅዱስ አማኑኤል በዓለ ልደት ለእግዚእነ ገና

    ታህሳስ 29. ቅዱስ በዓለ ወለድ /ተዘከረ ልደቱ ለእግዚነ/ገና/

    ጥር

    ጥር 1. ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሚ ሰማእት (እረፍቱ)

    ጥር 4. ቅዱስ ዮሐንስ /ወንጌላዊ/ወልደ ነጎድጓድ

    ጥር 6. ኢየሱስ/ግዝረቱ ለእግዚእነ /እየሱስ ገዳም/ ነቢዩ ኤልያስ የተሰወረበት ቀን

    ጥር 7. ቅድስት ሥላሴ

    ጥር 11. በዓለ ጥምቀት

    ጥር 12. በዓለ ቅዱስ ሚካኤል /ቃና ዘገሊላ/

    ጥር 13. ቅዱስ ሩፋኤል /የቃና ዘገሊላ በዓል መታሰብያ/

    ጥር 14 አቡነ አረጋዊ

    ጥር 15. ቅዱስ ቂርቆስ እየሉጣ

    ጥር 18. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ዝርዎተ አጽሙ/

    ጥር 21. የእመቤታችን በዓለ እረፍት

    ጥር 22. ቅዱስ ኡራኤል ቃል ኪዳን የተቀበለበትና የተሸመበት ቀን

    ጥር 23. ሐዋርያው ጢሞቲዋስ (እረፍቱ)

    ጥር 24. አቡነ ተክለሃይማኖት

    ጥር 28. ቅዱስ አማኑኤል ለ5000 ሰዎች ጌታችን ህብስቱን ያበረከተበት

    የካቲት  

    የካቲት 3. አባ ያዕቆብ (እረፍቱ)

    የካቲት 8. ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ወደ ምኩራብ የገባበት ቀን(የአረጋዊው የስምዖን ታሪክ ልብ የበሉ)

    የካቲት 9. አባ በርሱማ (እረፍቱ)

    የካቲት 15. ነቢዩ ዘካርያስ (እረፍቱ)

    የካቲት 16. ኪዳነምህረት /እመቤታችን ቃልኪዳን የተቀበለችበት/

    የካቲት 20. ቅዱስ ፊልጶስ

    የካቲት 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ

    የካቲት 26. ነቢዩ ሆሴዕ (እረፍቱ)

    የካቲት 28. ሮማዊው ቅዱስ ቴዌድሮስ(እረፍቱ)

    መጋቢት

    መጋቢት 4. ቅዱስ ጊዮርጊስ /ደብረዘይት/

    መጋቢት 3. ተዝካረ ልደቱ ለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ

    መጋቢት 10. መስቀሉን ንግስት እሌኒ ቆፍሬ ያገኘችበት ቀን መድሀኔአለም

    መጋቢት 15. ቅድስት ሳራ(እረፍቷ)

    መጋቢት 22. ጥንተ ሆሳእና

    መጋቢት 27. ቸሩ መድሃኒአለም (የጌታችን ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ)

    መጋቢት 29. የበዓለ ወልድ /የጌታችን ጽንሰት/

    ሚያዝያ

    ሚያዝያ 22. አባ ይስሀቅ(እረፍቱ)

    ሚያዝያ 23. የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍት

    ሚያዝያ 27. ምስካየ ሕዙናን /ስደተኛው መድሀኒአለም/

    ሚያዝያ 30. ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ያረፈበት ቀን ነው

    ግንቦት

    ግንቦት 1. ልደታ እመቤታችን የተወለደችበት ቀን ነው

    ግንቦት 7. ሊቁ አቡነ አትናቲዎስ (እረፍቱ)

    ግንቦት 11. ቅዱስ ያሬድ(የተሰወረበት)

    ግንቦት 12. አቡነ ተክለሃይማኖት /አፅማቸው የፈለሰበት /ክርስቶስ ሳምራ

    ግንቦት 14. አቡነ አረጋዊ፡ ቅዱስ ገብረክርስቶስ

    ግንቦት 17. አባ ኤጲፋንዮስ(እረፍቱ)

    ግንቦት 21 .  እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአራት ቀን የታየችበት ነው

    ግንቦት 24. ቁስቋም ማርያም /የስደቷ መነሻ/

    ግንቦት 28. ቅዱስ አማኑኤል፡ ቅድስት አመተ ክርስቶስ (እረፍቷ)

    ሰኔ

    ሰኔ 8. ከደረቅ ዓለት ላይ ውሃን ያፈለቀበት ከ33ቱ ከእመቤታችን በዓል አንዱ

    ሰኔ 9. ታላቁ ነብይ ሳሙኤል(እረፍቱ)(የሐና ልጅ)

    ሰኔ 11.ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውድዮስ (እረፍቱ)

    ሰኔ 12. ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከውሃ ያወጣበት ቀን ነው(አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት)፡ ቅዱስ ላሊበላ(እረፍቱ)

    ሰኔ 20.ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን

    ሰኔ 21. ጌታችን /የእመቤታችንን ቤት ያነጸበት ቀን ነው፡፡ ግሽን ማርያም በጎልጎታ በጌታችን መቃብር የጸለየችበት

    ሰኔ 23.ጠቢቡ ሰሎሞን እረፍቱ

    ሰኔ 24. አባ ሙሴ ፀሊም(እረፍቱ)

    ሰኔ 25. የዮሴፍ ልጅ ሐዋርው ይሁዳ እረፍቱ

    ሰኔ 26. ኢያሱ እረፍቱ

    ሰኔ 27.  እረፍቱ ለሐናንያ ሐዋርያ

    ሰኔ 30. ልደተ ዮሐንስ መጥምቅ

    ሐምሌ

    ሐምሌ 2. ሐዋርያው ታዴዎስ(እረፍቱ)

    ሐምሌ 3. አባ ቄርሎስ(እረፍቱ)

    ሐምሌ 4. ነቢዩ ሶፎንያስ እረፍቱ

    ሐምሌ 5. ጴጥሮስና ጳውሎስ እረፍታቸው

    ሐምሌ 7. አጋእዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እረፍቱ

    ሐምሌ 8. አባ ኪሮስ

    ሐምሌ 10.ሓዋርያው ናትናኤል እረፍቱ

    ሐምሌ 15. ኤፍሬም ሶርያዊው እረፍቱ

    ሐምሌ 16. ወንጌላዊው ዮሐንስ እረፍቱ

    ሐምሌ 18 .የጻድቁ የዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ያዕቆብ እረፍቱ

    ሐምሌ 19. በዓለ ቅዱስ ገብርኤል ቂርቆስና እየሉጣን ከእሳት ያዳነበት ቀን ነው/ቁልቢ ገብርኤል/

    ሐምሌ 22. ቅዱስ ኡራኤል ፡አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት

    ሐምሌ 23. ቅዱስ ጊዮርጊስ

    ሐምሌ 26. ቅዱስ ዮሴፍ (እረፍቱ) ፡አቡነ ሀብተማርያም ዘደብረሊባኖስ

    ሐምሌ 28.ቅድስት መስቀል ክብራ (እረፍቷ)(የቅዱስ ላሊበላ የትዳሩ አጋር)

    ሐምሌ 30.ቅድስት ማርያም ክብራ(እረፍቷ)

    ነሐሴ

    ነሐሴ 7.ፅንሰታ ለማርያም

    ነሐሴ 13. እግዚአብሔር አብ በደብረታቦር ተራራ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱ ለእነ ሙሴና ኤልያስ የገለጸበት ቀን ነው/የቡሄ በዓል/

    ነሐሴ 15. ቅድስት እነባመሪና(እረፍቷ)

    ነሐሴ 16. ኪዳነምህረት

    ነሐሴ 19. አባ መቃርስ የስጋው ፈልሰት

    ነሐሴ 21. ጌቴ ሴማኒ ገዳም እመቤታችን  (ሰበታ)

    ነሐሴ 24. አቡነ ተክለሃይማት እረፍታቸው ፤ክርስቶስ ሳምረ

    ነሐሴ 27 ቅዱስ ሱርያል(4 ሊቀ መላእክት)

    ነሐሴ 28.አበው አብርሃም ይህሳቅ ያዕቆብ (እረፍታቸው)

    ጳጉሜ

    ጳጉሜ 2.ሐዋርያው ቲቶ (እረፍቱ)

    ጳጉሜ 3. ቅዱስ ሩፋኤል

    ጳጉሜ 4.አባ ባይሞን(እረፍቱ)

    ወርሃዊ በዓላት

    “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።” ዘሌ 19፤2 በተባለው መሰረት ቅዱስ የሚለው
     ስያሜ በምግባር በቱርፋትለጽኑየሚታየውን አለም ለለወጡ ከዚህ አለም ደስታ ተድላ ይልቅ
     ዘላለማዊውን ለመረጡ ፤በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እራሳቸውንለኃላፊው ነገር ላላስገዙ የሚሰጥ 
    ስያሜ ነው። ስለዚህመ ለቅዱሳን የሚገባውን መታሰቢያ እናደርጋለን “እንግዲህ ምን እላለሁ?
    ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለነቢያትም
     እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥
    የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥
     ከድካማቸው በረቱ፥በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ
     ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉየሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤
     ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትናበወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ 
    ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራንእየተቀበሉ እየተጨነቁ 
    የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድርጕድጓድ
     ተቅበዘበዙ። /ዕብ 11፤26/  የተባለው በፅናትና በትጋት እግዚአብሔርን ላገለገሉ ቅዱሳን ነው፡፡                  

    አስተያየቶ እንዳይለየን የቅዱሳን አምላክ ከሁሉ ነገር ይጠብቀን፡፡

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ዓመታዊ እና ወርሃዊ መታሰቢያ በዓላት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top