ክፍል ሶስት መልክዐ ተክለሃማኖት
፪ ሰላም ለዝክረ ስምከ በጥንተ ፊደሉ መስቀል
ስም ክቡር ወስምልዑል።
ተክለሃማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል
ከመ እወድሰከ መጠነ አውሥኦተ እክል።
ማዕሠረ ልሳንየ ትፍታሕማርያም ድንግል።
ትርጉም <<የስምሀ መነሻፊደል የመስቀል ምልክት ለሆነውእና ክቡር ገናና ለሆነው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ ።የወንጌል ተቀዳሚ ስም ማቴዎስ የተባልክ ተክለሃይማኖት ሆይ እንደ ችሎታዬ አመሰግንህ ዘንድአንደበቴ ትፈታልኝ ዘንድ ድንግል ማርያምን እማልዳለሁ። >>
የአባታችን የቅዱስ ተክለሃማኖት የስማቸው መነሻ ፊደል‘’ተ’’ የመስቀል ቅርጽ ያለው ነው የስማቸውም ትርጉም ተክለ አብተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው ይህም በስማቸውላይ ስመ እግዚአብሔር እንዳለ ያስረዳናል በገድላቸው እንደተጻፈውይህንን ስም አባታችን ያገኙት የመንፈሳዊ ተጋድⶀአችው የቅርብረዳት በሆነው በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት ነው ገድ ተክ፳፰ ፤፲፪የቀድሞ ስማቸው ፍስሐ ጽዮን ነው ትርጉሙም የጽዮንየቤተክርስትያን ፤የእመቤታችን ደስታ ማለት ነው ። በአጠቃላይየአባታችን የቅዱስ ተክለሃይማኖት ስም የእግዚአብሄርን ክብርየሚገልጽ ልዩ መንፈሳዊ መልክዕት የያዘ ስም ነው።ስለስማቸውለመግቢያ ያህል ይህንን ካልን መጽሐፍ ቅዱስ ስለቅዱሳን ስም ምንእንደሚል አንዳንድ ነገሮችን እንመልከት
፩. በቅዱሳን ስም ላይ የእግዚአብሔር ስም ይከብራል
« በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱስለሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምናአታስመርሩት»ዘጸ፳፫፤፳፩
፪ .የቅዱሳን ስም ከስም ሁሉ የሚበልጥ ነው «……..ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚበልጥ መታሰቢያስም ………» ኢሳ፶፮፤፭
፫.የቅዱሳን ስም ዘላለማዊ እና የማይጠፋ ነው
«የማይጠፋም ዘላለማዊ ስም እሰጣቸዋለሁ» ኢሳ፶፮፤፮
፬. በቅዱሳን ስም የእግዚአብሔር ቤት እና ቅጽሩበመታሰቢያነት ይሰየማል
«በቤቴ እና በቅጽሬ ውስጥ……. የዘላለም ስምእሰጣቸዋለሁ» ኢሳ፶፮፤፭
፭. በሰማያዊት ቤተ መቅደስ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ስምቀጥሎ የቅዱሳኑ ስም ተጽፎአል
«በእነርሱም የአስራ ሁለቱ የበጉ ሃዋርያት ስሞች ተጽፈውነበር» ራእይ፳፩፤፲፬
፮. በቅዱሳን ስም ዝክር ማዘከር ፤ በጎ ሰራ መስራት ሰማያዊዋጋ አለው
«ከነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻበደቀመዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋባትም ።» ማቴ፲፤፵፪
እንግዲህ የቅዱሳኑ ስም ይህን ያህል የከበረ ከሆነ ለከበረውስማቸው ሰላምታ መስጠት ምን ነውርነት አለው ?ስማቸውየእግዚአብሔር ስም የሚገለጥበት ከሆነ ለስማቸው ክብርመስጠት የእግዚአብሔርን ስም ማክበር አይደለምን ? ስማቸውበሰማያዊት ቤተ መቅደስ በክብር ከተጻፈ በስማቸውየእግዚአብሔር ቤት የሚሰየም ከሆነ ለስማቸው ክብር ሰላምታመስጠት እንዴት ሊገርመን ይችላል ? ? በስማቸው የሚሰራ በጎስራ ሰማያዊ ዋጋ ካለው የቅዱሳኑን ስም በማወደስ ጸጋና በረከትአይገኝምን ? በአባታችን በቅዱስ ተክለሃይማኖት መልክዐጸሎታቸውም ላይ ለስማቸው ሰላምታ እና በጸጋ ምስጋናቢቀርብላቸውመጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያድረገ ነው ከላይእንደተዘረዘርው እግዚአብሔር አምላክ የወዳጆቹን ክብርበስማቸው ቀርቶ በለበሱት ልብስ ፤ በረገጡት መሬት ፤በጥላቸውስ እንኳን ሳይቀር ይገልጽ የለምን ? ቅዱስ ጳውሎስበልብሱ እራፊ ጨርቅ ድውያንን ይፈውስ ነበር፤ቅዱስ ጴጥሮስበጥላው ድውያንን ይፈውስ ነበር(የሐዋ፭፤፲፭ የሐዋ፲፱፤፲፪)ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን በቅዱሳኑስም እግዚአብሔር ድንቅስራዎችን እንደሚሰራ ያምናሉ በስማቸውም የቅዱሳንን አምላክይማጽናሉ ስለዚህም ነው የአባታንን ስም እያነሱ መጸለይ ተግቢመሆኑን ከመልክዐ ጸለታቸው የተመለከትነው።
፫. ሰላም ለስእርተ ርእስከ በኅሊና አምላክ ዘተፈቅዳ ።
እንተ ቦን ግልባቤ አምሳለ ሠላስ ደቂቀ ይሁዳ
ተክለ ሃይማኖት ማርቅስ ጸሐፌ መንክራት ውስተ ሰሌዳ ።
አበውእ ለከ እግዚኦ ዘስብሐተ ጋዳ። ህየንተ ወርቅወብሩር ጸዐዳ።
ትርጉም እንደ ይሁዳ ልጆች መጎናጸፍያ ለሆኑትና የቁጥራቸውብዛት በአምላክ ዘንድ ለሚታወቅ በራስህ ላይ ለሚገኝ የጸጉርህ ብዛት ሰላም እላለሁ ። እንደ ቅዱስ ማርቆስ ድንቅ የምትሆንወንጌልን የጻፍክና የሰበክ ተክለሐይማኖት ሆይ በወርቅ በብር ፈንታ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርብልሃለሁ።
ይህ ሰላምታ ከአባታችን ተክለሕዋሳት መካከል የጸጉራቸውን ክፍል የሚያወድስ ክፍል ነው ከንባቡ እንደምንረዳው የአባታችን የጸጉራቸው ብዛት በአምላክ ዘንድ እንደሚታወቅ ይገልጻል ።ይህም እውነት ነው ጌታ በወንጌል ሲያስተምር እንኳንስ የአባታችንየእያንዳንዳችን የጸጉር ብዛት በእግዚአብሔር የተቆጠረ መሆኑንገልጾልናል
«የእናንተ የራሳችሁ ጸጉር ሁሉ እንኳን የተቆጠረ ነው» ሉቃ፲፪፤፯
ስለዚህም በመልክዐ ጸሎታቸው ላይ የአባታችን የራሳቸው ጸጉርብዛት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሚታወቅ መገለጹ ትክክል ነውማለት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ልዑል እግዚአብሔርበመረጣቸው ቅዱሳን በጸጉራቸውም ሳይቀር ኃይሉን እንደሚገልጽስለ ጸጉራቸው በተለየ ሁኔታ የተነግረላቸውን መስፍኑ ሶምሶንን እናመጥምቁ ዮሐንስን ማንሳት ሃሳቡን የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል።በሶምሶን ላይ የእግዚአብሔር ኃይል የተገለጸው በጸጉሩ ነበርለዚህም ነው ሶምሶን እራሱ እንዲህ በማለት የተነገረው
«እኔ ከናቴ ማህጸን ጀምሬ ለእግዚአብሔር የተለየው ሰው ነኝበራሴ ላይ ምላጭ አልደረሰም የራሴንም ጸጉር ብላጭ ኃይሌ ከኔይሄዳል እደክማለሁም እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ» መሳፍ ፲፮፤፲፯
አዎ ቅዱሳንን እግዚአብሔር ከማህጸን ጀምሮ ይመርጣል በተለያዩየህዋሳት ከፍሎቻቸውም ኃይሉን ይገልጻል አባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖትም በፈቃደ አምላክ በብስራተ መልአክ ከማህጸንየተመረጡ ጻድቅ ናቸው ከራስ ጸጉራቸው አንስቶመላ ህዋሳቶቻቸውን ለእግዚአብሄር የተለዩ ናቸው ስለዚህም በመላአካላቸው ሊወደሱ ሊመሰገኑ ይገባል።
ሌላው በዚህ ክፍል ላይ የተገለጸው አባታችን ልክ እንደቅዱስ ማርቆስ ግሩም ድንቅ የምትሆን ወንጌልን እንደጻፉናእንደሰበኩ ነው። በዕርግጥም አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖትሐዲስ ሐዋርያ የወንጌል ሰባኪ ናቸው በሰው ልብ ላይ ወንጌልንስለጻፉ የወንጌም ጸሐፊ ናቸው። ቅዱስ ተክለሃይማኖት ወንጌልንአልሰበኩም የሚል ተከራካሪ ቢነሳ ግን ገድላቸውን አንብበህ ፍረድከማለት ውጭ ምንም ሊባል አይቻልም።በምድረ ኢትዮጵያንደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተዘዋውረው ብዙዎችን ከአምልኮተጣኦት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረጽድቅ የመለሱ ቅዱስ ተክለሃይማኖት አይድሉምን ? ከዚህ በላይወንጌልን መስበክ አለን ? ቅዱስ ማርቆስ ከግብጽ ጣኦታት ጋራብዙ መከራ እየተቀበለ ተጋድሎ ወንጌልን እንደሰበከ አባታችንቅዱስ ተክለሃይማኖትም በአገራችን ይተለያዩ ስፍራዎች በመዟዟርብዙ መከራ እየተቀበሉ አምልኮተ ጣኦትን እያጠፉ ወንጌልንሰብከዋል ለዚህም ነው በወንጌላዊው በማርቆስ የተመሰሉት።የአባታችንን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ትሩፋትንና ገድልንአልመስከር ለኢትዮጵያ ምድር ከቶ አይሆንላትም በምድሪቱ ላይየተከተቡ የታሪክ አሻራዎች በሙሉ አባ ተክለ ሃይማኖት አባተክለሃይማኖት እያሉይጮሃሉና።
ይቆየን
0 comments:
Post a Comment