• በቅርብ የተጻፉ

    Friday, 13 November 2015

    ‹‹የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡››(ምሳ 10፡7)


    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱአምላክ አሜን

    ከአብነት ተስፉ(AbinetZetewahido4@gmail.com)

    መግቢያ፡- ውድ የዳረጎት ዘተዋህዶየጡመራ መድረክ አንባቢያን ሆይ በቅዱሳን ሁሉአንደበት ያለች የእግዚያብሄር ፍጹም ሰላምከሁላችሁ ጋር ትሁን እያልኩኝ እግዚያብሄር እንደረዳን መጠን ‹‹የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው››(ምሳ 10፡7) በሚለው የጠቢቡ ሰለሞን ቃልበተከታታይ ክፍሎች እንማማራለን፡፡ እኔን ደካማውንየእግዚአብሔር  ብላቴና እጄን ከጥበብ ጋር ወደብዕር እንድልክ ለእናንተም የማንበብ ትዕግስትንእግዚአብሔር እንዲያድለን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡

    እነሆ ጽሁፌን በመግቢያጀመርኩኝ፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን አስቀድሞየፈጠረ ፈጣሪ፣ ከዓለም በፊት የነበረ ቀዳማዊነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን የሚያይ እንጂ የማይታይረቂቅ፣ ሁሉን የሚመረምር እንጂ የማይመረመርስውር ነው፡፡ መላዕክት እንኳን ራሳቸው ረቂቅ ሆነውሳሉ እርሱ ግን ከረቂቅም ረቂቅ፤ እምረቂቃን ነውናየልብሱን ዘርፍ እንኳን አላዩትም፡፡ በመሆኑምዘወትር ‹‹ምን ይመስል ይሆን?›› እያሉ በአንክሮበተዘክሮ ሆነው በተሰጣቸው ህሊና ጥልቁን ቀላይንይመረምራሉ፡፡ ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉምአይችሉምም ነበር፡፡ እርሱ የሰውና የመላዕክትአእምሮ በማይደረስበት በጨለማ የተሰወረ ነውና፡፡ሆኖም ሠዐቱ ሲደርስ ቀድሞ በህሊናው አስቦየነበረውን የሰው ልጅ በመፍጠር መልኩን ሊገልፅአሰበና እግዚአብሄር አዳምን (መልኩን) ኤልዳበምትባል ቦታ ፈጥሮ ለመላዕክት አሳያቸው፡፡መላዕክትም ‹‹እግዚአብሄር ሰውን ይመስላልኮ…!!››ብለው ክብሩን በይባቤ ከፍ ከፍ አደረጉት፡፡የፈጠረው የሰው ልጅ እውነተኛ የእግዚአብሔር መልክነቱን ይዞ መቆየት ተሳነውና በሀሳዌ ስብከተከይሲ ዲያቢሎስ ተታሎ ህሊናውን አጎደፈ፡፡በዚህም የሰው ዘር በሙሉ እግዚአብሔርንመምሰል በመልክ እንጂ በልቦና መምሰልተስኖአቸው ቀሩ፡፡ ነገር ግን በተለያዩ ዘመናት ውስጥአንዳንድ ጥቂት የእግዚአብሔር  ምሳሌዎችአልጠፉም፡፡ ምክንያቱም የተመረጡ ጥቂቶችናቸውና፡፡ እነዚህም ቅዱሳን ፃድቃን ናቸው፡፡እነዚህቅዱሳን በልዩ ልዩ መልክ እግዚአብሔርን መሰሉት፡፡በባህሪው ንፁህ እንደሆነ እራሳቸውን ከሃጥያትበማራቅ እግዚአብሄርን መሰሉት፡፡ ‹‹እኔ ቅዱስእንደሆንኩኝ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ››(ዘሌ 14፡2)የሚለውን ቃሉን እንደሚገባ ፈጸሙት፡፡ ‹‹እስከ ሞትድረስ የታመንክ ሁን፡፡››(ራዕ 2፡10) ይላልናህይወታቸውን እንኳን እሳልፈው ሰጡት፡፡በአጠቃላይ እግዚአብሔር ፍፁም እንደሆነ ፍፁማንሆነው አምላካቸውን መሰሉት፡፡(ማቴ 5፡48) ይህንንተከትሎ መልካም ላደረገ ሽልማት ይገባዋልና የርሱየሆኑትን ነገሮች ሰጣቸው፡፡ እርሱ በባህርይ ቅዱስእንደሆነ እነርሱን በፀጋ ቅዱሳን አደረጋችው፡፡ እርሱበባህርይ ብርሃን አንደሆነ እነርሱን በፀጋ ብርሃንአደረጋቸው፡፡ እርሱ በባህርይ ከፍ ከፍ እንደሚልእነርሱን በፀጋ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡‹‹በስምህ ቀኑንሁሉ ደስ ይላቸዋል፡፡ በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፡፡››(መዝ 88 (89)፡16) እንዲሁም በአጋንንት ላይ እናበበሽታዎች ላይ በአህዛብም ላይ ስልጣንንሰጣቸው፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገውበእምነት ጉልበት ድውይን ፈወሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣አጋንንትን አስወጡ፣ በክርስቶስ ወንጌል ለአህዛብህይወትን ሆኑ፡፡ ምክንያቱም ‹‹እውነት እውነትእላችኋለሁ፡፡ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ስራእርሱ ደግሞ ያደርጋል፡፡ ከዚህም የሚበልጥያደርጋል፡፡››(ዮሐ 14፡12) ይልላቸዋልና ቃሉ ፡፡በዚህም ክርስቶስ ሙትን በእጁ ዳስሶ እንዳስነሳእነርሱ በጥላቸው አስነሱ፡፡ እርሱ በውሃ ላይ እንደተራመደ እነርሱ በእርሱ መንፈስ በደመና ላይተራመዱ፡፡ በዚህም አንዳንዶች ባለማወቅመስዋዕት እንሰዋላችሁ እስኪሉ ድረስ ክብራቸውከፍ ከፍ አለ፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ እግዚአብሔርስለ ተጋድሎአቸው በሰዎች መታሰቢያ በዓልእንዲደረግላቸው አዘዘ፡፡

    ውድ የዳረጎት ዘተዋህዶ ቤተሰቦችሆይ በተከታታይ ጽሁፎቻችን መታሰብያ ምንድንነው? ቅዱሳን በምን ይታሰባሉ? እንዴት ይታሰባሉ?የመታሰቢያ ጥቅሙ ምንድን ነው? ከዚሀ ጋርበተያያዘ ለቅዱሳን ስለተሰጠ ቃልኪዳንእግዚአብሔር እንደ ፈቀደ መጠን እንዳስሳለን፡፡የእግዚአብሔር  አብ ጸጋ የእግዚአብሔር  ወልድቸርነት የእግዚአብሔር  መንፈስ ቅዱስ አንድነትከሁላችን ጋር ይሁን!!!!

    ወስብሃት ለእግዚአብሔር

    ወለወላዲቱ ድንግል

    ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን!!!!!አሜን

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ‹‹የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡››(ምሳ 10፡7) Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top