• በቅርብ የተጻፉ

    Monday 9 November 2015

    አቡነ ዘርዓ ብሩክ


    አትሮንስ - የዲያቆን ንጋቱ አበበ ገጽ: The አቡነ ዘርዓ ብሩክ የጻድቁ አባታችን የዘርዓ ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩየአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች ጻድቁአባታችን ገና በናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሄር መርጡአቸዋልናበሁአላም ከክርስቶስ ልደት በሁአላ በስምንተኛው መቶ /ዘመን መጨረሻ ላይ በነሃሴ 27 ጻድቁ አባታችንተወለዱ 40 ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩእድገት አሳደጉአቸው 7 አመትም በሞላቸው ግዜ

    በልጅነቴ የዚን አለም ክፋቱን እንዳላይ ብለው ቢጸልዩ አይናቸው ታውሩአል:: ቤተሰቦቻቸውም የዚህን አለም ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል።

    የእግዚአብሄር ፈቃድ አይደለምና ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውንእውቀት ፈጣሪ አምላክ ራሱ ገልጾላቸዋል:: ክህነትን እስከጵጵስና እራሱ መድሃኒአለም ክርስቶስ ሰቶአቸዋል:12 አመትምበሞላቸው ግዜ አይናቸው በርቶላቸው ታላላቅ ተጋድሎንማድረግ ጀመሩ። የሃጥያት ማሰርያን ያስሩና ይፈቱ ዘንድጵጵስናን በሾማቸው ጊዜ እግዚአብሄር ያወጣላቸው ሁለተኛስም "ዘርዓ ብሩክይባል ነበር።

     3ኛውም ስማቸው ደግሞ "ጸጋ ኢየሱስይባላል:: ጻድቁአባታችን በዚህ ዓለም በህይወተ ስጋ ሳሉ አቡቀለምሲስእንደሚባል እንደ ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ እግዚአብሔር እሱወዳለበት ወደ ሰማይ አውጥቶ በገነት መካከል ያኖራቸው ነበር

    እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጁ ለብጹዕ አባታችን ዘርዓ ብሩክበጎ ነገር እንዳደረገላቸውና ያለ ድምጽ የሰማይ ደጆችን አልፎ የእሳት ባህርን ተሻግሮ ፈራሽ በስባሽ ሲሆን እንደህያዋን መላእክት በፍጥነት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአድማስ እስከ አድማስ ይደርስ ዘንድ 12 ክንፍን ሰጣቸው።

    መላእክትም ለሌሎች ቅዱሳን ያልተሰጠ ይህንን ስልጣን አይተው ለምድራዊ ሰው ይህ ነገር እንዴት ይቻላል?እያሉ አደነቁ። ከዛም በኋላ ጻድቁ አባታችን ከፈጣሪ ዘንድ የመላእክትን አስኬማ የሾህ አክሊል አምሳያ የሆነውንመንፈሳዊ ቆብን ሰማያዊ ቅናትን እና የደረት ልብስን (ስጋ ማርያምተቀብሎ በጾም እና በጸሎት በልመና እናበስግደት እግዚአብሄርን ሲያገለግል ኖረ። ከዛም በላይ ወንጌልን እጅግ ብዙ በማስተማር ደከመ።

    ከኢትዮጵያም አልፎ ግብጽ ድረስ ገባ። የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳ አባ ዮሐንስን አገኘውና እርስ በርስሰላምታን ተለዋውጠው፤ እጅ ተነሳሱ።

     ከዛም ተመልሶ ወደ ሃገሩ መጣ፤ ከዛም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመላለሰ ወንጌልን አስተማረ እጅግ ሥጋንበሚያስጨንቅ ትጋትም የኢትዮጵያን ህዝብ ማርልኝ እያለ እያለቀሰ ይጸልይ ነበር።  

    አንድ ቀን አባታችን በንጉስ ጭፍሮች ተይዘው ሲሄዱ ዳዊታቸውን ለግዮን ወንዝ አደራ ሰተዋት ዓመትበሁአላ ሲመለሱ ግዮን ሆይ ዳዊቴን ግሺ መልሺሊን ቢሉአት አንድም የውሃ ጠብታ ሳይኖርባት ዳዊታቸውንብትመልስላቸው ለደቀ መዝሙራቸው ዘሩፋኤል አሳዩትና ግዮንንም "ግሽ አባይብለውታል እስካሁንምበዚሁ ስም የሚጠራው ከዚ በመነሳት ነው:: ከዚህም ሌላ ጻድቁ አባታችን በዚሁ ወንዝ አካባቢ  30 አመትሲጸልዩ ፈጣሪ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ እጅግ ልዩ የሆነ ቃል ኪዳን ሰቶአቸዋል:በስተመጨረሻምየሚያርፉበት እለት በደረሰ ሰአት መልአከ ሞት መቶ እስኪደነግጥ እና ወደ ሁአላው እስኪያፈገፍግ ድረስ ነውነው እግዚአብሄር ጸጋውንና ክብሩን ያበዛላቸውበስተመጨረሻም ጥር በገባ 13 ቀን 482 አመታቸውስጋቸው ከነፍሳቸው ተለይታ ገነትን ወርሰዋል:: 

    ለእግዚአብሔ ምስጋና ይሁን እኛንም በኚህ ጻድቅ ጸሎትይማረን በረከታቸውንም ያድለን አሜን!!!

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: አቡነ ዘርዓ ብሩክ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top