የገንዳ ውኃ ደ/ገ/ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስቲያ ን የመረጃ ገጽ: ሰንበት ት/ቤትNov 20, 2012
እንኳንለመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊታላቅ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!!!!
ድርሳን ዘቅዱስ ሚካኤል (እም ቅዱስ መጽሐፍ)
ቅዱስማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤልማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደእግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤልየሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ -የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ»ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ»ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልንስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለእግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርንበባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንምየሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለየሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡንያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትንአምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥«አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክትከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድምአማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናትመካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንምዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። ዘጸ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክትየሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ ፹፭፥፰።
፩፥፩፦«ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?» መሳ፲፫፥፲፯
የእስራኤልልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉበመሥራታቸው፥ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያንእጅ ለአርባ ዓመት አሳልፎ ሰጥቷቸው ነበር.። በዚህዘመን ከዳን ወገን ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፥ሚስቱም መካን ስለነበረች ልጅ አልወለደችምነበር። የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦእንደምትፀንስ፥ ወንድ ልጅም እንደምትወልድ፥ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔርየተለየ ናዝራዊ እንደሚሆን ነገራት። የሚያሰክርመጠጥ እንዳትጠጣ፥ የረከሰም ነገር እንዳትበላ፥በልጁም ራስ ላይ ምላጭ እንዳይደርስ (ፀጉሩንእንዳትላጨው) አስጠነቀቃት። እርሷም ተመልሳየሆነውን ሁሉ ለባሏ ነገረችው፤ «የእግዚአብሔርሰው ወደ እኔ መጣ፥ መልኩም እንደ እግዚአብሔርመልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትምእንደመጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙንአልነገረኝም፤» አለችው።
ማኑሄም፥«ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላክኸውየእግዚአብሔር ሰው እባክህ እንደገና ወደ እኛይምጣ፤ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንደምናደርግያስገንዝበን፤» ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።እግዚአብሔርም የማኑሄን ቃል ሰማ፤የእግዚአብሔርም መልአክ በእርሻ ውስጥ ሳለችእንደገና ወደ ሴቲቱ መጣ፥ እርሷም ፈጥና ባሏንጠራችው፥ «እነሆ፥ አስቀድሞ ወደ እኔ የመጣው ያሰው ደግሞ ተገለጠልኝ፤» ብላ ነገረችው።እርሱም፦ «ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን?»ብሎ ቢጠይቀው «እኔ ነኝ፤» ሲል መለሰለት።ማኑሄም፦ «እነሆ ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ነገር፥ግብሩስ ምንድነው?» ብሎ ዳግመኛ ጠየቀ።መልአኩም ለሴቲቱ ነግሯት የነበረውን ሁሉ መልሶነገረው። ማኑሄ ለመልአኩ የፍየል ጠቦትለማዘጋጀት ቢፈልግም፦ «አንተ የግድ ብትለኝእህልህን አልበላም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕትብታደርግ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤» አለው።ምክንያቱም ቅዱሳን መላእክት ቅድሚያ የሚሰጡትለእግዚአብሔር ክብር ነው። እነርሱን ግንእግዚአብሔር ራሱ እንደሚያከብራቸውእንደሚያስከብራቸውም ያውቃሉ። ማኑሄየተገለጠላቸው የእግዚአብሔር መልአክ እንደሆነአላወቀም፥ ሚስቱም አላወቀችም። በመሆኑም፦«ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማንነው?» በማለት ጠየቀው። የእግዚአብሔርምመልአክ፥ «ስሜ ድንቅ ነው፥ ለምን ትጠይቃለህ?»ብሎታል። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉንቊርባን በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበ።መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱምይመለከቱ ነበር። ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክበመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፥ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርምበግንባራቸው ወደቁ። (ሰገዱለት)። ይህ መልካምየምሥራችን የተናገረ፥ የተለያዩ ተአምራትን ያደረገ፥መሥዋዕታቸውንም ወደ ሰማይ ያሳረገ፥የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው።ሚካኤል ማለት በሁለተኛ ትርጉሙ«የእግዚአብሔር ነገሩ ዕፁብ ድንቅ ነው፤» ማለትነውና። መሳ ፲፫፥፩-፳። በዚህም የስሙ ትርጓሜነገረ እግዚአብሔር መሆኑን እንረዳለን።
፩፥፪፦የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፤ ኢያ ፭፥፲፬
ከነቢያትአለቃ ከሙሴ በኋላ በእርሱ እግር ተተክቶየእግዚአብሔርን ሕዝብ የመራው ኢያሱ ነው።የመረጠውም ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው።እግዚአብሔርም፦ «በሕይወትህ ዘመን ሁሉየሚቋቋምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደነበርሁእንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ አልጥልህም፥ ቸልምአልልህም፤» ብሎታል። ኢያ ፩፥፭። ይህእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነለት ታላቅ ሰውኢያሱ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነትአስፈልጐታል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእርሱጋር ለመሆኑ ምልክቱ ቅዱሳን መላእክት ናቸውና።እግዚአብሔር ባለበት ቅዱሳን መላእክት አሉ፥ቅዱሳን መላእክትም ባሉበት እግዚአብሔር አለ።ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስበተወለደባት ሌሊት የምሥራቹን «እነሆ፥ ለእናንተናለሕዝቡ ሁሉ ደሰታ የሚሆን ታላቅ የምሥራችእነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማመድኃኒት ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታክርስቶስ ነው።» በማለት ለእረኞች የነገሯቸውቅዱሳን መላእክት ናቸው። እረኞቹም፦ «እስከቤተልሔም እንሂድ፥ እግዚአብሔርም የገለጠልንንይህን ነገር እንወቅ፥ አሉ።» ሉቃ ፪፥፮-፲፭። በዚህምቅዱሳን መላእክት የገለጡላቸውን ምሥጢርእግዚአብሔር ገለጠልን ብለዋል።
ኢያሱወልደ ነዌ፥ ሕዝቡን እየመራ በኢያሪኮ አጠገብሳለ ዐይኑን አንሥቶ ቢመለከት እነሆም የተመዘዘሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ። ወደእርሱም ቀርቦ «ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችንወገን ነህን?» አለው። እርሱም «እኔ የእግዚአብሔርሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ፤»ብሎታል። ኢያ ፭፥፲፫-፲፭። የእግዚአብሔር ሠራዊትየሚባሉት ቅዱሳን መላእክት ናቸው። «ያዕቆብምመንገዱን ሄደ፥ በዓይኖቹም የእግዚአብሔርንሠራዊት ከትመው አየ፥ የእግዚአብሔር መላእክትምተገናኙት። ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ እነዚህየእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው አለ፤» ይላል። ዘፍ፴፪፥፩-፪። ቅዱስ ዳዊትም፦ «ሠራዊቱ ሁሉ፥ፈቃዱን የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርንያመሰግኑታል፤» ብሏል። መዝ ፩፻፪፥፳፩።የእነዚህም (የእግዚአብሔር ሠራዊት) አለቃቸውቅዱስ ሚካኤል ነው። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስይሁዳ «የመላእክት አለቃ ሚካኤል» በማለትመስክሮለታል። ይሁዳ ፩፥፲፪።
፩፥፫፦ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉት፤ ራእ፲፪፥፯
ቅዱስዮሐንስ ወንጌላዊ በደሴተ ፍጥሞ በግዞትሳለ በተመለከተው ራእይ ሃላፊያትና መጻእያትተገልጠውለት ስለነበረ፥ «በሰማይም ሰልፍ(ጦርነት) ሆነ፤» ካለ በኋላ «ሚካኤልና መላእክቱምዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም ከነሠራዊቱተዋጋቸው። አልቻላቸውምም፥ ከዚያም በኋላበሰማይ ቦታ አልተገኘላቸውም። ዓለሙን ሁሉየሚያስተው ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፥ ወደምድርም ተጣለ፥ መላእክቱም (የዘንዶው ሠራዊት)ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤» ብሏል። ራእ ፲፪፥፯-፱።
ታሪክ፦ሰይጣን በክህደቱ አጥቶት እንጂ ክብርም ፥ኃይልም፥ ሥልጣንም ነበረው። በአሥሩ የመላእክትከተሞች በተሾሙ አሥር የመላእክት አለቆች ላይየአለቃ አለቃ ነበረ። የተፈጠረው የመላእክት አለቃሆኖ ነው። ይኽንንም ቀሌምንጦስ ተናግሮታል።እግዚአብሔር መላእክትን በነገድ መቶ ፥ በከተማአሥር አድርጐ ፈጥሮ ተሰወራቸው። ይህምካልፈለጉኝ አልገኝም ፥ ባሕርዬም አይመረመርምሲላቸው ነው። ወዲያው፦ «እኛ ምንድር ነን? ከየትመጣን ? ማንስ ፈጠረን? በራስ በራሳችን ተፈጠርን? ወይስ ከሌላ ነው?» አሉ። ሳጥናኤል ከበታቹእንዲህ ሲሉ ሰማ። ከበላዩ ደግሞ «ፈጠርኳችሁ፤»የሚል አጣ። በቦታው ከሁሉ በላይ አድርጎ ፈጥሮትነበርና «እኔ ፈጠርሁ፤» ብሎ አሰበ ፥ አስቦም አልቀረ«እኔ ፈጠርኋችሁ፤» አለ። ይኽን ሰምተው «ሰጊድይገባዋል፤» ያሉ አሉ። «እኛም እንደ እርሱ ነን፤»ያሉም አሉ። « አምላክ ነኝ ያለስ ከእርሱ በቀር ሌላየለምና ፥ ይሆንን?» ብለው የተጠራጠሩ አሉ።ሀልዎተ እግዚአብሔርን ሳይመረምሩ የቀሩም አሉ።እኲሌቶቹ ግን ፦ «በምን ፈጠርኋችሁ ይለናል፥በቦታ ከበላይ በመሆን ፈጠርኋችሁ እንዳይለን ፥ እኛየበታቾቻችንን መቼ ፈጠርናቸውና ነው?። በዚያውስላይ ምቀኞቹ አይደለንም፤ በእውነት ፈጣሪ ከሆነፈጥሮ ያሳየን ።» ብለው፦ «ፈጥረህ አሳየን፤»አሉት። እርሱም እፈጥራለሁ ብሎ ፥ እጁን ወደ እሳትቢጨምር ፈጀውና « ዋይ» አለ። በዚህን ጊዜ«በአፍአ ያለውን (የሚነገረውንና እና የሚሠራውንብቻ የሚያውቅ) አምላክ ቢሆን ነው እንጂውሳጣዊውን (ልብ ያሰበውን የሚያውቅ) አምላክቢሆን ኖሮ ገና ሳስበው ለምን አሰብከው ፥ ባለኝነበር ፤» አለ። ወዲያው ልቡን ተሰማውና «ዋይ»አለ። እግዚአብሔር ግን ፈወሰው። ይህንንምማድረጉ ንስሐ ቢገባ እንደሚምረው ሲነግረውነበር።
ከዚህበኋላ በመላእክት ሽብር ቢጸናባቸው፦መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል፦ «ንቁምበበህላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ ፤ አምላካችንንእስክናገኘው ድረስ በየህልውናችን ጸንተን እንቁም፤» በማለት አጽንቷቸዋል። ይህም በጎ አርበኛ ጦርበተፈታ ጊዜ «አይዞህ ባለህበት ጽና፤» ብሎእንደሚያጸናው ማለት ነው።« ወበእንተዝ ደለዎይፁር ዜናሃ ለማርያም ፤ በዚህ ምክንያት የድንግልማርያምን ዜና ያደርስ ፥ ብሥራቷን ይናገር ዘንድተገባው ፤ » እንዲል ፥ ብሥራት ተሰጥቶታል።«በስድስተኛው ወር (አምስት ሺህ አምስት መቶዘመን ሲፈጸም ፥ ስድስተኛው ሺህ ደግሞ ሲጀምር)መልአኩ ገብርኤል . . . ወደ አንዲት ድንግል ተላከ»ይላል። ሉቃ ፩፥፳፮።
እግዚአብሔርምጨርሶ ሳያስታቸው ብሎ እርሱ(ሳጥናኤል) በሌለበት በኲል በምሥራቅ ባሕረብርሃንን አፍስሶላቸዋል። ከዚህም ጋር ስሙየተጻፈበት መጽሔተ ብርሃን ቢሰጣቸው አንድነቱሦስትነቱ(ምሥጢረ ሥላሴ) ተገልጦላቸው « አሐዱአብ ቅዱስ ፥ አሐዱ ወልድ ቅዱስ ፥ አሐዱ ውእቱመንፈስ ቅዱስ፤» ብለው አመስግነውታል። እርሱንግን ባደረው ጨለማ ጠቅልሎ በዕለተ እሑድከኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወደ ኢዮር አውርዶታል።ከሰባቱ ሰማያት ሦስቱ ፦ ኢዮር ፥ራማ፥ ኤረርየመላእክት ናቸው። በውስጣቸውም አስርየመላእክት ከተሞች አሉ። በእነርሱም ላይ አስርአለቆች ተሹመዋል። እግዚአብሔር ሳጥናኤልበሌለበት በኲል ባሕረ ብርሃንን ያፈሰሰላቸው «እኔፈጠርኩ » እንዳይል ነው።
ሳጥናኤልበኢዮር ሆኖ በዕለተ ሠሉስ የተፈጠሩዕፅዋት፥ አዝርዕት ፥ አትክልት ፥ጽጌያትን አይቶእንዳያደንቅ፦ «እንዲህ አድርጐ አከናውኖየፈጠረለት ቢኖር ነው፥ » አለ። እግዚአብሐርም«ከወደድሃት በዚያ ላኑርህ ፤» ቢለው «ደገኛይቱንማን ከልክሎኝ ፤» አለ። ከዚህ በኋላ ለሚካኤልናለገብርኤል «እናንተ ኢየሩሳሌም ሰማያት ይሏችኋል፥ ሰባቱ ሰማያት እንኳ አያህሏትም። እኛ ከጩኸትበቀር የተጠቀምነው የለም። ገዢ ነኝ የሚለውንወግተን እጅ እናድርግ።» ብሎ ላከባቸው። እነርሱምየተላኩትን ከንጉሥ ከተማ እንደገባ ዕብድ ውሻአድርገው ሰደዷቸው። ተመልሰውም አልተቀበሉንምቢሉት ፦ «ቀለምጺጸ እሳት (የእሳት ፍንጣሪ) የሆኑሚካኤል ገብርኤል በእኔ ዘንድ ምን ቁም ነገርናቸው። ይልቁንስ ኑ ተሸከሙኝና እንሂድ ፤»አላቸው። በዚህን ጊዜ በአርባዕቱ እንስሳ(በኪሩቤል) አምሳል አራት ሁነው ተሸክመውትሽቅብ እወጣለሁ ቢል ኃይል ተነሥቶታል። ወደ ታችእንጂ ወደ ላይ መውጣት የማይቻለው በመሆኑም፦ «ጐየ እግዚእ ምስለ አርያሙ፤ እግዚአብሔርሰማዩን (ጽርሐ አርያምን) ጠቅልሎ ሸሸ፤» ብሎተመለሰ።
ቅዱሳንመላእክት ግን ፍጥረትን ሲፈጥር እያዩያመሰግኑ ነበር። በዕለተ ረቡዕ ፀሐይ ፥ ከዋክብት ፥ጨረቃ ፥ ሲፈጠሩ አይተው አመስግነው አመስግንቢሉት ፦ «አንሰ ዕድው (ውፁዕ) እምዝንቱ ኅሊና፤»እንዲል፦ «እኔ ከዚህ ውጪ ነኝ ፥ ባይሆን አራተኛአድርጋችሁ ብታመሰግኑኝ እወዳለሁ፤» አላቸው።እነርሱም «ይህ ስሑት ፍጥረት እንዲህ እያለ እስከመቼ ሲታበይ ይኖራል?» ብለው ሄደው ቢገጥሙትድል አደረጋቸው። ሁለተኛም ቢገጥሙት ዳግመኛድል አደረጋቸው። በዚህን ጊዜ፦ «እኛስለአምላክነትህ ቀንተን ነበረ ፥ አንተ ግን ፈቃድህሳይሆን ቀረ፤» ብለው ወደ እግዚአብሔርቢያመለክቱ ፦ «ፈቃዳችሁ ፈቃዴ ነው ፥ ነገር ግንድል የሚነሣበትን (የሚሸነፍበትን) ታውቁ ዘንድነው፤» ብሎ ስሙ የተጻፈበትን ትእምርተ መስቀልሰጣቸው። ያን ይዘው በዕለተ ረቡዕ ወደዚህ ዓለምአውርደውታል። በዚህን ጊዜ የእርሱ ወገኖችለሦስት ተከፍለዋል። ሀለዎተ እግዚአብሔርንሳይመረምሩ የቀሩ በአየር ቀርተዋል። ይሆን ፥አይሆን ብለው የተጠራጠሩ በዚህ ዓለምቀርተዋል። « አምላክ ነው ፥ ሰጊድ ይገባዋል፤» ያሉአብረው እንጦሮጦስ ወርደዋል።
፩፥፬፦ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ዳን ፲፪፥፩
ቅዱስሚካኤል ለእግዚአብሔር መንጋ እረኛቸውነው። ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት፦ በመዝ ፴፫፥፯ላይ «የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት (ፈሪሃእግዚአብሔር ባላቸው) ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥(ይከትማል፥ የእሳት አጥር ይሆናል)፥ያድናቸውማል፤» እንዳለ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስሚካኤል በተለይም በፍጻሜ ዘመን ከሚመጣውመከራ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያድናል። ይህምሥጢር የተገለጠለት ነቢየ እግዚአብሔርዳንኤል፦ «በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆችየሚቆመው (በአማላጅነት በተራዳኢነትየሚቆመው) ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፥ሕዝብም በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ዘመንድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመንይሆናል፤» ብሏል። ዳን ፲፪፥፩። በዚህም፦ ገናናመልአክ፥ የመላእክት አለቃ፥ አማላጅና ተራዳኢመሆኑን መስክሮለታል። ስለዚያች ቀን፥ ጌታችንአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥«ያንጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዛሬያልተደረገ፥ ከእንግዲህም ወዲያ የማይደረግ ታላቅመከራ ይሆናል፤» ካለ በኋላ፥ «መላእክቱንምከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥የተመረጡትንም ከሰማይ ዳርቻ እስከ ዳርቻውከአራቱ መዐዝን ይሰበስቧቸዋል።» ብሏል። ማቴ፳፬፥፳፩-፴፩። ቅዱስ ዮሐንስም ስለ ሓሳዊ መሲሕዘመን ተገልጦለት፥ «ከዚህ በኋላ ሌላ አውሬከምድር ሲወጣ አየሁ፤ . . . ለአውሬውም(ለፊተኛው አውሬ) ምስል ያልሰገደውን ሁሉእንዲገደሉ ያደርጋቸዋል፤» ብሏል። ራእ ፲፫፥፲፩፣፲፭። እንግዲህ የዚህን ክፉ ዘመን መከራ ሥጋለባሽ የሆነ ሁሉ ስለማይቋቋመው የመላእክት አለቃየቅዱስ ሚካኤልና የሠራዊቱ ተራዳኢነትአስፈልጓል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፦«መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለምሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስይላኩ የለምን?»ያለው ለዚህ ነው። ዕብ ፩፥፲፬።
፩፥፭፦ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝመጣ፤ ዳን ፲፥፲፫
ነቢዩዳንኤል፥ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በሦስተኛውዓመተ መንግሥት በራእይ ምሥጢር ተገልጦለታል፥ነገሩም ከእግዚአብሔር በመሆኑ ምሥጢር ነበረ፥ታላቅ ኃይልና ማስተዋልም በራእዩ ውስጥተሰጥቶታል። ነቢዩ ዳንኤል ስለ ሕዝቡ ኃጢአትናሊመጣ ስላለው መከራ ሶስት ሳምንት ሙሉአዝኗል። (ጾም ጸሎት ይዟል)። ማለፊያ እንጀራአልበላም፥ ሥጋና የወይን ጠጅም በአፉ አልገባም፥ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ራሱን ዘይትአልተቀባም። ከልጅነቱ ጀምሮ ጾም ጸሎትን አጥብቆየያዘ ነቢይ ዳንኤል በራእይ የተገለጠለት ምሥጢረሥጋዌ ነው። «ዳንኤልም ከንጉሡ ማእድእንዳይበላ፥ ከሚጠጣውም ጠጅ እንዳይጠጣ ልቡጨከነ፥ እንዳያበላውም የጃንደረቦቹን አለቃለመነው፥ እግዚአብሔርም በጃንደረቦቹ አለቃ ፊትለዳንኤል ሞገስንና ምሕረትን ሰጠው። . . . ይህንምነገራቸውን ሰምቶ ዐሥር ቀን ፈተናቸው። ከዐሥርቀንም በኋላ ከንጉሡ ማዕድ ከበሉ ብላቴኖች ሁሉይልቅ ሰውነታቸው አምሮ ሥጋቸው ወፍሮ ታየ።አሚሳድም መብላቸውንና የሚጠጡትን ጠጅአስቀርቶ ጥራጥሬውን ሰጣቸው፤» ይላል። ዳን፩፥፰-፲፮።
በትንቢተዳንኤል ምዕራፍ ዐሥር ቊጥር ፲፫ ላይ፦«ዳንኤል ሆይ! አትፍራ፥ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድከአደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን (ኀዘን፥ ጾም፥ጸሎት ከጀመርክበት ዕለት) ጀምሮ ቃልህ (ጸሎትህ፥ምልጃህ) ተሰምቷል፥ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ።የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን በፊቴነበር። እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤልሊረዳኝ መጣ፥ እኔም ከፋርስ ንጉሥ ጋር በዚያተውሁት።» የሚል እናገኛለን። ይኽንንም የተናገረውየመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ነው። ነቢዩዳንኤል ጾም ጸሎት በሚይዝበት ጊዜ ዘወትር ወደእርሱ እንደሚመጣ «ገብርኤል ሆይ! ራእዩን ለዚህሰው ግለጥለት፤ . . . እኔም ገና ስናገርና ስጸልይ፥በኃጢአቴና በሕዝቤም በእስራኤል ኃጢአትስናዘዝ፥ በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ይቅርታን ስጠይቅ፥ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼውየነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ አየበረረ መጣ፥በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።» የሚል አብነትይገኛል። ዳን ፰፥፲፮፣ ፱፥፳።
ቅዱሳንመላእክት ሁልጊዜ ከዲያቢሎስና ከሠራዊቱጋር ይዋጋሉ፥ ያሸንፉማል። ቅዱስ ገብርኤል ወደነቢዩ ዳንኤል ሳይመጣ ለሶስት ሳምንት የዘገየበትንምክንያት ሲነግረው «የፋርስ መንግሥት አለቃ ግንሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤» ብሏል። ይህም በፋርስንጉሥና በሠራዊቱ ካደሩ አጋንንት ጋር ሲዋጋመሰንበቱን ያመለክታል። ይኸውም ዕለቱን ማሸነፍተስኖት ሳይሆን ሰይጣን ኢዮብን በከሰሰበትመንገድ እስራኤልን እየከሰሰ ቀኑን አዘግይቶበታል።ታላቁ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «ሰይጣንአዘገየኝ፤» ያለው ከዚህ ተመሳሳይ ነው። ቅዱስገብርኤል በሦስተኛው ሳምንት መጨረሻ ሊመጣየቻለበትን ምክንያት ሲናገር ደግሞ «ከዋነኞቹአለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፥ እኔምከፋርስ ንጉሥ ጋር በዚያው ተውሁት፤» ብሏል።በዚህም ቅዱሳን መላእክት እንኳ እርስ በርስእንደሚረዳዱ እንማራለን። ይህም ድካምተሰምቷቸው አንዳቸው የሌሎቹን እርዳታ ይፈልጋሉማለት ሳይሆን የአገልግሎት አንድነታቸውንየሚያጠይቅ ነው። ይህ እንዲህ ከሆነ እጅግ ደካማየሆኑ የሰው ልጆች የኃያላን መላእክት ተራዳኢነትእንዴት አያስፈልገንም ይላሉ? በተዋሕዶ ሰው የሆነአምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተከታዮቹ አብነትለመሆን በጌቴሴማኔ አጸድ በጸለየበት ጊዜ«የሚያበረታታው የእግዚአብሔር መልአክምከሰማይ ታየው፤» ይላል። ሉቃ ፳፪፥፵፫። እንግዲህእርሱንስ ምን ሊሉት ነው?
፩፥፮፦ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝማንም የለም። ዳን ፲፥፳፩
ሰይጣንሠራዊቱን አሰማርቶ በአሕዛብ ነገሥታትእያደረ የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባሉ እስራኤልንዘወትር በጦርነት ያስጨንቃቸው ነበር። በዚህምምክንያት ሲወድቁ ሲነሡ፥ ሲነቀሉ ሲተከሉ፥ሲፈርሱ ሲገነቡ፥ ሲበተኑ ሲሰበሰቡ፥ ሲሰበሩሲጠገኑ ኖረዋል። በዚያ ዘመን መጋቤ ብሉይ ተብሎየሚታወቀው ቅዱስ ሚካኤል ነው። እርሱም ዘወትርከቅዱስ ገብርኤል ጋር ሆኖ ሕዝቡን ይረዳቸውነበር። ይኽንንም «ወደ አንተ የመጣሁት ለምንእንደሆነ ታውቃለህን? አሁንም የፋርስን አለቃእዋጋው ዘንድ እመለሳለሁ፥ እኔም ስወጣ እነሆየግሪኮች አለቃ ይመጣል። (ሰይጣን በግሪክ ንጉሥአድሮ ሌላ ጦርነት ይጀምራል)። ነገር ግን በእውነትጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፥ በዚህም ነገርከአለቃችሁ (ከመላእክት አለቃ) ከሚካኤል በቀርየሚያጸናኝ የለም።» በማለት ቅዱስ ገብርኤልለነቢዩ ለዳንኤል ነግሮታል። ቅዱስ ገብርኤልእንዲህ ካለ እኛስ ምን እንበል?
፩፥፯፦በመላእክት አለቃ ድምጽ፥ በእግዚአብሔርምመለከት ከሰማይ ይወርዳል፤ ፩ኛ ተሰ ፬፥፲፮
ጌታችንአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስለጻድቃን ሊፈርድላቸው፥ በኃጥአን ሊፈርድባቸውዳግም እንደሚመጣ ቅዱሳት መጻሕፍት በመተባበርይመሰክራሉ። ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት፦«እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል። አምላካችንምዝም አይልም፥ (ይፈርዳል)፥ እሳት በፊቱ ይነድዳል፥በዙሪያውም ብዙ አውሎ አለ።» ብሏል። መዝ፵፱፥፫። ነቢዩ ዘካርያስም በበኲሉ የሚመጣውከቅዱሳን ሁሉ ጋር እንደሆነ ሲናገር፦ «አምላኬእግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣል፤» ብሏል።ዘካ ፲፬፥፮። በአዲስ ኪዳን ደግሞ ራሱ ባለቤቱኢየሱስ ክርስቶስ፦ «የሰው ልጅ (ወልደ ዕጓለእመሕያው) በጌትነቱ ቅዱሳን መላእክትን ሁሉአስከትሎ በሚመጣበት ጊዜ፥ ያንጊዜ በጌትነቱዙፋን ይቀመጣል፤» ብሏል። ማቴ፳፭፥፴፩። በዕርገቱጊዜም ቅዱሳን መላእክት ለደቀመዛሙርቱተገልጠው፦ «እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛይመጣል፤» ብለዋቸዋል። የሐዋ ፩፥፲፩። ሐዋርያውቅዱስ ጳውሎስ ስለ ትንሣኤ ሙታን ባስተማረበትትምህርቱ፦ «ወንድሞቻችን ሆይ፥ ስለ ሞቱ ሰዎች፥ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁእንወዳለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደተነሣካመንን፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስያስነሣቸዋል። ይህንንም በእግዚአብሔር ቃልእንነግራችኋለን፥ ጌታችን በሚመጣ ጊዜ ሕያዋንሆነን የምንቀር እኛ የሞቱትን አንቀድማቸውም።»ካለ በኋላ «ጌታችን ራሱ በትእዛዝ፥ በመላእክትምአለቃ ድምፅ፥ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይይወርዳልና፤» ብሏል። ፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫-፲፮። ይህየመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው። እንዲህእስከመጨረሻው ከጌታ የማይለየውን መልአክ«ለምን ስሙ ተጠራ?» ማለት ራስን ከጌታ መለየትነው።
፩፥፰፦የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሰይጣን ጋርተከራከረ፤ ይሁ ፩፥፱
የያዕቆብወንድም ይሁዳ፥ ቅዱስ ሚካኤልና ሰይጣንየተከራከሩበትን ምክንያት ሲናገር፦ «የመላእክትአለቃ ሚካኤል እንኳን ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋርበተከራከረ ጊዜ የስድብን ቃል ሊናገር አልደፈረም፥እግዚአብሔር ይገሥጽህ አለው እንጂ። እነዚህ ግንየማያውቁትን በመሳደብ ይበድላሉ፤» ብሏል። ይሁ፩፥፱። ቅዱስ ይሁዳ፥ በዘመኑ ላሉትም ሆነ እስከዓለም ፍጻሜ ለሚነሡት ተሳዳቢዎችእንደተናገረው፥ የመናፍቃን ሥራቸው፥ እንደ ግብርአባታቸው እንደ ዲያቢሎስ ቅዱሳንን መርገም ነው።
የነቢያትአለቃ ሙሴ ከዚህ ዓለም በሞትየሚለይበት ጊዜ ሲደርስ፥ ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስወጣ፤ እግዚአብሔርም የከነዓንን ምድር ካሳየውበኋላ፦«ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምናለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህችናት፤ እነሆም፥ በዐይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ነገር ግን ወደዚያች አትገባም፤» አለው።የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደእግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ።በቤተ ፌጎርም አቅራቢያ በናባው ምድር ቀበሩት፥እስከዛሬም ድረስ መቃብሩን ማንም የሚያውቅየለም። ዘዳ ፴፬፥፩-፯። የሙሴ መቃብር እንዴትሊታወቅ አልቻለም? የቀበረውስ ማነው?
ታሪክ፦እግዚአብሔር የሙሴን መቃብር ከእስራኤልሰውሮባቸዋል፥ የሰወረበትም ምክንያት ካላቸውጽኑዕ ፍቅር የተነሣ መቃብሩን እንዳያመልኩ ነው።አንድም የተቀበረበትን ቦታ ካወቁ ጧት ማታ እየሄዱከመቃብሩ ላይ እያለቀሱ ኀዘን እንዳይጸናባቸውብሎ ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ወደ ተራራውሲወጣ ሁለት መላእክት በአረጋውያን ተመስለውመቃብር ሲቆፍሩ አገኛቸው። መላእክት መሆናቸውንግን አላወቀም። «አክብር ገጸ አረጋዊ» የሚለውንሕግ ስለሚያውቅ «ላግዛችሁ፤» ብሎ መቃብሩንቆፍሮ ጨረሰላቸው። እነርሱም፦ «ልክ ይዘንአልመጣንም፥ ስለዚህ ሟቹ በግምት አንተንስለሚያክል ውስጡ ተኝተህ ለካልን፤» አሉት።እርሱም «እሺ፥በጀ፤» ብሎ ተኝቶ ሲለካ በዚያውነፍሱ ከሥጋው ተለይታ አርፏል። ከዚህ በኋላ አፈርመልሰውበታል። የሙሴ መቃብር በሰው ዘንድያልታወቀው በዚህ ምክንያት ነው።
እስራኤልዘሥጋ ከሞቱ ይልቅ የመቃብሩ መሰወርአሳዝኖአቸዋል። በዚህን ጊዜ የሰውን ችግርመግቢያ በር አድርጐ መግባት የሚያውቅበትሰይጣን ወደ ሕዝቡ የሚቀርብበትን ምክንያትአገኘ። ቀርቦም «ኑ፥ ተከተሉኝና የሙሴን መቃብርላሳያችሁ፤» አላቸው። እንዲህም ማለቱ ለእነርሱአዝኖላቸው ሳይሆን፥ የሚሆንለት መስሎት፥ በሙሴሥጋ አድሮ ሊመለክ ፈልጐ ነው። ሕዝቡም እውነትመስሏቸው ተከተሉት። በዚህ ቅጽበት የመላእክትአለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ ሰይጣንንተቃወመው። «በቅዱሱ በሙሴ ሥጋ ማደርአትችልም፥ እርሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነው፤»ብሎ ተከራከረው። በመጨረሻም ሦስት ጊዜ«እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤» ቢለው ሰይጣን እንደትቢያ ተበትኖ ርቆላቸዋል። ይህ የመላእክት አለቃቅዱስ ሚካኤል ፍላጐታችንን ምክንያት አድርጐባልሆነ መንገድ እንዳይመራን ሰይጣንንይቃወምልናል፥ ተከራክሮም ያሸንፍልናል ብለንእናምናለን። እንኳን በሕይወት እያለን ሞተንምበመቃብር ይጠብቀናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
፩፥፱፦በእስራኤል ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረውየእግዚአብሔር መልአክ፤ ዘጸ ፲፬፥፲፱
ከባርነትቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ፥እግዚአብሔር፦ ቀኑን በደመና ዓምድ፥ ሌሊቱንደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል። የግብፅንጉሥ ፈርዖን እስራኤልን «ሂዱ፤» ብሎ ከለቀቃቸውበኋላ መልሶ ስለጸጸተው ሠራዊቱን ይዞተከተላቸው። ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤልልጆች ዓይናቸውን አንሥተው ግብፃውያንሲከተሉአቸው አዩ፤ እጅግም ፈርተው ወደእግዚአብሔር ጮኹ። ምክንያቱም ሸሽተውእንዳያመልጡ ከፊት ለፊታቸው ያለው ባሕር ነው።በዚህ ላይ ፈርዖን ከነሠራዊቱ የተከተላቸው በፈረስበሰረገላ በመሆኑ ሸሽተውም ቢሆን ማምለጥአይችሉም። መሸሻ ሜዳ፥ መሸሎኪያ ቀዳዳ፥መመከቻ ጋሻ፥ መሸሸጊያ ዋሻ አልነበራቸውም።ሙሴንም፦ «በግብፅ መቃብር ስላልኖረ በምድረበዳ እንሞት ዘንድ አወጣኸንን? ከግብፅ ታወጣንዘንድ ይህ ያደረግህብን ምንድነው? በምድረ በዳከምንሞት ብንገዛላቸው ይሻለናልና፦ ተወን፥ለግብፃውያን እንገዛ፥ ብለን በግብፅ ሳለን ያልንህቃል ይህ አይደለምን?» አሉት። ሙሴም ለሕዝቡ«አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንንለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ (በእምነት ጽኑ)፤ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳንእዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተምዝም ትላላችሁ።» አላቸው። እግዚአብሔርምሙሴን፦ «ለምን ትጮኽብኛለህ? ከብቶቻቸውንእንዲነዱ ለእስራኤል ልጆች ንገር። አንተም በትርህንአንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም፥የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስያልፋሉ። እነሆም እኔ የፈርዖንን እና የግብፃውያንንልብ አጸናለሁ፥ በስተኋላቸውም ይገባሉ፤ በፈርዖንናበሰረገሎቹ፥ በፈረሰኞቹም ላይ እከብራለሁ።(ኃይሌን ገልጬ እመሰገናለሁ)። ግብፃውያንምበፈርዖንና በሰረገሎቹ፥ በፈረሰኞቹም ላይ ክብርባገኘሁ (ኃይሌን ገልጬ በተመሰገንሁ) ጊዜ እኔእግዚአብሔር እንደሆንሁ (ኃያልና ገናና ፈጣሪመሆኔን) ያውቃሉ፤» አለው። በእስራኤልም ሠራዊትፊት ይሄድ (ይመራቸው፥ ይጠብቃቸው) የነበረውየእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤(ከፈርዖንና ከሠራዊቱ በክንፈ ረድኤቱ ጋረዳቸው)፤የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎበኋላቸው ቆመ፥ በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤልሰፈር መካከልም ገባ፥ በዚያም ጭጋግና ጨለማነበረ፤ ሌሊቱም አለፈ፥ ሌሊቱንም ሁሉ እርስበርሳቸው አልተቃረቡም። ሲነጋም እግዚአብሔርአስቀድሞ እንደተናገረ በበትረ ሙሴ ላይ ኃይለእግዚአብሔር ተገልጦ ባሕረ ኤርትራ ለሁለትተከፈለ፥ ውኃው ግራና ቀኝ እንደ ግድግዳ ቆሞ፥እስራኤል በደረቅ ተሻገሩ፥ ግብፃውያን ሰጥመውቀሩ። ዘጸ ፲፬፥፩-፴፩።
እስራኤልዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው፥መና ከሰማይ ያወረደላቸው፥ ተአምራትንያደረገላቸው፥ ማርና ወተት ወደምታፈስሰውርስታቸው የመራቸው፥ በደመና መጋረጃየጋረዳቸው፥ በክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይየተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው። እኛንም ከዲያቢሎስናከሠራዊቱ ይጠብቀናል፥ ከአሽክላው ይሰውረናል፥ወደ ምድረ ርስት ገነት መንግሥተ ሰማያትይመራናል፥ ብለን እናምናለን። ኅዳር አሥራ ሁለትቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረውይኽንን ለእስራኤል ዘሥጋ የተደረገውን በማሰብነው። የበለጠው ደግሞ እስራኤል ዘነፍስ ለምንባልክርስቲያኖች ይደረግልናል።
የእግዚአብሔርቸርነት
የድንግልማርያም አማላጅነት
የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን አሜን።
0 comments:
Post a Comment