• በቅርብ የተጻፉ

    Friday 13 November 2015

    ጥንተ ስቅለት- መጋቢት 27፣ 34 ዓ.ም.


    የዛሬ አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት ዓመት በዕለተ ዓርብ መጋቢት 27 ቀን 34 ዓመተ ምሕረት (5534 ዓመተ ዓለም) የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው፡ ‹‹ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ›› (ማቴዎስ 27፡45) ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች፡፡ እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት፡፡ ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ፤ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች፤ በዚያ ጊዜ  ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር፡፡ እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋር አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ (1 ጴጥሮስ 3፡18-19)

    እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ፣ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሡን ሰውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል፡፡

    ለዘለዓለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር፤ አሜን፡፡

    (የመጋቢት 27 ቀን ስንክሳር )

    -       ሔኖክ መደብር

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ጥንተ ስቅለት- መጋቢት 27፣ 34 ዓ.ም. Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top