ከ በረከት ጉዲሳ(emush1988@gmail.com)
ሁለት ባለፀጋ ባል እና ሚስቶች በአንድ ጌታ ግዛት ውሰጥ በትልቅ ስልጣን ተሹመው ይኖሩ ነበር፡፡ እኚህ ሁለት ባለ ፀጎች እጀግ ጌታቸው አብልጦ የሚወዳቸው ፣የከበረ ቦታ ሰጥቷቸው በግዛቱ ላይ በበላይ ሲያስተዳድሩ የቆዩ ፣በዚህ ደግ ዘመናቸው ሁሉ ጌታቸውን በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ እናም ጌታቸው እጅግ ይወዳቸው የነበር ፣የሚፈልጉትን ሁሉ የሚያደርግላቸው እንደ ልጅም ስለ ሚመለከታቸው ካለው ሁብት ብቻ ሳይሆን ከእውቀቱም ጭምር የሚጠቅማቸውን እና እሚጎዳቸውን ነገር እየመከረ ከዛም አልፎ ተርፎ ሁሌ በሱ ድጋፍ ብቻ እንዳይቆሙ ከምክር እና ደጉን ነገር ከመጠቆም ውጪ ውሳኔ በራሳቸው እንዲወስኑ ያደርግ የነበር ጌታ ነበራቸው፡፡ በዚህ ሁሉ ፍቅር መሀከል በዚሁ ጌታ ግዛት የነበረ በጌታው ላይ በ ማመፁ ግን የተባረረ በፊት ግን የበላይ ገዢ የነበረ ስሙ በክፋት የተቀየረ ተንኮለኛ ከመሆነም በላይ የጌታውን ንብረት እና ስልጣን እሚፈልግ ስለ ነበር ክፋቱ ምንም በዝቶ ቢቀጣ በጀ ባለማለት ይባሱኑ ይህን ሀሳቡን ለማስፋፋት እና ለማራመድ ሲል ሌሎች የጌታውን ባለ ሟሎችን የሱን ሀሳብ በእነርሱ ለመፈፀም በማሰብ ይህን የክፋት ተንኮሉን ወደነዚህ ሁለት ባለ ፀጎች ይዞ ቀረበ፡፡
መጀመሪያ ለሀሳቡ መሳካት ከምን እንደሚጀምር ጠንቅቆ የቃልና ሀሰቡን ሲያቀርብላቸው በደካማ ጎናቸው ተጠቅሞ ጀመረ፡፡ ደግ የሚያስብላቸውን ጌታቸው መልካም ብሎ የመከራቸው ሁሉ ሰለነሱ ጥቅም እንዳልሆነ ይልቁንም እሱ የመከራቸውን ነገር ንቀው ቢያፈርሱ እንደሱ ጥበበኛ እንደሱ ገዢ እነደሚሆኑ ቢመክራቸው ልባቸው ያንን ነገር አብዝቶ ስለናፈቀ ጌታቸውን ምክር ንቀው በተንኮለኛው ምክር ተመርተው ከሱ ጋር ውል ፈርመው ምክሩን ቢቀበሉት ጌታቸው ይህንን ነገር ሰምቶ ከ ግዛታቸው አባረራቸው፡፡ ይህ የጥፋት ምክር እንደሆነ ግን ካለፈ በሁዋላ ቢገባቸው እርስ በርስ መተያየት ተፋፈሩ ስራቸው አሸማቀቃቸው ከ ባለጠግነት ተነጥለው በግዞት መኖራቸውን ሲያስቡ አለቀሱ፡፡ በለቅሶ ብዛት ከዱር ተቀምጠው ቢጨነቁ ከጌታቸው ባለ ሟሎች መካከል ለቅሶዋቸውን አይቶ አንድም የቀደመ ክብራቸውን አስታውሶ እንባ አየተናነቀው ወደነሱ ቀርቦ እንዲህ አላቸው፡፡
‹‹ ወዳጆቼ ያለፈው በደላቸሁ እንኩዋን ከ ጌታቸሁ ምን ያህል እርስ በርሳቸሁ እንደ አለያያቸሁ ተመልከቱ እሰቲ በዚህ ፍቅር መካከል የነፈሰው ንፋስ ያበላሸውን ነገር ዳግም ከ ይቅረታ ውጪ እሚመልሰው እሚጠግነው አለ ብላቸሁ ታስባላቸሁን? ድሮም ጌታቸሁ ከፍቅሩ የተነሳ ስራችሁን ሁሉ በናንተ ውሳኔ መሰረት እንዲከናወን ያደርግ ነበር፡፡ እኔም እምነግራቸሁ መልካሙን አውቃቸሁ በተሻለው መንገድ እንድትጉዋዙ በማሰብ ሰለሆነ ይቅርታ በመጀመርያ በሁለታቸሁ መካከል ይጀመር ከዛም የሁለታችሁን አንድነት በሚፈልግ በጌታቸሁ ፊት ቀርባቸሁ ይቅርታ ጠይቁ እኔ ጌቶችን እስከ ማውቃቸው ጊዜ ድረስ ሩሁሩህ ናቸው፡፡ በዛ ላይ በእናንተ ሳይሆን በስራቸሁ ስለተቀየሙ ዳግም ወዳጅ እነደምትሆኑ አልጠራጠርመም አደራ መልካሙን ነገር አድረጉ፡፡››
ብሎ ካጠገባቸው እያዘነ ሔደ፡፡ ባለሟሉ እንደመከራቸው እርስ በርስ ይቅር ተባባሉ ዳግምም በመሸማቀቅና በመንቀጥቀጥ ከ ጌቶች ዘንድ ቀርበው ይቅርታ ጠየቁ ፡፡ በመመለሳቸው ደስ ያለው ጌታቸውም ሰለ ጥፋታቸው በሱ ላይ ስለማመፃቸው እጅጉን ቢቆጣም በነፃ ፍቃዳቸው በወሰኑት ውሳኔ ክብራቸውን ቢገፍባቸውም ይቅርታ በሉኝ ሳይል በገዛ ፍቃዳቸው በመመለሳቸው የቀደመው በደላቸውን ሁሉ ተደምስሶ ክብራቸውና ብልፅግናቸው ይመለስላቸው ዘነድ 5 ቀን ተኩል ድረስ ባረፉበት አርፈው ይበልጥ መልካሙንና ደጉን እንዲቃኙ ዳግም ደግሞ ዝምድናው እንዲጠናከር በሰርግ ደግሶ መልሶ ወደ ክበራቸው እንደሚመልሳቸው ነግሮ ሰርጉም ከ5 ቀን ተኩል በኃላ ተቆረጠ፡፡
እነሱም ዳግም በዛች የጊዜ ገደብ ውስጥ በተስፋ እሚሆነውን ነገር ሁሉ ማየት ናፈቃቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሊዛመዳቸው እንደሆነ ዝምድናውን ወደ ስጋ ዝምድና ሊለውጠው እንዳሰበ ባወቁ ጊዜ እቺ 5ቀን ተኩል 5500 ዘመን ሆነባቸው፡፡ ይቅርታው ፍቅሩ ከልብ እነደሆነ እሚያውቁበት ቀን ያኔ ነበር፡፡ እናም እቺን ሰርግ እምትደረግበትን ቀን በተስፋ መጠበቅ ጀመሩ ሰርጉን ናፈቁ ድግሱን ለማየት ጓጉ የጌቶች ድግስ ማንም እንደመይደግስ ልቦናቸው ያውቀዋል፡፡ ለዚህ ነው ዓለም ጉድ እሚለው ተሰምቶ ታይቶ እማይታወቅ ድግስ ከዛም በሁዋላ ያንን የመሰለ ድግስ እንደማይደረግ በማመን ነበር ልባቸው የተንጠለጠለችው፡፡
ታዲያ በዚህ 5ቀን ተኩል ውሰጥ ያኔ ባስፈረማቸው ውል እየመጣ በነዚህ ባለፀጎች ላይ ያ ከሀዲ ያደርስ የነበረው ተንኮል ጌቶች ተመልክተዋል ይህ እንደሚፈጠርም አስቀድመው ያውቁታል፡፡ ምክንያቱም በሁለት ግልባጭ ጽፎ እንዳስፈረማቸው ጭምር ጌቶች ዘንድ ደረሶ ነበርና ነው፡፡ ለዚህም ዘዴውን ቀድመው ዘይደውት ነበርና ዝምድናቸውን የስጋ ዝምድና በማረግ በሁለቱ መካከል ጥብቅ የሆነ ትስስርን ፈጥሮ የዚን ባላጋራ ድብቅ ሴራ እና ወጥመዱን ብትንትኑን ማፍረስ መፍትሄ እንደሆነ ቀድመው አውቀውታል፡፡ ለዚህም የ5ቀን ተኩል እድሜ ያህል የተቆረጠለት፡፡
እናም እቺ ቀን መድረሱዋ አይቀርም ደረሰች የጌቶች ልጅ ተላከና ከ ከባለጠጎች ወገን ከነበረ ከዳዊት ቤት አደረ እነደ ባለጠጋነቱ ሙቀትና ድሎት ሳይል ዝቅ ብሎ በግርግም ልክ እንደነሱ ሆኖ ከመጥፎ ምግባራቸው እና ከድካማቸው ውጪ ልክ እንደነሱ ሆኖ ቀረበ ዝምድናውንም መሰረተ፡፡ ዳግም ግን በጌቶች እና በባለጠጎቹ መሀከል እየገባ የሚበጠብጠው ያ ተንኮለኛ ውሉን ያስፈረመበትን ሰነዶች ካስቀመጠበት መቀደድ ነበረባቸው ግና በዚህ 5ቀን ተኩል ውሰጥ እነሱ ሊቀዱት ያልቻሉትን አንድ ቀን ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዶ ከሁለቱ አንደኛውን ከተቀመጠበት ደርሶ ቀዶታል፡፡ አባቱም ሰለልጁ ተናገረ፡፡ በዚህም ተንኮለኛው መሰሪ ልቡ ደነገጠ ቢመለከተው የባለ ጠጋ ልጅ አይመስልም አለባበሱን ተመለከተ አረማመዱንም ቃኘ ፍንጭ አጣ ቢሆንም በልቡ ተጠራጣሪ ስለ ነበር ይፈትነው ዘንድ ፈተናውን ቀጠለ፡፡ ጌቶች ካዘጋጁት ሰርግ ውጪ ከባለጠጎቹ ወገን ሰርግ ተዘጋጅቶ የጌቶች ልጅ በቃና ዘገሊላ ተጋብዞ እሱም በሰርጉ ተገኘ ድንቅ ነገርም ለሰርገኞቸሁ አደረገ ይሄን የተመለከቱ በሙሉ ምነው ሰረጉን ተመልክተን ከሰረጉ በልተን ጠጥተን በሞትን ብለው አደነቁ፡፡ ፈተናውን ያላቋረጠው ተነኮለኛው መሰሪ ስለ ጥርጣሬው በዙ መከራን አደረሰበት የተጉዋጉዋለት ሰርግም ደረሰ ጥቂት ቀናትም ሲቀር የጌቶች ልጅ ሚዜዎቹን ሰበሰበ እና ትህትናን ሲያስተምራቸው ጎንበስ ብሎ እግራቸውን አጠበ መልካሙን ስራ በፀሎት እንዲጀምሩ ከሰርጉ በፊት ፀሎትን አስተማራቸው ደግሞም ከሰረጉ በፊት በሰርጉ እሚቀርበውን እውነተኛ እንጀራ ቆርሶ እንካቸሁ አላቸው፡፡
እሄንን ካደረገ በሁዋላ የከበረ ሰረገላ እንኩዋን ክብሩን የማይገልጥለት እርሱ በወታደሮች እየተገፋ ከሸንጎ ቀረበ ስለ ሰረጉ ተቃወሙት ምራቅም ተፉበት እሱ ግን በአባቱ ቤት ለእነዚህ ባሮቹ ቦታን ያስብላቸው ነበር፡፡ በንጋታው በ 3 ሰዓት ለሰርጉ መዳረሻ 6666 ጊዜ በላይ ተገረፈ፡፡ ያኔ ስለ ልጅነቱ እና ድንቅ ድንቅ ስራን በመስራቱ ዘንባባን ይዘው ዝቅ ብለው ሰርጉን በበላን ያኔም በሞትን እንዳላሉ ዛሬ ሰርጉ ደረሶ ዕጃቸውን ከፍ አድርገው ይሰቀል ብለው በዛው አንደበታቸው ተናገሩ፡፡ ቀለበት ለጋብቻ ምልክት እንዲሆን እርሱም ለዚህ ታለቅ የጌቶች ሰርግ መሰቀሉን ምልክት አደረገ፡፡ እሱንም አሸከሙት እጆቹን በ ችንካር ቸነከሩ በሰርጉ መድረክ በ ቀራኒዮ እርሱ የጌቶች ጌታ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቀለ በ መስቀል ላይ ሆኖም የዚህ ሁሉ ሴራ ጠንሳሹን ዲያብሎስን ጠርቆ አሰረው፡፡ እሱም ያኔ የተጠራጠረው ሁሉ ትዝ አለው፡፡ ግና እሱን የመሰለ ጌታ እንዴት ከግርግም ያድራል ብሎ ይመን እንዴት ምራቅ ሲተፉበት ዝም ብሎ ያያል ብሎ ይመን እንዴት ይርበዋል በሎ ይቀበል ግን ይሄን ሁሉ ባለጠግነትን ገንዘብ አድርጎ ከሰጣቸው ከሰው ልጆች ጋር ካለው ፍቅር የተነሳ አከናወነ፡፡ እራሱን ደገሰ ከሰርጉ በሁዋላ ሞት አያስፈራንም ሁለተኛውን ሰነድ እሱንም ደመሰሰልን ስለ እውነተኛ እንጀራነቱ እራሱን ሰጠን ከሰርጉ ማእድ የተካፈለ ሁሉ የዘላለም ህይወት እንደሚኖረው ጭምር በዚህ ሰረግ አወቅን ስለኛ ፍቅር የመጣ የአምላኮች አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሉን ይዘን እንድንከተለው በአባቱም በዙ መኖሪያ እንዳለ ያንንም በእምነትና በሃይማኖት ፀንተን ከተገኘን ብቻ እንደምኖርስ ነገረን እሱም ወደ ባህሪይ አባቱ ወደ አብ ወደ ባህሪ ህይወቱ ወደ መንፈስ ቅዱስ ዐረገ፡፡ የተናፈቀውም ሰረግ ለዘላለም ህይወት ሆነን!!!!!
‹‹እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል፡፡››(ብሂለ አበው)
ወስብአት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወመስቀሉ ክቡር
0 comments:
Post a Comment