• በቅርብ የተጻፉ

    Wednesday 11 November 2015

    በዓለ ቅዱስ ገብርኤል


    በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክአሜን::

    እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል አደረሳችሁ አያልን ከ ዲ /ን መላኩ አዘዘው ጡመራ መድረክ ሰለበአዓሉ ያገኝነውን ፅሁፍ ከዚህ በታች አስፍረነዋል፡፡

    ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊትየሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊመልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታትገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀውወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡ ኦርቶዶክስተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላእክትንወርኃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በፀሎትና በምሥጋናታከበራለች፤ በተለይ ታህሣሥ 19 ቀን የሚከበርበትምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤልሠለሥቱ ደቁቅን ከዕቶነ እሳት ( ከነደደ እሳት )ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡

    በጣዖት ፍቅር እጅግ ከመጠን በላይ ልቡ ተቃጥሎየነበረው የባቢሎን መሪ ናቡከደነጾር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣኦትእንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡ ያ ዘመን ለእግዚአብሔርወዳጆች የፈተና ዘመን ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣኦትሰገዱ ተረበረቡ፡፡

    እውነተኛው አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይያላቸው እምነት ንጉሥ የወደደው ጊዜ የወለደውበሚል አስተሳሰብ አይለወጥም፡፡

    በዚያ ፈታኝ ዘመን ነበር ሶስት ታማኝ የእግዚአብሔር ባለሟሎችየተገኙት፡፡ ንጉሡ ላቆመው ጣኦት ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ውሣኔው መሆኑን ወጣቶቹ በሚገባ ያውቁታል ግን ይህንን አልፈሩም፡፡ንጉሥ ሆይ አምላካችንን በመካድ አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም አሉት፡፡ ሶስቱ ወጣቶች የወሰዱት ይህ አቋም ለንጉሡ ታላቅ ራስ ምታትን ፈጠረ፤ንጉሡም አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍእንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ እሳቱም ሰባት እጥፍ ነደደ፡፡ ወዲያውኑ የንጉሡ አገልጋዮች አናንያን፣ አዛርያ፣ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ እቶን እሳት ወረወሯቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ከየት እንደመጣ ከማይታወቅ እንግዳጋር በመሆን በዕቶን እሳት ውስጥ ይንሸራሸሩ ጀመር፡፡ ይህ ተዓምራት ንጉሡንና መኳንንቱን አስገረመንጉሡም በዚህ ወቅት እነሆ እኔ በእሳቱ መካከልየሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንምአላቆሰላቸውም አራተኛውም የአማልክትን ልጅይመስላል አለ፡፡

    የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰመከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ሥጋ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምሥክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመልአኩ ሥም በፈለቀው ጠበል ተጠምቀው ደዌ የራቀላቸው እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በየዓመቱ በቁልቢና በቅዱስ ገብርኤል ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበሰበው ምዕመናን ሥዕለቱ የሰመረለት ልመናው የተሰማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን የመልአኩን አማላጅነት በመጠቀም ልናከብረው  ይገባል፡፡

    የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ረድኤት እና በረከትአይለየን - አሜን

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: በዓለ ቅዱስ ገብርኤል Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top