• በቅርብ የተጻፉ

    Monday, 5 October 2015

    ማኅሌታይ ያሬድ


    አልቦ እምቅድሜሁ ወአልቦ እምድኅሬሁ ማኅሌታይ ሰብእ ዘከማሁ፣  ያሬድ ካህን ለክርስቶስ ሰበከ ትንሣኤሁ፣  ኢይዓዱ እንስሳ ወሰብእ እምነ ሠላስ ዜማሁ።  /ከእርሱ በፊትም ከእርሱም በኋላ እንደ እርሱ ያለ ማኅሌታይ አልተፈጠረም……………./

    በስድስተኛው  ም እ ት  ዓመት  የተነሳው  ቅዱስ  ያሬድ  ማኅሌታይ  አ ምስት  አ በይት  መጻሕፍትን  በመድረሱ  ከዜማው  ጋር  አ ብሮ  ይወሳል፡፡ የድጓና  የማኅሌት  አ ባት  ያሬድ፣  አሮድዮን  እ ንደሚባለው  ወፍ  ዜማው  ልብ  የሚመስጥ  እ ጅግ  ድምፀ  መልካም  ስለሆነ  የዜማው  ደራሲ  ያሬድ፣  ወፉም  ኦ ፈ  ያሬድ  መባሉን  ር እ ሰ  ደብር  ጥ ዑ መ  ልሳን  ካሳ  በመጽሐፋቸው  ገልጸውታል፡፡    አ ንድ  የጎጃም  ባለቅኔ  ይኸንን  በማስመልከት
    " አእመርናሂ  ከመ  ሀሎ  በቀራንዮ  ገነት፣  ያሬድ  ዘወለዶ  ሄኖክ  ማኅሌት፡፡ "  ብሎ  ተቀኝቷል፡፡ 
    ትርጉሙ  ያሬድ  የወለደው  ሄኖክ  ማኅሌት  በቀራንዮ  ገነት  እ ንዳለ  አ ወቅን፣  ተረዳን  ማለት  ነው፡፡  ምሥጢሩም  ሲብራራ  ሄኖክ  እ ንደ  ኤልያስ  በሥጋ  ወደ  ሰማይ  አ ርጎ  እ ንደሚኖር  ሁሉ  ማኅሌትም  የተገኘው  ከሰማያውያን  መላ እ ክት  ዘንድ  መሆኑን  ለማነጻጸር  ነው፡፡  በ አ ፄ  ገብረ  መስቀል  ዘመነ  መንግሥት  (515-529)  ስለነበረው  ማኅሌታይ  ያሬድ  የተለያዩ  የታሪክ  ምንጮች  ሲኖሩ  አ ንዳንዶቹ  የሚመሳሰሉበትና  የሚለያዩበት  አ ጋጣሚ  አለ፡፡  ለምሳሌ  ወላጆቹን  በተመለከተ  የተለያዩ  ስሞች  አ ሉ፡፡  አባቱ  አብዩድ፣  ይስሐቅ፣  አዳም፣  እምበረም  እናቱን  ደግሞ  ታውክልያ፣  ክርስቲያን  እያሉ  የጻፉ  አ ሉ፡፡ 
    ያሬድ  የ ኢትዮጵያ  ቤተክርስቲያን  ዜማ  ያደራጀና  ለ 1500  ዓመታት  በተከታታይ  አ ገልግሎት  እ የሰጠ  ያለ  ነው፡፡  የያሬድ  ዜማ  አ ደራረስ  ትረካ  ወደ  ሚቶሎጂ  ደረጃ  ከመወሰዱም  በላይ  ድርሰቱም  ሰማያዊ  በረከት  በመሆኑ    ቅድስና ደረጃ  ተሰጥቶታል፡፡  ወደ  ሚቶሎጂ  ያመራው  አ ንዱ  ነጥብ  በስንክሳር  ግንቦት  11  ቀን  ምንባብ  ውስጥ  የሚገኝ  ነው፡፡  " እ ግዚ አ ብሔርም  መታሰቢያ  ሊያቆምለት  በወደደ  ጊዜ  ከኤዶም  ገነት  ሦስት  አ ፅዋፍን  ላከለት፡፡  እ ነርሱም  በሰው  አ ንደበት  ተናግረውት  ወደ I የሩሳሌም  ሰማያዊት  ከ እ ነርሱ  ጋራ  አ ወጡት፡፡  በዚያም  24 ቱ  ካህናት  ሰማይ  የሚያመሰግኑትን  ማኅሌታቸው  ተማረ፡፡ "  ይህቺንም  ምስጋና  አ ርያም  ብሎ  ጠራት፡፡  የቃሉንም  ድምፅ  በሰሙ  ጊዜ  ንጉሡም፣  ንግሥቲቱም፣  ጳጳሱም  ከካህናቱ  ሁሉ  ጋራ  የመንግሥት  ታላቆችና  ሕዝብ  ሁሉ  ወደርሱ  ሮጡ፤  ሲሰሙትም  ዋሉ፡፡  ከዚያም  በኋላ  ከዓመት  እ ስከ  ዓመት፣  በየክፍለ  ዘመኑ  በክረምትና  በበጋ፣  በመጸውና  በጸደይ  በ አ ጽዋማትና  በበዓላት፣  በሰንበታትም  እ ንዲሁም  በመላ እ ክት  በዓል  በነቢያትና  በሐዋርያት፣  በጻድቃንና  በሰማ እ ታት፣  በደናግልም  በዓል  የሚሆን  አ ድርጎ  በሦስቱ  ዜማው  በግ እ ዝ፣  በ እ ዝል፣  በ አ ራራይ  ሠራው፡፡ "  ያሬድ  ለዜማው  መሠረት  የኾኑት  ድርሰቶች  አ ምስት  ናቸው፡፡  እ ነሱም  ድጓ፣  ጾመ  ድጓ፣  ዝማሬ፣  መዋሥ እ ት፣  ም እ ራፍ  ናቸው፡፡  ከዘመነ  አ ክሱም  ጀምሮ  እ ስካሁን  የዘለቁት  ንዋያተ  ማኅሌት  ( የዜማ  መሣሪያዎች )  መቋሚያ፣  ጸናጽልና  ከበሮ  ናቸው፡፡  የዜማ  ስልቱም  ( ሜሎዲ )  በሦስት  መሠረታዊ  መደብ  ግ እ ዝ፣  እ ዝልና  አ ራራይ  ተብለው  ይከፈላሉ፡፡  የድጓው  ድርሰት  በ አ ራቱ  ክፍላተ  ዘመን  ( ወቅቶች )  ተመሥርቶ  የተዘጋጀ  ነው፡፡  ለ አ ብነት  ያህል  የክረምትና  የመጸው  ድርሰቶቹን  እ ነሆ፡፡  ክረምት  " ደምፀ  እ ገሪሁ  ለዝናብ  ሶቦ  ይዘንብ  ዝናብ  ይትፌስሑ  ነዳያን  ደምፀ  እ ገሪሁ  ለዝናብ  ሶበ  ይዘንብ  ዝናብ  ይፀግቡ  ርሁባን " ( ሲተረጐም )  የዝናብ  ኮቴ  ተሰማ፤  ዝናብ  በዘነበ  ጊዜ  ነዳያን  ይደሰታሉ፤  የተጠሙ  የተራቡ  ይጠግባሉ፡፡  መፀው / መከር " በጊዜሁ  ኀለፈ  ክረምት  ቆመ  በረከት  ናሁ  ጸገዩ  ጽጌያት " ( ሲተረጐም )  ክረምቱ  በጊዜው  አ ለፈ  አ ሁን  የበረከት  ጊዜ  ይሆናል  አ በባዎችም  ያብባሉ፡፡  የትንሣኤ  በዓል  በመጣ  ቁጥር  የ ኢ ትዮጵያ  ቤተ  ክርስቲያን  ካህናትና  ም እ መናን  እ የተቀባበሉ  የደስታ  መግለጫ  የሚያሰሙበት  የትንሣኤ  ምልልስ  የደረሰውም  ቅዱስ  ያሬድ  ነው፡፡  " ክርስቶስ  ተንሥ አ  እ ሙታን  በ አ ቢይ  ኃይል  ወሥልጣን  አ ሠሮ  ለሰይጣን  አ ግ አ ዞ  ለ አ ዳም  ሠላም  እ ምይ እ ዜሰ  ኮነ ፍስሐ  ወሰላም፡፡ " ( ሲተረጐም )  ክርስቶስ  ከሙታን  ተለይቶ  ተነሳ  በታላቅ  ኃይልና  ሥልጣን  ሰይጣንን  አ ሠረው  አ ዳምን  ነፃ  አ ወጣው  በዚህም  ሰላም  ይሁን፡፡  የታሪክ  ማ እ ምሩ  ዶክተር  ሥርግው  ሀብለ  ሥላሴ  በጥናታቸው  ለ ኢ ትዮጵያ  ባህላዊ  እ ድገት  ማኅሌታይ  ያሬድ  ያደረገውን  አ ስተዋጽ ኦ  ይዘረዝራሉ፡፡  ሀ )  የቅኔው  ወጣኒ  ( ጀማሪ " ና  የባህላዊ  ትምህርት  መሥራች  ይሉታል፡፡  የግ እ ዝ  ሥነ  ጽሑፍ  የተጀመረው  በቅኔ  መልክ  ሆኖ  በኋላ  ወደ  ዝርው  ( ስድ )  ተሻገረ፡፡  የያሬድ  ድጓ  የቅኔና  የዝርው  ስብጥር  ነው፡፡  ለ )  በሥነ ጽሑፍ  ረገድ  ከ አ ክሱም  ዘመን  ጀምሮ  ልዩ  ቦታ  አ ለው፡፡  ታላቁ  ድርሰት  ድጓው  የ " ኤፒክ "  ቅርጽ  ወይም  ዓይነት  ያለው  የመላ እ ክትን፣  ቅዱሳንና  ሰማ እ ታትን  ትግል  አ ጉልቶ  በቅኔያዊ  ቋንቋው  ያሳያል፤  ይገልጣል፡፡  ያሬድ  ስለ  ጥበብ  ያለው  አ ተያይም  በድጓው  ውስጥ  ይስተዋላል፡፡  " ጥበብ  ትኄይስ  እ ምብዙኅ  መዛግብት ኢ ወርቅ  ሤጡ  ወ ኢ ብሩር  ተውላጡ  ጥበብ  ክቡራት  እ ንቁ  መሠረት  አ ልቦ  ለጥበብ  ዘይመስላ፡፡ "    ትርጉሙ  ጥበብ  በዋጋ  የማትተመን  የሰው  ልጅ  ስጦታ  ናት፡፡  በዚህች  ዓለም  ከጥበብ  ጋር  የሚወዳደር  አ ንዳች  ነገር  የለም፡፡  ስለዚህም  ሀብትን  ከመሰብሰብ  ይልቅ  ጥበብን  መጠየቅ  ይሻላል፡፡  ወርቅ፣  ብር፣  እ ንቁ  ወይም  ማንኛውም  የተከበረ  ደንጊያ  ከጥበብ  ጋር  ሊተካከሉ  ሊመሳሰሉ  አ ይችሉም፡፡  ሰው  ሊመረምር፣  ሊያውቅ  እ ንደሚገባ  ያሬድ  አ ጽን ኦ ት  ሰጥቶ  ጽፎበታል፡፡  በድጓው  ውስጥ  ዘመነ  ዮሐንስ  በተሰኘው  ክፍል  ውስጥ  የጠቀሰው  " ዑ ቅ  ወጤይቅ፣  አእ ምር  ወለቡ " ( እ ወቅና  ጠይቅ፣  አ ውቀህም  አ ስተውል )  ይህንኑ  ያሳያል፡፡  ቅዱስ  ያሬድ  ከድጓ  ደራሲነቱ  ሌላ  ለዝማሬ  እ ንዲመች  ምልክት  ( ኖታ )  አ በጅቶላቸዋል፡፡  በኋላ  ዘመን  በዘመነ  ጎንደር በ 17 ኛው  ም እ ት  ዓመት  ታካይና  ተጨማሪ  ምልክቶች  ሊቃውንቱ  አ ዘጋጅተውለታል፡፡  ዐሥሩ  ምልክቶች  ይዘት፣  ደረት፣  ርክርክ፣  ድፋት፣  ጭረት፣  ቅናት፣  ሂደት፣  ቁርጥ፣  ድርስ፣  አ ንብር  ይሰኛሉ፡፡  ያሬድ  ማኅሌታይ  በድርሰቶቹ  የሃይማኖት፣  የፍልስፍና  የታሪክ፣  የሥነ  ምኅዳር  ( ስለ  አ ካባቢ  ጥበቃ  -  ኢ ኮሎጂ )  ፍሬ  ጉዳዮችን  የመረመረበትና  ያመለከተበት  ሁኔታ  ጎልቶ  ይታያል፡፡  ስለ  ሥነ  ምኅዳር  ከነገረ  መለኮት  ጋር  አ ያይዞ  በግንባር  ቀደምትነት  " ኮቴ ኦ ሎጂ " ( ኢ ኮሎጂና  ቴ ኦ ሎጂ )  ጽንሰ  ሐሳብ  ያስተዋወቀ  በመሆኑ  የ I ትዮጵያ  ኤኮቴ ኦ ሎጂ  የበላይ  ጠባቂ  ( ዘፓትረን  ኦ ፍ I ትዮፒያን  ኤኮቴ ኦ ሎጂ )  ተብሎ  ሊጠራ፣  ሊታወጅለት  ይገባል፡፡  ስለ  ቅዱስ  ያሬድ  ታላቅነት  መታሰቢያ  ምን  ሠራን ?  በቀዳማዊ  ኃይለ  ሥላሴ  ዘመን  በስሙ  " ያሬድ  ሙዚቃ  ት / ቤት "  የተሰየመ  ሲሆን፣  አ ዲስ  አ በባ  ውስጥ  በ ኢ ትዮጵያ  ቴሌቪዥንና  በጥቁር  አ ንበሳ  ሆስፒታል  መካከል  ላይ  ያለው  አ ውራ  ጎዳና  " ያሬድ  መንገድ "  ተብሎ  ተሰይሞለታል፡፡  ሐውልት  ግን  የለውም፤  ለምን ?  ቦሌ  መድኃኔ  ዓለም  አ ካባቢ  ያለው  አ ደባባይ  ላይ  ( የ አ ንድ  ተቋም  በርሚልን  ለማስተዋወቅ  የደንጊያ  ክምር  በተተከለበት  ጊዜ  በ አ ንድ  መድረክ  የቀረበ  አ ስተያየት )  ሐውልቱ  እ ንዲተከል  ሐሳብ  ቢቀርብም  ከቤተ  ክህነትም  ሆነ  ከቤተ  መንግሥቱ  ( ባህልና  ቱሪዝም  ሚኒስቴር )  ከቁብ  የቆጠረውም  የለም፡፡  የቀድሞው  የያሬድ  ሙዚቃ  ት / ቤት  ዳይሬክተር  መራሔ  መዘምራን  ( ኮንዳክተር )  አ ማኒ  ኢ ብራሂም  በ 1970 ዎቹ  አ ጋማሽ  በ አ ንድ  መጽሔት  ስለ  ት / ቤቱ  ተጠይቀው  ሲመልሱ  ስለ  ቅዱስ  ያሬድ  ታላቅነት  አ ውስተው  " ሐውልት  ቢቆምለት  በወደድኩ "  ብለው  ነበር፡፡  ያኔም  ሆነ  አ ሁን  ያዳመጠና  ወደ  ተግባራዊነት  ለመሸጋገር  የሞከረ  የለም፡፡  አ ሁንም  ድምፃችንን  እ ናሰማለን፡፡  በ 1970 ዎቹ  አ ጋማሽ  የ ኢ ትዮጵያ  ደብተራዎች  ያሬዳዊ  ዜማን  ለማሰማት  ወደ  አ ውሮፓ  የተለያዩ  ከተሞች  አ ምርተው  አ ስደናቂውን  ዜማ  አ ሰምተው  ነበር፡፡  የቢቢሲ  ራዲዮ  " ፎከስ  ኦ ን  አ ፍሪካ /focus on Africa/"  አ ዘጋጅ  ፕሮግራሙን  ተከታትሎ  ከተረዳ  በኋላ  ምን  እ ያላችሁ  ነው ?  በስድስተኛው  ም እ ት  ዓመት  አ ፍሪካዊው  ያሬድ  በራሱ  ድርሰት፣  በራሱ  ኖታና  የዜማ  መሣሪያ  ከነ  ሞዛርት፣  ቤቶቨን  በፊት  ዜማ  ደርሷል  ማለታችሁ  ነው፡፡  ምነው  እ ስካሁን  ደበቃችሁት ?  ወይ  የያሬድ  ሰዎች  ያሬድን  አ ታውቁትም፤  አ ሊያም  ንፉጎች  ናችሁ  ብሎ  መናገሩን  አ ስታውሳለሁ፡፡  በአጠቃላይ ቅዱስ ያሬድ ከነ ቅዱስ ሄኖክ፣ ከአባታችን አቡነ አረጋዊና ከነ ነቢዩ ኤልያስ ጋር በብሔረ ሕያዋን ለመኖር የበቃ ቅዱስ አባታችን ነው። ስለዚህ ይህንን ታላቅ የዜማ አባትና የቤተ ክርስቲያን ዓምድ ቅዱስ ያሬድን ሁሌም ልንዘክረው ይገባናል። በረከተ ጸሎቱ ከሁላችን ጋር ትኑር::

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ማኅሌታይ ያሬድ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top