• በቅርብ የተጻፉ

    Saturday 24 October 2015

    ብሒለ አበው ስለ ነገረ ሕማማት


    † ‹‹እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸዉ ችንካሮች መወጋቱን እናምናለን ነቢዩ  ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወስዶ ህማማችን ተሸከመ እንዳለ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ

    † ‹‹ነፍሱን ከስጋዉ በለየ ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ ጌታችን በአካለ ስጋ ሳይሆን በ አካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሄደ ሲኦልም ተናወጠች መሰረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ››ቅዱስ አትናቴዎስ ዘ እስክንድርያ

    † ‹‹የሚሰዋ በግ እርሱ ነዉ የሚሰዋ ካህን እርሱ ነዉ፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከ አብ ከባሕርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መስዋዕት የሚቀበል እርሱ ነዉ፡፡››ያዕቆብ ዘ ስሩግ

    † ‹‹ኃጢአታችን ለማሰተሰርይ በስጋ እንደታመመ እንደሞተ ከነፍሱም በተለየ ጊዜ ስጋዉን እንደገነዙ እናምናለን›› የ ኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ ቅ/ዮሐንስ

    † ‹‹ምትሐት ያይደለ በእዉነት ተራበ ተጠማ ዳግመኛም ከኃጥአን ጋር በላ ጠጣ›› ቅ/ባስልዮስ ዘ ቂሳርያ

    † ‹‹ከ አብ ጋር አንድ እንደመሆንህ ሞት የሌለብህ አንተ ነህ ከእኛም ጋር አንድ እንደመሆንህ በፈቃድህ የሞትክ አንተ ነህ›› ቅ/ኤራቅሊስ

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ብሒለ አበው ስለ ነገረ ሕማማት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top