• በቅርብ የተጻፉ

    Saturday 24 October 2015

    ብሒለ አበው ክፍል ሁለት

    †  ‹‹ብዙ ከመብላትና ብዙ ከመጠጣት የማይከለከል ሰዉ ሰይጣነ ዝሙትን ድል አይነሳዉም፡፡›› (ማር ይስሐቅ)

    † ‹‹መመጽወትና መጾም ለነፍስ ህይወትን ለስጋ ጤንነትን ይሰጣል፡፡›› (አንጋረ ፈላስፋ)

    † ‹‹ያለ ጸሎት መንፋሰዊ ነኝ የሚል ሰዉ እሳት መካከል ገብቶ የሚጫወትን የ እሳት እራትን ይመስላል፡፡›› (ማር ይስሐቅ)

    † ‹‹ልጀ ሆይ አንተ በራስህ ላይ ስትፍረድ እግዚአብሔር ፍርዱን ያነሳልሃል አንተ በራሰህ ላይ ባትፈርድ ግን  እግዚአብሔር  ይፈርድብሀል (ታላቁ መቃሪዮስ) 

    † ‹‹በወንድሙ ወድቀት የሚደሰት ሰዉ ተመሳሳይ ወድቀት ይጠብቀዋል›› (ቅዱስ ኤፍሬም)

    †  ‹‹የወንድምህን ኃጢአት መሸፈንና ያእርሱን ኃጢአት እንደራስህ አድርግህ በእርሱ ፋንታ መሞት ካልቻልክ ቢያንስ ስለ ኃጢአቱ አትፍረድበት›› (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ)

    †  ‹‹በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ታገኝ ዘንድ ታገስ›› (ማር ይስሐቅ)

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ብሒለ አበው ክፍል ሁለት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top