• በቅርብ የተጻፉ

    Monday 19 October 2015

    የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ስድስት

    6ኛ በጎነት

    በገላትያ ምዕራፍ 5ከተገለጹት የመንፈስ ፍሬዎች መካከል አንዱ በጎነት ነው፡፡ በጎነት ለሰዎች ያለን መልካም አመለካከትና የምናደርገው ማንኛውም መልካም ሥራ ሁሉ ነው፡፡ በጎነት ማንኛውንም መልካምና ጥሩ፣ የበጀ የተወደደ፣ ሥራን ያካትታል አምላካችን እግዚአብሔር በባሕርዩና በሥራው በፈጠረው ፍጥረት መደነቁ ሁሉ የበጎነቱ አይነተኛ ምልክት ነው፡፡ ሁሉንም በየወገኑ በመፈጠሩ ማለቴ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በፍጥረቱ በጎነት ይታወቃል እንዳሉ አበው እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን በጎነት ሲባል ንጽጽራዊ በጎነት ማለት ነው፡፡ ፍፁም በጎነት የእግዚአብሔር ባሕርይ ብቻ ነው፡፡ “የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ” ማቴ. 5፡48 ተብሎ በጌታ ቃል ከተገለጸው ፍጹምነት ጋር ተመሳሳይ ነው ይህም ንጽጽራዊ ፍጹምነት ነው፡፡ሁለት ዓይነት በጎነት አለ ይኸውም አሉታዊና አወንታዊ ናቸውአሉታዊ በጎነት ማለት ክፋትና ኃጢአትን ማስወገድ ነው፡፡ ይህም በ10ቱ ትዕዛዛት ውስጥ የምንማራቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡-“የአግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ…”ዘዳ.5፡11በሚለው ውስጥ በእምነት የምንተገብራቸው ናቸው፡፡ አወንታዊ ስንል ደግሞ በጎነትን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስንመለከት “አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍፁም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም ኃይልህ ውደድ ዘዳ.6፡5”. በሚለው ውስጥ የተካተቱት ናቸው፡፡ አዲስ ኪዳንም ውስጥ ክርስቶስ ስለ ብፁዓን በተናገራቸው ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ተጠቅሰዋል፡፡ በመንፈስ ድሆች የሆኑ…የዋሆች….ልበ ንጹሖች…የሚያስታርቁ…ብፁዓን ናቸው ወዘተ…ማቴ.5፡3፡፡ አሁን በጻፍኩላችሁ በበጎነት የመንፈስ ፍሬ ላይም በግልጽ የምንማረው ነው፡፡ ከማንኛውም ኃጢአትና ክፉ ሥራ ሁሉ ለመራቅ፣ እና በመልካም ምግባር ታንጾ ለመጓዝ ሁለቱንም መንገዶች መከተል አለብን በሕግና በፍቅር /በውዴታ/የምንፈጽማቸው የበጎነት ሥራ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ሙሉ የሆነ በጎነትን ገንዘቡ ካደረገ ከማንኛውም ክፉ ነገር ነፃ ይሆናል፡፡ይህን በእውነተኛ መጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ለማስረዳት የሞከርኩትን ከዚህ የሚከተለውን በጥሞና አንብባችሁ ተረዱልኝ፡፡ ይስሐቅና እስማኤል፣ ቃየልና አቤል በአንድነት መኖር እንዳልቻሉ ሁሉ መንፈስና ሥጋ /አሮጌ ተፈጥሮ/ እርስ በርሳቸው በተቃውሞና በጦርነት ላይ ናቸው፡፡መንፈስ ቅዱስ አካላችንን የሚቆጣጠረው ከሆነ በመንፈስ እንመላለሳለን ሥጋ አካላችንን የሚቆጣጠረው ከሆነ በሥጋ ምኞትና ፍላጎት እንመላለሳለን፡፡ በመንፈስና በሥጋ መካከል ያለው ተቃውሞ ምክንያት መንፈስና ሥጋ የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው መሆናቸው ነው፡፡ለምሳሌ፡-በግ ቆሻሻ ነገሮችን የማይወድ ንፁሕ እንስሳ ነው፡፡አሳማ ግን ከታጠበች በኋላ ወደ ጭቃ የምትመለስ ንጽሕናን የማትወድ ናት 2ጴጥ 2፡19በኖኀ ዘመን የሆነው ቁራ ሥጋ በል እንደመሆኑ በቂ ምግብ በማግኘቱ በዚያው ቀረ፡፡ መልካሟ ርግብ ግን የምሥራች ይዛ ተመልሳ መጣች ሁለተኛ ሲለቃት ወዲያውቀረች የምታርፍበት ምድር ተስተካክሎ ነበርና ዘፍ.8፡6-12፡፡ ሮሜ 7፡15 ፤ ዕብ. 10፡14 ፤ 2ቆሮ. 3 ፤ 1 መዝ.40፡8 ፤ 1ጢሞ 1፡9 ፤ 2ጢሞ. 3፡2 ፤ ኤር. 17፡9 አንብቡ፡፡ቅዱስ ዳዊት “ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”መዝ.15፡2ባለው መሠረት የክርስቲያኖች በጎነታቸው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ምክንያቱም ቃሉ እንደሚለን“እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደአሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን”ሮሜ.8፡28ከእግዚአብሔር የሆነው ነገር ሁሉ በጎ ነገር ነው፡፡ይህንን የእግዚአብሔርን በጎነት ለሰው ልጆች በሙሉ ማስተማር መንገር አለብን 1ጴጥ.2፡9ክርስቲያኖችም መልካም ሥራን መፈለግም ሆነ ማድረግ የምንችለው በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው፡፡“የአግዚአብሔር በጎ ፈቃድም በስብከት ሞኝነት የሚያምኑ እንዲድኑ ነው ፊልጵ. 2፡13”፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ “በጎ ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው ብሏል 1ጰጥ.3፡13”፡፡ በክርስትና ኃጢአት የሚባለው ክፉ ሥራ ብቻ ሳይሆን በጎ አለማድረግም ነው፡፡ “እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው”ያዕ.4፡17፡፡ሐዋርያው ያዕቆብ በተጨማሪ እንዲህ ሲል ይመክረናል፡፡“የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ አትሳቱ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ፡፡ በጎ መሆን በራሱ ስጦታ መሆኑን አስረድቷል”በጎ ሥራ የሌለው እምነት የሞት ነው“ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድምወይም እህት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ ከእናተ አንዱም በደኅና ሂዱ እሳት ሙቁ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግንየሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚህም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞት ነው” ያዕ. 2፡14በጎነት ከቅናት የራቀ ነውከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው?በመልካም አነዋወሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ፡፡ ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም ነገር ግን የምድር ነው፣ የሥጋም ነው፣ የአጋንንትም ነው ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ሰፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና፡፡ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት በኃላም ታራቂ ገር እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት፡፡ የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል ያዕ.3፡13 ሲል ያስተማረው የበለጠ ልብ የሚነካ ምስጢር ነው፡፡…………………ይቆየን …………………….ይቀጥላል

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ስድስት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top