• በቅርብ የተጻፉ

    Monday 19 October 2015

    የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ሁለት

    2ኛ ደስታ

    ደስታ በምናየውና በምንሰማው፣ በምንቀምሰው ነገር በተፈጸሙ ክስተቶች የሚሰማን የህሊና እርካታ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ሕይወትደግሞ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የሚገኝ መንፈሳዊ የርካታ ስሜት ነው፡፡ ደስታችንም የሚፈጸመው በዓለም ከሚገኘው ጊዜያዊ ደስታ በተለየ መልኩ ነው፡፡

    የክርስቲያኖች ልዩ ደስታ የሚሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዓምለካዊ ፍቅሩ ዓለምን በማዳኑ በሚሰማን ደስታ ነው፡፡ ይህም መልዐኩ ለእረኞች እንደነገራቸው “ታላቅ ደስታ” ተብሏል፡፡ ሉቃ. 2:፡10ለ

    ጌታችን እናት ለድንግል ማርያምም ቅዱስ ገብርኤል ሲያበስራት “ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ”ብሏታል ሉቃ.1፡28 እርስዋም የጌታችን እናት ስለ ደስታ ስትናገር “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት /ደስታ/ ታደርጋለች”ብላለች ሉቃ.1፡47

    የባሕርይ አባቱ አብ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው፣ የመረጥኩት ልጅይህ ነው”ብሏል ማቴ 3፡17 ፣ 17፡5፡፡ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስና በፍቅሩ ሥራ ደስ ሊለን ይገባል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ጌታን ከሕዝቡ ካገናኘ በኋላ “እንግዲህ ደስታዬ ተፈጸመ” ብሏል ዮሐ. 3፡29፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰውን በደስታ እንዲኖር አድርጐ ነው የፈጠረው ሁሉንም ለሰው ልጅ ምቾት አዘጋጀለት፡፡ እዚህ ላይ በእርካታና በደስታ መካከል ያለውን ልዩነት ለይተን ማወቅ አለብን እርካታ በአብዛኛው ለሥጋና ለስሜቶች የተገባ ነው፡፡ እውነተኛ ደስታ ግን ለመንፈስ የተገባ ነው፡፡

    ሰው በመብላት፣ በመጠጣት ወይም ውብ የሆነ ትዕይንት በማየት ወይም በመስማት እርካታ ሊሰማው ይችላል፡፡ እነዚህም ስሜታዊ እርካታዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊ መዝሙር ወይም መንፈሳዊ ቃላትን በመስማት መንፈስ የራሱን ደርሻ ይወስዳል፡፡ ሐሰተኛ ደስታ-በጠለት ወድቀት ወይም በእርሱ ለይ በደረሰበት ማንኛውም ክፉ ነገር መደሰት የውሸት ደስታ ምሳሌ ነው፡፡ ይህ በራስ ላይ የሚሠራ ኃጢአት ነው ጠቢቡ ሰዘለሞን “ጠለትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ ”ምሳ 24፡17 ሲል ተናግሯል፡፡ ለኃጢአት መጋበዝን የሚያመለክት በኃጢአት የተሞለ ደስታ ነው፡፡ ይህም የፍቅር ተቃራኒ ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ“ፍቅር በደልን አይቆጥርም” 1ኛ ቆሮ 13፡6 ብሏል፡፡

    -ሌለው በትዕቢት፣ እራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ጋር የተቀላቀለ ደስታም ሐሰተኛ ደስታ ነው፡፡ ለዚህ ትምህርት እጀግ በጣም የምወደውን የወንጌል ክፍል መጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ ሉቃ፡10፡17 ደቀመዞሙርቱ በደስታ ተሞልተው “ጌታ ሆይ አጋንንት እንኳ በስምህ ተገዝተውልናል”አሉት፣ “ጌታም በዚህ ደስ አይበላችሁ…ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ“ ሲል አስተምሯቸዋል፡፡

    -አንዳንዶች በቁሳዊ ነገሮች ይደሰታሉ አንድ ቀን አዲስ አበባ አንድ ትልቅ የገበያ ማዕከል ውስጥ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር ገብቼ በጣም ውደ የሆኑ የቤት ዕቃዎችን ማየት ጀመርኩ አንዱ ከእኛ በፊት የገባ ሰው ዓይኑ ላይ የሚገቡትን የዕቃዎች ዋጋ ይጠይቃል፡፡ ዋጋቸው በትንሹ ከ2000 በላይ ነው የሚጠሩት እያየ ያደንቃል አንዲት ትንሽ የብር ሳሐን ይዞ ወደ እኔ ጠጋ አለ አየህ እንዴት ያምራል አለኝ እኔም የማላውቀውን ሰው ላለማሳፈር ጥሩ ነው ያምራል አልኩት በሆዴ የማን አቅም ችሎ ይገዛዋል እያልኩ…

    -እኔም አንዴ አናግሮኛል ብዬ በቤትህ በጣም የሚያምሩ ነገሮች ቢኖሩህ ደስተኛ ነህ አልኩት ቀበል አድርጐ አወን በጣም ደስ ይለኛል አለኝ፡፡ ግን እቤትህ ታላቁን ደስታ የሚሰጠው መጽሐፍ ቅዱስ አለህ? አልኩት ቀና ብሎ እያየኝ አይ ድሮ ነበረኝ አሁን ግን የለኝም አለ፡፡ ሰዎችን ምን ይህል ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ በቁሳቁስ እንደሚማረኩ ይህ ሰው መልካም ማሳያ ሆኖልኛል፡፡ ለዘለዓለም ወደ ማይሻረው የእግዚአብሔር ሕገ መንግሥት “መጽሐፍ ቅዱስ” ገለጻ ልዉሰዳችሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ”ፊል.4፡4፡፡

    ሁልጊዜ ሲል በምን በምን ጊዜ ነው? ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ለአንባቢዎቼ አቀርባለሁ፡፡
    1.በቀራንዮ አደባባይ ደሙን ለኛ አፍሶ በፍጹም ፍቅሩ የወደደንን አምላክ እምነታችን በተገለጸ ጊዜ ሐዋ.8፡39 ፣ ሐዋ. 16.312.ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉን ጊዜ መዝ. 121፡13.የክርስቶስ ወንጌል በማንኛውም ጊዜና መንገድ በሙላት ለሰዎች በተሰበከ ጊዜ ፊል. 1፡184
    እግዚአብሔር በሕይወታችን ታላቅ ነገርን ባደረገልን ጊዜ መዝ. 125፡15.ምንም እንኳን እህልና ከብቶች ሌላም ሀብት በማይኖረን ጊዜ ዕንባ. 3፡176.በሚወደን በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ስደት፣ መከራና ስቃይ በሚደርስብን ጊዜ ማቴ. 5፡11፣ 2ቆሮ.5፡8 ፣ 2ቆሮ. 7፡4፣ 1ጴጥ. 4፡12 በጌታ ያገኘነውን ደስታ የምንገልጠው እንደዓለም በዘፈንና በስካር ሳይሆን አምላካችንን በመዝሙር በማመስገን ነው ኢሳ. 52፡9፡፡ ይህንንም ቅዱስ ያዕቆብ “ደስ የሚለውም ማንም ቢኖር እርሱ ይዘምር”በማለት ገልጾአል፡፡ ያዕ.5፡13፡፡ ከጌታ ጋር ከሆንን የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ ስለምንጥል ሁሉጊዜ ደስታ ይሰማናል፡፡እርሱም በእኛ እምነትና የክርስትና ሕይወት ይደሰታል፡፡ የወይን ግንድ የሆነው እኛ ቅርንጫፎቹ እንድንሆንና ብዙ ፍሬ እንድናፈራ የነገረን በእኛ ደስ እንዲለው እኛም በእርሱ ደስ እንዲለን ነው ዮሐ. 15፡11፡፡

    ይቆየን …..ወስብሐት ለእግዚአብሔር

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ሁለት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top