• በቅርብ የተጻፉ

    Saturday 24 October 2015

    ብሒለ አበው ክፍል አንድ

    1. ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስነው /ቅዱስ ስራፕዮን/

    2. የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ ፡፡ /መጽሐፈ ምክር/

    3. አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ምስጢር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡ /አረጋዊ መንፈሳዊ/

    4. ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡ /ማር ይስሐቅ/

    5. ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡ /አረጋዊ መንፈሳዊ/

    6. ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ›› /አባ እንጦንስ /

    7. ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል›› /ቅዱስ አትናቴዎስ /’

    8. ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል›› /ቅዱስ ሚናስ/

    9. ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› /ታላቁ አባመቃርስ/

    10. ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/

    11. ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል›› /ቅዱስ እንድርያስ/

    12. ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተሞላን እንሆናለን›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/

    13. ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

    14. ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/

    15. ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/

    16. ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል  ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል›› /ቅዱስ እንጦስ/

    • Blogger Comments
    • Facebook Comments

    3 comments:

    1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

      ReplyDelete
      Replies
      1. አሜን እግዚአብሔር ይስጥልን::

        Delete
      2. እግዚአብሔር እድሜ እና ጤና ይስጥልን

        Delete

    Item Reviewed: ብሒለ አበው ክፍል አንድ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top