• በቅርብ የተጻፉ

    Thursday 29 October 2015

    የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለመከላከል እና ለማጋለጥ በመካሔድ ላይ የሚገኘው እንቅስቃሴ በቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ወሰነ፡፡

    የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በትምህርት ይከላከላል፤ ማስረጃዎችን እያቀረበ ያጋልጣልየጠቅ/ቤተ ክህነቱ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ይመራልቋሚ ኮሚቴው፣ ከሰርጎ ገቦች የጸዳና አባላቱም በሃይማኖታቸው እንከን የሌላቸው ሊኾኑ ይገባል

    ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፤የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ

    የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊ እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ መጠበቅ እና ማስጠበቅ፤ አገልግሎቷ እና አስተዳደሯ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲመራ የማድረግ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ÷ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለመከላከል እና ለማጋለጥ በመካሔድ ላይ የሚገኘው እንቅስቃሴ በቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ወሰነ፡፡

    ቋሚ ኮሚቴው÷ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት እና ክርስቲያናዊ ትውፊት በመበረዝ እና አስተዳደራዊ አንድነቷን በማናጋት ለመከፋፈል አልያም ባለችበት አዳክሞ ለመውረስ ወደ መዋቅሯ ሰርገው የገቡትን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆችንና የዋነኛ አዝማቾቻቸውን ሤራ በማስረጃ የማጋለጥ እና በትምህርት የመከላከል ተልእኮ የተሰጠው ሲኾን ተግባሩን የሚያስፈጽምበት መዋቅርም በዘላቂነት እንዲዘረጋ ነው የተወሰነው፡፡

    ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አህጉረ ስብከት እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የሚዘረጋው የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ በበላይነት የሚመራው በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሲኾን በቋሚ ኮሚቴው አባልነት የሚመረጡት ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችም በእምነታቸው እንከን የሌለባቸው፤ በቀናዒነታቸው፣ በዕውቀታቸው እና በሕይወታቸው የተመሰከረላቸው ሊኾኑ እንደሚገባ ቅዱስ ሲኖዶሱ በውሳኔው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለመከላከል እና ለማጋለጥ በመካሔድ ላይ የሚገኘው እንቅስቃሴ በቋሚ ኮሚቴ እንዲመራ ወሰነ፡፡ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top