• በቅርብ የተጻፉ

    Sunday 25 October 2015

    ከእነዚህ ደግሞ ራቅ

     

    ሐሜት፡ ያለ መሳርያ ሰውን መግደል ነው።

    ቁጣ፡ ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት።

    ማጉረምረም ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።

    ብስጭት፡ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስና የኃጢአት ምንጭ፣ ጭንቀትን    የሚያነድ ክብሪት ነው።

    መዋሸት እውነተኛ ሰውን ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።

    መርገም አቅም ሲያንስ ወደ ላይ የሚወረውር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።

    መሳደብ ኅሊናን የሚያቆስል ቁስል ቶሎ    የማይድን አቅም የልላቸው ሰዎች ዱላ ነው።

    ዋዛ ፈዛዛ፡ በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።

    ዘፈን፡ ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ክፉ ፍላፃ ነው። ድንፋታ፡ የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ ነው።

    መንፈግ፡  የሚለምነውን ሰው የሚወጉበት የስስታሞች ፍላፃ ነው።

    መጠራጠር፡ ወደ ክህደት የሚመራ የከሃዲዎች መንገድ መጥረጊያ ነው። ማሽሟጠጥ፡ ሰውን የሚደበድቡበት የእነ እያዩኝ ባይ ዱላ ነው።

    ምኞት፡ በሐሳብ ተጸንሶ በቅዠት የሚወለድ ክፉ ፍላፃ ነው። ጠብ፡  እሳትን ለማንደድ የሚጫር የነገረኞች የኪስ ክብሪት ነው።

    መሳለቅ፡ የማይታይ የቀናተኞች ጦር ነው። ነገር ማመላለስ፡ የቁም ህልም ነው።

    በክፉ ማንሾካሾክ፡ ሰውን የሚገድሉበት የአሳባቂዎች ጩቤ ነው።

    ቃልን መለወጥ፡ የነመስዬ ልደር የማውደልደያ ትጥቅ ነው።

    በሐሰት መማል፡ ሰውን ለማዘናጋት ሆን ብሎ የያዙት የግብዞች ማደሪያ ነው።

    ሰውን ማስነወር፡ ስም ለማጥፋት ምቀኞች የሚቀቡት ቀለም ነው።

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ከእነዚህ ደግሞ ራቅ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top