• በቅርብ የተጻፉ

    Saturday 24 October 2015

    ብሒለ አበው ክፍል ሦስት

    * ሰይጣን ራሳችንን ስንገዛና ከራሳችን ጋር ስንሆን ኃጢአታችንንም ስናስተውል ስለንሰሐም ስናስብ ይፈራል። በዚህ ጊዜ ከእርሱ ማምለጥ ይቻላል።

    * በእናንተ ሳይፈረድባችሁ አስቀድማችሁ እናንተ በራሳችሁ ላይ ፍረዱ”   /ቅዱስ መቃርዮስ/

    * እንባህ ከመፍሰስ እንዳይቆም ከወደድህ በጸሎት ጽሙድ ሁን አንድም በተዘክሮ ጽሙድ ሁነህ ኑር። /ማር ይስሐቅ/

    * መከራ  መጥቶብህ መከራውን ለማራቅ ከምትጸልየው  ጸሎት አስቀድሞ ለሚገባ ንሰሀ ተዘጋጅ።  /ማር ይስሐቅ/

    * እኛ ሀጢአታችንን ያስታወስን እንደሆነ እግዚአብሔር ይተዋቸዋል። እኛ ግን ኃጢአታችንን የዘነጋን እንደሆነ እግዚአብሔርያስታውሰናል”   /ቅዱስ እንጦስ/

    * በንሰሀ ሕየወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም።  /አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ/

    * አንተ ሌሎችን የምትምር ከሆነ እግዚአብሔርም አንተን ይምርሃል። ነገር ግን አንተ እቁጡና ጨካኝ ሆነህ ሳለህ የእጅህንዋጋ ብታገኝ እንዳታማርር። /አቡነ ሽኖዳ/

    * የዋህ ሰው ሰለ እርሱ ሰዎች ይከላከሉለታል እንጂ እርሱ አይከላከልም። አቡነ ሽኖዳ*.ክርስቲያን በተፈጥሮው የማስተዋል የአርምሞ የጥንቃቄና የሰላም ሰው ነው።

    * አንተ ካስፈለገህ ሁለት ጊዜ ከተጠየቅህ በመጠኑ ተናገር፣ መልስህም በጥንቃቄ እና በ’እውቀት ባጭሩ የሰዎችን አእምሮ የማያስጨንቅ ይሁን።

    * እውነትን ከመስማት የበለጠ ለጆሮውች ጌጣጌጥ የላቸውንማ ሴቶች ለምድራዊ ጌጣጌጦች ጆሯቸውን አይብሱ፣ እውነትን ለመስማት የተበሱ ጆሮዎች ቅዱስ ነገርን መለኮታዊ ቃልን ያደምጣሉና።

    * አንደበትህ በአርምሞ በዝምታ የተመላ ይሁን ልብህን በእርጋታ አአኑረው የሁሉም መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ፣ ለከንቱ ንግግር (ወሬ) ዘገምተኛ እና ሰነፍ ሁን፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድህነት የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን።

    * ማንኛውንም ነገር ለማውቅ የክፋት መርዝ በአምሮህ እንዳይሰራጭ ጉጉት አይደርብህ*.የመንፈስ ስጦታዎች ልዩ ልዩ እንደመሆናቸው መጠን እና አንዱ አገልጋይ ሁሉንም ገንዘብ ማድረግ ሰለሚችል በተሰጠው ጸጋበማመስገን ቢቀመጥ መልካም ነው።

    * ለመስበክ የተመረተው ሰባኪ ወንጌልን ለመስበክ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይጠብቅ እንጂ የራሱን አይደለም

    * ሰነፍ ሰው ሲስቅ ይጮሀል ድምጹንም ከፍ ከፍ ያደርጋል።

    * የሚስት አክሊሏ ባሏ ነው፣ ፣የባልም ጋብቻው ለሁለቱም የጋብቻቸው አበባም አንድነታቸው ልጆቻቸው ናቸው። ይኸውም በመለኮታዊ አመሰራረት ከስጋ እርሻ yeተገኘ ነው ።

    * ድንቁርና በሃጢአት እንድነውድቅ ስለሚያደርግ እውነትንም በግልጽ የምናይበትን ችሎታን ስለማይሰጥ ጨለማ ነው። እውቀት ግን የድንቁርናን ጨለማ አስወግዶ እውቀትን ሰለሚያጎናጽፈን ብርሃን ነው።

    * ልብህን በእርጋታ አኑረው፤የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር (ወሬ) ዘገምተኛናሰነፍ ሁን። ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድህነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን ።    /ታላቁባስልዮስ የቂሳሪያ ሊቀ ጳጳስ/

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ብሒለ አበው ክፍል ሦስት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top