• በቅርብ የተጻፉ

    Wednesday 28 October 2015

    የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ።

    (ኤፍ ቢ ሲ፤ አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም.)

    የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች፣ መምህር ግርማ ዛሬ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መኾኑን ተናግረዋል።

    አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ፣ በማጥመቅ እፈውሳለኹበሚል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ሕገ ወጥ ሀብት ሲያካብት እና በርካታ ምእመናንን ለችግር ሲዳግር ቆይቷል፡፡

    ይኹን እንጂ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነገጋረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ አጥማቂው ዕውቅና እና ፈቃድ የተነፈገው ሕገ  ወጥ  እንደኾነ  አረጋግጧል።

    የፋና ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ በፈውስ አገልግሎት ስም የማጭበርበር ወንጀል ሳይጠረጠር እንዳልቀረ ነው የተናገሩት።

    • Blogger Comments
    • Facebook Comments

    2 comments:

    1. ነኝ ባዩን ይህ አቋምህን ይገልጻል እውነት ግን ያለ አድልዎ ነው ሪፖርት መደረግ ያለበት

      ReplyDelete
    2. abatachene ke egzyabhere yetesetune talake sewe nachewe mene seytane betere ersachewe fewse gemerewale egzyabhere yemsgene lesacheweme ersgheme edemena tena yestlene amen

      ReplyDelete

    Item Reviewed: የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ። Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top