• በቅርብ የተጻፉ

    Tuesday, 6 October 2015

    ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን

    ምሥጢር ማለት ምን ማለት ነው?

    ምሥጢር፡- ‹‹አመሥጠረ›› አራቀቀ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ረቂቅ የማይታይ ፣ ኅቡዕ ፣ ሽሽግ ማለት ነው፡፡ አንድም

    ምሥጢር፡- በመንፈሳዊ ትርጉሙ ሲታይ የሰው ልጅ በራሱ ጥበብ መርምሮ ሊደርስበትና ሊያውቀው የማይችል አምላካዊ ግብር መንፈሳዊ ረቅቅ የማይታይ የሚደንቅ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ 5ቱ አእማደ ቤተክርስቲያን

    ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን በእምነት ካልሆነ በቀር በሥጋዊ ጥበብ ሊቀበሉት አይችሉም ከሰው አእምሮ በላይ ናቸውና፡፡ ለዚህም ግልጽ የሆኑ ቃላትን በመጽሐፍ ቅዱስ መመልከት ይቻላል፡፡
    ለምሳሌ ጌታችን በዮሐ 6፡56 ላይ‹‹ ሥጋዬን የበላ ከሜን የጠጣ የዘለአለም ሕይወት አለው›› ብ የቅዱስ ቁርባንን ምሥጢርናት ሲያስተምራቸው ብዙዎች ወደኋላ እንደተመለሱ ቅጥር 66 ላይ ይናገራል፡፡ እንዲሁም አሉ ‹‹ ይህ ነገር የሚያስጨንቅ ንግግር ነው ማን ሊሰማው ይችላል?›› ዮሐ 6፡60፡፡ በሌላም ቦታ ላይ በዮሐ 3፡3 ላይ ‹‹ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሕርን መንግሥት ሊያይ አይችልም›› ብሎ ለኒቆዲሞስ ምሥጢረ ጥምቀትን ሲሰብከው ይህ ረቂቅ የሆበት ኒቆዲሞስ የመለሰው መልስ ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ይወለዳል?›› ነበር ያለው፡፡ ጌታ በእምነት ሊቀበሉት ስለሚችል ምሥጢር ሲነግረው እሱ ግን ስለ ምድራዊ /ሥጋዊ/ ያስባል ያ መንፈሳዊ ይህ ሥጋዊ ከዛም አለው ነፋስ ሲነፍስ ታያለህ ከወዴት እንደሚመጣ ግን አታውቅም ዳግም መወለድም እንዲሁ ነው ብሎ ረቅቅነቱን ነግሮታል፡፡ ስለዚሀ ሁሉም ምሥጢራት ከኛ አእምሮ በላይ ስለሆኑ በእምነት ብቻ መቀበል አለብን ያልነው ለዚህ ነው፡፡ በዳዊት ትርጓሜ ላይም ‹‹ በሬ ቀንበር ከተጫነበት ያ ቀንበር ሲያስጨንቀው እንደሚውል እንዲሁም ባሕርየ ሥላሴን ወይም የእግዚአብሔርን ሥራ ምሥጢር እመረምራለሁ የሚል ሰውም እንዲሁ ሲጨነቅ ይኖራል›› ይላል፡፡ ስለዚሀም ሠለስቱ ምዕት ያለመመርመር እንመን ያሉት፡፡ እኛ ሥጋውያ ሰዎች እንኳን ምሥጢራተ እግዚአብሔርን ልንመረምርና ልናውቅ ቀርቶ በውስጣችን ስላለች ነፍስ እንኳን ምን እንደሆች ግብሯን ጠባይዋን ባሕርይዋን መርምረን አልደረስንበትም፡፡ በውስጣችን ያለችን ነፍስ መርምረን ካለደረስንባት ረቂቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ምሥጢራትማ እንዴት? ስለዚህ እግዚአብሔር ያሳወቀንን
    /የገለጠልንን/ ያህል መረዳት እንጂ መመርመር ጉዳት እዳለው ከላይ የጠቀስናቸው ያስረዱናል፡፡

    ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በሚታይ መንፈሳዊ አገልግሎት የማይታይ መንፈሳዊ ጸጋና በረከት የምናገኝባቸው የዘለአለም ሕይወት የሚያሰጡን መንፈሳዊ መሣሪያዊች ናቸው፡፡ ይኸውም ለዘላለም ተሰውሮ የነበረ አሁን በሐዲስ ኪዳን በወንጌል የተገለጠ ከእግዚአብሔር የወጣ የእውነት ቃል /ትምህርት/ እና እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ ድኅነትን ለዓለም ሁሉ ማቅረቡ ነው፡፡ ሮሜ 16፡26 ፣ ኤፌ 1፡9 

    የምሥጢር አከፋፈል

    ምሥጢር በ3 ዓይነት አከፋፈል ይከፈላል፡፡

    1. ጊዜያዊና ፣ ዘለአለማዊ

    ጊዜያዊ ምሥጢር፡- ብዙዎች የማፈያውቁት ጥቂቶች ብቻ የሚያውቁት ጊዜሊፈታው የሚችል ማለት ነው፡፡

    ዘለአለማዊ ምሥጢር፡- ከእግዚአብሔር በቀር በማንም የማይታወቅ፡፡ ለምሳሌ 5ቱ አእማደ ቤተክርስቲያን ስንመለከት በእምነት ብቻ እግዚአብሔር ያሳወቀንን ያህል ስለምንረዳ ዘላለማዊ ምስጢር ተባሉ፡፡ ይህንንም አባቶች፡- ‹‹ የገናናነቱን ነገር ለመመርመር የነቢያትና የሐዋርያት አንደበት አይታቻለቸውም፡፡ ስለዚህ አንመርምር ጥልቅነቱንም አንጠናቀቅ›› አባ ሕርያቆስ በማለት ያስረዱናል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያም ‹‹ የእግዚአብሔርን የጌትነቱን ነገር በነገር ትችት መመርመር ድፍረትም ኃጢአትም ነው›› የሚል ቃል ተናግሯል፡፡
     
    1. የፈጣሪና ፣ የፍጡራን

    የፈጣሪ ምሥጢር፡- ተምረው ተመራምረው የማይደረስበት በእምነት ብቻ የሚገለጥ ምሥጢር ነው፡፡ ፍጡር ስለፈጣሪ ሊያውቅ የሚችለው የተገለጠለት ያህል ብቻ ነውና፡፡ ይህ ምሥጢር በተለይ የተገለጠው በሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ይህም ቢሆ ግን እንደየብቃታችን እንጂ ለሁሉም እኩል አይገለጥም፡፡ ሮሜ 16፡25

    የፍጡራን ምሥጢር፡
    -1ኛ የሰዎች ፤በሰዎች መካከል በድብቅ ለተወሰነ ጊዜ በምጢር ከቆየ በኋላ የሚገለጥ ነው፡፡

    -2ኛ የመላዕክት ምሥጢር፤ መላእክት ረቅቃን ከመሆቸው የተነሳ የሰው ላጅ ስለመላእክት የሚያውቀው በመጸፍ የተገለጠለትን ብቻ ነው፡፡ ቅዱሳን እንኳን ሲበቁ ምሥጢራቸውን ያውቃሉ እንጂ ለሁሉም ኩል አይገለጥም፡፡


    1. ፍጻሜ ያለውና ፣ ፍጻሜ የሌለው
    ፍጻሜ ያለው፤ የሰው ልጆች ሊረዱ በሚችሉበት መንገድ ስለሚገለጡ የፍጡራን ምሥጢርና ጊዜያዊ ምሥጢር ፍፃሜ ያላቸው ምሥጢራት ይባላሉ፡፡

    ፍጻሜ የሌለው፤ የፈጣሪና የዘለአለማዊ ምሥጢር ፍፃሜ የሌላቸው ምሥጢራት ናችው፡፡ ምክንያቱም ከሰው ልጅ አእምሮ በላይ ስለሆኑ ነው፡፡
    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top