• በቅርብ የተጻፉ

    Friday 6 November 2015

    የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ሦስት

    3ኛ. ሰላም

    ሰላም  ሐዋርያው  ቅዱስ  ጳውሎስ  ከገለጸው  የመንፈስ  ፍሬ  ፍቅርን፣  ደስታንና  ሰላምን  አስቀድመን  ተመልክተናል፡፡  አሁን  ዳግም  ወደ  ሰላም  እንሸጋገራለን፡፡  በቅድሚያ  በቅዱስ  መጽሐፍ  በጸሎት  እና  በሕይወታችን  ሰላም  ያለውን  አስፈላጊነት  እና  ጥቅም  በመግለጽ  እንጀምር፡፡  ሰላም  በአጭሩ  ለሰዎች  ሕይወት  በጣም  አስፈላጊና  የእግዚአብሔር  ስጦታ ነው፡፡  በመቀጠልም  ስለሰላም  ሦስት  መሠረታዊ  ነገሮችን  እንመልከት፡ - 
    1.  ከእግዚአብሔር  ጋር  ሰላም  እና ከእግዚአብሔር  የሚገኝ  ሰላም  
    2.  ሰላም  ከሰዎች  ጋር 
    3.  ከራስ  ጋር  የሚረግ  በልብ  ያለ  ውስጣዊ  ሰላም  የሰላም  አስፈላጊነት  ሰላም  ለሰው  ልጆች  ሕይወት  በጣም ወሳኝና  አስፈላጊ  ነው፡፡  ከሰላም  ውጭ  ቤተሰብም  ሆነ  ማኅበረሰብ  ሊረጋጋ  አይችልም፡፡

    በጸጥታ  የሚኖር  ሰው  የለም  አይኖርምም፡፡  ምክንያቱም  በዓለም  መኖር  የምንችለው  ከብዙ  ውጣ  ውረድ  ጋር  በመሆኑ  ነው፡፡  ይሁን  እንጂ  ያለሰላም  በጸጥታ  መኖር  አይታሰብም፡፡  ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  ለደቀመዛሙርቱ " ሰላምን  እተውላችኋለሁ  ሰላሜን  እሰጣችኋለሁ  ልባችሁ  አይታወክ  አይፍራም " ዮሐ .14 ፡ 27  ብሏቸዋል፡ :

    ሰላም  ቅዱሳን  መላዕክት  በጌታችን  ልደት  ዕለት " ክብር  ለእግዚአብሔር  በአርያም  ይሁን  ሰላምም  በምድር …" ሉቃ .3 ፡ 14  በሥርዓተ  ቅዳሴ " ሰላም  ለሁላችሁ ይሁን " የሚለው  ቃል  በሚቀድሰው  ካህን  ቅዳሴው  እስኪያልቅ  ድረስ  ብዙ  ጊዜ  በተደጋጋሚ  የሚሰጥ  ቡራኬ  ነው፡፡  በሌላ  መልኩ  ሰላም  ስንል  አንድ  ሰው  በውስጡ  የሚሰማው  የዕረፍት  ስሜት  ሰላም  ይባላል፡፡  ሰላም  ከሌለው  ጋር  በስምምነትና  በአንድነት  መኖር  ነው፡፡  እውነተኛ  ክርስቲያን  በውስጡ  የጭንቀት  መንፈስ  አይኖርበትም  በማኅበራዊ  ኑሮ፣  ከቤተሰቡ  ጋር፣  ከሚሠራበት  መ / ቤት  ሠራተኛ ጋር፣  ከጐረቤቱ  ጋር፣  ከትምህርት  ቤቱ  ጓደኞች  ጋር፣  ከሰው  ሁሉ  ጋር  በኑሮው  ውስጥ  ሁከት  አይፈጥርም፡፡    

    ጌታ  ከትንሣኤው  በኋላ  ሁለቱን  ማርያም  ባገኛቸው  ጊዜ  ሰላምን  ሰጣቸው  ማቴ .28 ፡ 8  ደቀ መዛሙርቱ  ተሰብስበው  በነበሩበት  በመምጣት " ሰላም  ለእናንተ  ይሁን " ዮሐ .20 ፡ 19  ብሎአቸዋል፡፡  ዳግመኛም  ጌታችን  ደቀ መዛሙርቱን ሲልክ  ወደ  ምትገቡበት  ቤት  ሁሉ  አስቀድማችሁ " ሰላም  ለዚህ  ቤት  ይሁን  በሉ፡፡ " በዚያም  የሰላም  ልጅ  ቢኖር  ሰላማችሁ  ያድርበታል  አለዚያም  ይመለስላችኋል  ሉቃ .10 ፡ 5 ፡፡ 

    እመቤታችን  ቅድስት  ድንግል  ማርያም  ኤልሳቤጥን  በጐበኘችበትወቅት  ሰላምታ  በመስጠት  ነው  የጀመረችው፡፡  ኤልሳቤጥ  የማርያምን  ሰላምታ  በሰማች  ጊዜ  ጽንሱ  በማህፀኗ  ዘለለ  በእርሷም  መንፈስ  ቅዱስ  ሞላባት  ሉቃ .1 ፡ 14 ፡፡  ይህ  ሰላምታ  ምን  ያህል  የሚያስደስት  ነው፡፡ አባቶቻችን  ሐዋርያትም  መልዕክቶቻቸውን  ለመጀመር  ፀጋና ሰላም  ለእናንተ  ይሁን  የሚል  ቃል ተጠቅመዋል  ሮሜ 1 ፡ 7  ፣ 1 ቆሮ .1 ፡ 2 ፡፡ 

    በብዙ  ውይይቶችና  ፣  ስብሰባዎች፣  ጉባዔዎች  መካከል  ሰላም  ትልቁን  ቦታ  የያዘ  ነው፡፡ ሐዋርያው " የጽድቅም  ፍሬ  ሰላምንለሚያደርጉት  ሰዎች  በሰላም  ይዘራል " ያዕ .3 ፡ 18 በአብዛኛው  በሰው  ልጅ  ግንኙነት  ወቅት  ሰላምየንግግር  መጀመሪያና  መጨረሻም  ነው፡፡  ነብዩ  ኤልሳዕ  ከሶርያው  ከንዕማን  ጋር  ያደረገው  ንግግር " በሰላም  ሂድ 2 ነገ .5 ፡ 19  በሚልቃል  ተሰናብቷል፡፡ "  መድኅነዓለም  ኢያሱስ  ክርሰቶስም ከኃጢአተኛዋ  ሴት  ጋር  ያደረገው  ንግግር " በሰላም  ሂጂ "  ሉቃ 7 ፡ 50  በሚል  በምህረት  አስናበታት፡፡ 

    ሰላም፡ -  ከእግዚአብሔር  እና  ከሰው  ሁሉ  ጋር  ሊኖረን  ይገባል፡፡  ሰው  በጥንተ  ተፈጥሮው  ከእግዚአብሔር  ጋር  ሰላም  ነበር፡፡  ነገር  ግን  በኃጢአት  ሲወድቅ  ከእግዚአብሔር  ጋር  የነበረውን  ያን  ሰላም  አጣ፡፡  ይህም  ሰላም  ማጣት  የመጀመሪያው  ልጅ  በወንድሙ  እጅ  በሞት  አሳልፎአል  ዘፍ 3 ፡ 4 ፡፡  ከዚያም  ወደ  ትውልዱ  ቀጠለ፡፡  ሮሜ .5 ፡ 1" እንግዲህ  በእምነት  ከጸደቅን  በእግዚአብሔር  ዘንድ  በጌታችን  በኢየሱስ  ክርስቶስ  ሰላምን  እንያዝ " ይላል፡፡  ይህ  ሰላም  በቀራንዮ  አደባባይ  የተሰቀለው  ጌታችን  መድኃኒታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ  ስለ  እኛ  ያፈሰሰው  የቅዱስ  ደሙ  ፍሬ  ነው፡፡  እርሱ  ሰላማችን  ነውና … የጥል  ግድግዳን  በሥጋው  ያፈረሰው …  ኤፍ .3 ፡ 14  እርሱ  በሰማይና  በምድር  መካከል  ሰላምን  አደረገ፡፡  የዳዊት  መዝሙር " እግዚአብሔር  ሕዝቡን  በሰላም  ይባርክልን  መዝ .28 ፡ 11 ፡፡ 

    እውነተኛ  ሰላም  የሚኘው  በእግዚአብሔር  ነው " ፡፡  ቅዱስ  ጳውሎስ " አአምሮንም  ሁሉ  የሚያልፍ  የእግዚአብሔር  ሰላም  ልባችሁንና  አሳባችሁን  በክርስቶስ  ኢየሱስ  ይጠብቃል  ፌል .4 ፡ 7 ፡፡ " በሁለት  ሰዎች  መካከል፣  በጓደኛ፣  በትዳር፣  በመ / ቤት፣  በጐቤት፣ …. ማንኛውም  ዓይነት  ግጭት  አለመስማማት  ከተፈጠረ  መታረቅ  አለባቸው  ማቴ .5 ፡ 23 ፡፡ " በመሰዊያው  ፊት  መባህን  ትተህ  ሂድ  አስቀድመህም  ከወንድምህ  ጋር  ታረቅ  ያለው  ለዚህ  ነው፡፡ "    

    ቅድስት  ቤተክርስቲያን  ቅዱስ  ቁርባን  ከመቀበላችን  በፊት  እንድንታረቅ የምታስተምረው  ለዚህ  ነው፡፡  ነገር  ግን  ለብዙ  ጠላቶች  ወይም  በላንጣዎች  እርቅን  መፈጸም  አስቸጋሪ  ሊሆን  ይችላል  በማለት  ሐዋያው " ቢቻላችሁስ  በእናንተ  መካከል / በኩል / ከሰው  ሁሉ  ጋር  በሰላም  ኑሮ " ሮሜ ..12 ፡ 18 ፡፡  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክረስቶስ  የታወከውንና  የተጨነቀውን  ልቦናለማረጋጋትና  ለሕይወታችን  ዕረፍት  ለመስጠት  ሰላሙን  ትቶልን  ሄዷል፡፡ " ሰላምን  እተውላችኋለሁ  ሰላሜን  እሰጣችኋለሁ " ሲል  አስተምሮናል  ዮሐ .14 ፡ 27 ፡፡  ጌታ  ሰላምን  ከተወልን  እኛ  ልናገኘው  የምንችለው  ደግሞ  ይህንን  ሰላም  አጥብቀን  በመፈለግና  በመከተል  ነው  መዝ .33 ፡ 14 ፡፡  በኤፌ . 6 ፡ 14  ላይ " ክፋትንም  በክፋት  ላይ  ይጨምራል  ክፉዎችም  ሰላም  ሳይኖር  ሰላም  ይባሉ  እንጂለክፉዎች  ሰላም  የላቸውም፡፡ "  ውድ  አንባቢዎቼ  በልቡ  ሰላም  የነገሠበት  መንፈሳዊ  ሰው  ሞትን  ፈጽሞ  አይፈራም  የተቀደሰ  ሕይወት  መምራት  የሞት  ፍርሃትን  ከአንድ  ሰው  ልብ  ያስወግዳል፡፡  ይልቁንም  በእንደዚህ  ዓይነት  ቅድስና  የተዘጋጀ  ሰው  ሞትን  ይመኛል፡፡  ምክንያቱም  ይህ  ወደ  ክርስቶስና  ወደ  መላዕክት  እንዲሁም  ወደ  ጻድቃን  ኅብረት  ይወስደዋልና  ነው፡፡ 

    ክርስቲያን  ሰማዕታት  እና  የቅዱሳን  የበረሃ  አባቶች  ታሪክና  ሕይወት  ለዚህ  ደርጊት  መልካም  ምስክር  ነው፡፡  ሰማዕታት  ሞትን፣  ሥቃይን፣  ዛቻን፣  ትችትን፣  መነቀፍን፣ እንዲሁም  ገዢዎችን / ባለጊዜዎችን / ለፍርድ  መቅረብን እና  እስር  ቤቶችን  አይፈሩም፡፡  ይልቁንም  በደስታና  በሰላም  ይዘምራሉ፡፡  የሰላምና  የልብ  ሙሉነት  ባለቤት  ለመሆን  የእግዚአብሔርን  የጥበቃኃይል  ዘወትር  በእምነት  ማስታወስ  ያስፈልጋልና  ሁላችንም በዚህ  በኩል  እንበርታ …  እያንዳንዱ  ችግር  መፍትሔ  እንዳለው  ሁሉ  እግዚአብሔርም  በሕይወታችን  ውስጥ  ብዙ  መፍትሔዎች  አሉትና  በነገሮች  ሁሉ  አንፍራ፡፡  በሰዎቹ  ዘንድ  የማይቻው  በእግዚአብሔር  ዘንድ  ይቻላልና፡፡  ከዚህም  በተጨማሪ  ለሚያምን  ሁሉ  ይቻለዋል፡፡  ማር . 9 ፡ 23 ፡፡ 

    የሰላም  አምላክ  ቀሪውን  ጊዜያችንና  ሕይወታችንን ከእኛ  ከሆኑት  ጋር  ሁሉ  ይጠብቅልን  አሜን፡፡  ይቆየን ………… ይቀጥላል  ወስብሐት  ለእግዚአብሔር

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የመንፈስ ፍሬዎች ክፍል ሦስት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top