ሜሮን ቃሉ የፅርዕ ነው የሚሸት፣ የሚጣፍጥ፣ ልብ የሚመስጥ መዐዛ ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት የሚመስል ነው፡፡ “ሜሮዲያ” ይላል፡፡ ግሪክ “መዐዛ” ማለት ነው፤ በግዕዝም ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ ዕፀዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡
ጥቅሙና አገልግሎቱ በብሉይ ኪዳን ሜሮን ለእግዚአብሔር የኾነው ኹሉ የሚታተምበት፣ ያደፈው የረከሰው የሚቀደስበት ቅብዕ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚሾሙ ሌዋውያን ካህናት /አራት ሽቱ አምስተኛ ዘይት/ የሚቀቡት ዕብፅ ይህ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እስራኤልን የሚጠብቁ የእግዚአብሔር እንደራሴዎች ነገሥታትም “መሢሐን” የሚባሉት በዚህ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡
“መሢሕ” ማለት ቅቡዕ የተቀባ ማለት ነውና፡፡ ይኸም ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተ መቅደስ እንጅ ለተራ አገልግሎት አይውልም ነበር:፡ ከብሉይ ኪዳን በፊት የነበረው አካሔዱን ከእግዚአwሔር ጋር ያደረገው ከአሥሩ በው አንዱ ሔኖክ ከመሰወሩ በፊት ሜሮን ተቀብቶ እንደ ተሰወረና ልማደ ሰብእ እንደ ጠፉለት ይነገራል፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና ከዚህ ላይ አነሳነው እንጅ በምሳሌነት ሲሰራበት የኖረው ይህ የነርሱ ቅብዕ በቤተ ክርስቲያን ላለው ቅብዓ ሜሮን ጓዱ ዘመዱ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያኑንስ እንደሚከተለው እንመልከት፡፡
በሐዋርያት ጊዜ ማንኛውም አማኝ ከተጠመቀ በኋላ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ የሚቀበለው በሐዋርያት አንብሮተ ዕድ ማለት ሐዋርያት እጃቸውን ሲጭኑበት እንደነበርና፣ ከሐዋርያት በኋላ የተነሱ ኤጲስ ቆጶሳትም ይህንኑ ሲሰሩበት መቆየታቸውን ስለ ምሥጢረ ጥምቀት በተነጋገርንበት አንቀጽ አንስተነው ነበር፡፡ የምዕመናን ቁጥር ሲበረከት ኤጲስ ቆጶሳትም በየቦታው ሜሮን እያፈሉ በሜሮኑ ላይ እየቀደሱ ወደ የአብየተ ክርስቲያናቱ እንዲልኩና፣ የሚጠመቁ ምዕመናንም በእነሱ አንብሮተ ዕድ ፈንተ ሜሮን እንዲቀቡ በሎዶቅያ ጉባኤ ተወሰነ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አማኞቹ ተጠምቀው ከማጥመቂያው ሲወጡ ያጠመቋቸው ቄስ ሜሮን ይቀባዋል፡፡
በአንብሮተ ዕድ ፈንታ ሜሮን እንዲተካ ሥርዓት የተሰራው ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ቅብዓ ሜሮን በብሉይ ኪዳን በምሳሌነት ይሰራበት ከነበረው ሌላ አዲስ ኪዳን የጻፉ ቅዱሳን ሰዎችም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዓት ይሉት ነበር፡፡ ቅብዕን የመንፈስ ቅዱስ ማህተም ይሉታል፡፡ ማህተም ያለበት ኹሉ የማንነቱ እንደሚታወቅ ዕመናንም የመንፈስ ቅዱስ ገንዘቦች መኾናቸው የሚታወቀው
የሚረጋገጠው በጥምቀት በቅብዓ ሜሮን ሲታተሙ ነውና፡፡
የምዕመናን ሁለተኛ ልደት ከውና ከከመንፈስ ስለኾነ ምዕመናን በውሀ ሲጠመቁ ከውሀ፣ ሜሮን ሲቀቡ ከመንðፈ ቅዱስ ይወለዳሉ፡ ስለ ሜሮን አወጣጥ የሜሮን አፈላል በጥን ዊት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት እንደሚ ወቀው ጌታ ከተገረፈባ†ቸ ና ከተሰቀ ባቸው ዕፀዋት ተሰብስቦ ተነጥሮ ነው ከተነጠረ በኋላ ኤጲስ ቆጶሳት ተሰብስበው ምህላና ጸሎት ያደርሱበታል ይቀድሱበታል፡፡
በኋላም በአንብሮተ ዕድ ባርከው ወደ የሀገረ ስብከታቸው ይከፋፈሉታል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዓመታት ሜሮን የሚመጣላት ከእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ አሁን ነጻነቷን ካገኘት በኋላ ግን ፈልሀተ ሜሮን አስፈላጊ ሲኾን ስለ መንበረ ማርቆስ ክብር የኢትዮጵያ ጳጳሳት ወደ ካይሮ እየተላኩ ከግብጽ ጳጳሳት ጋር ኹነው የፍልሀተ ሜሮንን ሥርዓት ይፈጽማሉ፡፡ የኢትዮጵያንም ድርሻ ተካፍለው ያመጣሉ፡፡ በግብጽ የሚደረገው ፍልሀተ ሜሮን ሁል ጊዜ በሰኔ ወር የመጀመሪያው ፍልሀተ ሜሮን ተደረገ የሚባለው በሰኔ ስምንት ቀን ነውና በመለካውያን ዘንድ ሜሮን የሚፈላው በጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቅዳሴ ላይ ነው፡፡ ግሪኮች የቁስጥንጥንያ መንበር ለማክበር ሲሉ ጳጳሶቻቸውን ወደ ቁስጥንጥንያ ልከው በዚያ ፍልሀተ ሜሮን ያደርጋሉ፡፡ ሌሎች መለካውያን ግን በየቦታቸው ነው፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም የሜሮንን ምሥጢርነት ትቀበላለች አፈጻጸሙ ግን እስካአሁን ካየነው የተለየ ነው፡፡
የሜሮን አቀባብ
በኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ከላይ እንደገለጥነው የሜሮን አቀባብ ወዲያ ከጥምቀት አያይ ይፈጸማል፡፡አቀባቡም እንደዚህ ነው፡፡ የተጠመቀው ሕጻን እንደኾነ በክርስትና ዋሱ እቅፍ እንዳለ ይቀባል፡፡ አዋቂ እንደኾነ ከማጥመቂያው ወጥቶ እንደቆመ ቄሱ ሜሮኑን በአውራ ጣቱ እየጠለፈ “እቀብአከ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እያለ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በትዕምርተ መስቀለ ያትመዋል በመጀመሪያ ግንባሩን ያትመዋል አዕምሮው የተባረከ እንዲኾን ግራ ቀኝ አይኖቹን ያትመዋል ዓይኖቹ የእግዚአብሔርን እውነት እንዲያዩ፣ ግራ ቀኝ ጆሮቹን ያትመዋል ጆሮዎቹ የእዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ፣ አፉን ከናፍሩን ያትመዋል፣ እውነት እንዲናገር የእግዚአብሔርን ጥበብ እንዲማር፣ ደረቱን ያትመዋል፡፡ ልቡ ቅን እንዲያስብ፣ ግራ ቀኝ እጆቹን ይቀባዋል
እጆቹ ለመልካም ሥራ እንዲፋጠኑ፣ ግራ ቀኝ እግሮቹን ይቀባዋል እግሮቹ ወደ መልካም ሥራ እንዲፋጠኑ፡፡ በአጠቃላይ መላ ሰውነቱን ይቀባዋል በኋላ ሰውነቱ የእግዚአብሔር ማደሪያ እንዲሆን፡፡
በሜሮን የሚ ተሙ በሜሮን የሚቀደሱ አዲስ ክርስቲያኖች ብቻ አይደሉም፡፡ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ተሰርቶ ካለቀ በኋላ አገልግሎት የሚ መርበት በሜሮን ከተቀባ በኋላ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ንዋያተ ታቦት፣ ጻህል፣ ጽዋ፣ ዕርፈ መስቀል፣ መሶበ ወርቅ፣ ማዕጠንት፣ ማህፈድ፣ መንበር፣ እነዚህና የመሳሰሉትም ለአገልግሎት ከመቅረባቸው በፊት በሜሮን ይታተማሉ ልዩ ጸሎትና ቡራኬም ይፈጸምባቸዋል ከዚያ በኋላ ተራ ሥራ አይሰራባቸውም፡፡
በግሪክና በሌሎች መለካውያን አቀባቡ ከእኛው ጋር ተመሳሳይነት አለው ከጥምቀት ጋር አያይዘው ይቀባሉ ሲቀቡ ግን “ማህተመ ፀጋ ዘመንፈስ ቅዱስ ዝውእቱ” እያሉ ነው የሚቀባው ቄሱ ነው፡፡
በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በፊት እንደተናገርነው ምሥጢረ ሜሮን የሚፈጸመው ሕጻኑ ተጠምቆ ለአሥር አመታት ያህል ከቆየ በኋላ ነው፡፡ የሚቀባውም ኤጲስ ቆጶሱ ብቻ ነው፡፡ ቄስ የመቅባት መብት የለውም ፕሮቴስንታቶች ግን የሜሮንን ምሥጢርነት አይቀበሉም፡፡
0 comments:
Post a Comment