አንድ ሶርያዊ ክርስቲያን የሚከተለውን ደብዳቤበ1983 ዓ.ም ጽፎ ነበር፡፡ ደብዳቤው እንዲህይነበባል፡-
«እስከ 1970 ዓ.ም (የተወለደው በ1943 ዓ.ምነው) «በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት ሥጋወደሙ እቀበል ነበር፣ አሥራት አወጣ ነበር፣ገዳማትን ለመርዳት የተቋቋመ ማኅበር አባል ሆኜሌት ተቀን እሠራ ነበር፣ ሁል ጊዜ በመንፈሳዊሕይወቴ ውስጥ የመለወጥ ስሜት ነበረኝ፣ለመማር፣ ለመጾምና ለመጸለይ የነበረኝን ትጋትአስታውሰዋለሁ፡፡ ይሁን እንጂ በ1970 ዓ.ምመንፈሳዊ ሕይወቴ ባለበት ቆመ፡፡ እንኳን ከበፊትየተሻለ ምግባር ልፈጽም የነበረኝንም እየተውኩትመጣሁ፡፡ ድካምና መሰልቸት ሕይወቴንተጫጫነው፡፡ ራዕይ አጣሁ፡፡ ከፊት ለፊቴ ምንምነገር አይታየኝም፡፡ ግድግዳ ያለ ይመስለኛል፡፡ቤተክርስቲያን በበለጠ ለማገልገል የነበረኝ ጉጉትሁሉ ሞተ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በማንኛውም ደብዳቤዓመተ ምሕረቱን 1970 እያልኩ እጽፋለሁ፡፡ እስከአሁን ድረስ(1983 ዓ.ም ማለቴ ነው) በኔ አቆጣጠር1970 ዓ.ም ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ በኑሮዬውስጥ ምንም የተለወጠ፣ ያደገ ወይምየተስተካከለ ነገር የለምና፡፡ ብፁዕ አባታችን፡-እባክዎ ምክርዎን በመለገስ ወደ 1971 ዓ.ምያሸጋግሩኝ;»
ሕይወት ካልተለወጠ፣ ካላደገ፣ ሃይማኖት ካልሰፋ፣ምግባር ካልጸና ፣ ትናንት ያሸነፉንን ኃጢአቶች ዛሬካላሸነፍን፣ የደከመውን አበርትተን፣የተሰበረውንካልጠገንን፣ ዘመን ተለውጦ ዘመንቢተካም፣ የምድርን ዕድሜ እንቆጥራለንን እንጂ እኛእንደሆንን እንደቆምን ነን፡፡ አንዳንዶቻችን ያኔ ሕጻንሆነን ሥጋ ወደሙ እንደተቀበልን፣ሌሎቻችንበወጣትነት ለሰንበት ት/ቤትና ለጽዋመርሐ ግብር በነበረን ትጋት ላይ ሌሎችምበማስተማር፣ ቤተክርስቲያንንበማሰራት፣በማስቀደስ በመጸለይና በመጾም፣በነበረን የጥንት ምግባር አንዳንዶችም ወደምንኩስና (ምናኔ) ሲገቡ በነበራቸውየወጣኒነትትጋት እዚያው ላይ ዓመተ ምሕረታችንቆሟል፡፡
አዲስ አበባ አራት ኪሎ መሐል የአርበኞች ኃውልትአለ፡፡ እዚያ ኃውልት ጫፍ ላይ ሰዓት ተሰቅሏል፡፡ሰዓቱ የሚያመለክተው አርበኞች አዲስ አበባየገቡበትን ሰዓት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ቆሟል፡፡ የዛሬውትውልድ ያንን ሰዓት ሲያየው ጀግኖች አባቶቹጠላትን ድል አድርገው ሀገሪቱን ነጻ ያወጡበትንጊዜ ያስብበታል፡፡ ያ ሰዓት የጥንቲቱን ተግባር ብቻእያመለከተ ቆሟል፡፡ የዛሬውን ትውልድ ጀግንነትናዝና የሚያሳይ ሰዓት ግን የለም፡፡ የብዙዎቻችንሰዓት ቆሟል፡፡ በአንድ ወቅት የሠራነውን መልካምስራ፣ የነበረን መንፈሳዊ ትጋት፣ የሃይማኖትጥንካሬና ሰማይ ጥግ የደረሰ ዝና እያመለከተቆሟል፡፡ ዛሬ በአቡሻህር አቆጣጠር2007 ዓ.ምነው:: በእኛ አቆጣጠርስ ስንት ነው; ያ ሶርያዊክርስቲያን «በኔ አቆጣጠር 1970 ዓ.ም ነው»ብሏል፡፡ እርሱ የነበረበትን ዘመን ግን እስከ1983ዓ.ም ነበር፡፡
የዘመን መለወጫን በዓል አከበርነውምአላከበርነውም ዘመኑ መለወጡ አይቀሬ ነው፡፡እያንዳንዷን ቀን ተጠቀምንም አልተጠቀምንምጊዜው መሮጡ አይቀርም፡፡ እርሱ የራሱን ጊዜይቆጥራል፡፡ ይለወጣል፡፡ እኛስ; እስቲ ጊዜ ሰጥተንራሳችንን እንመርምረው፡፡ በሃይማኖት እየጸኑ፣በምግባር እየበረቱ፣ በትጋት እየጨመሩ፣በመንፈሳዊ እውቀት እያበሩ፣ ሰማዕትነትን ይበልጥእያፈኩ ካልሄዱ ዘመኑ ብቻውን ቢቀየር «እንኳንአደረሳችሁ».ያስብላልን; የአክሱምንም አደባባይየጎበኘ ሰው ሦስት ነገሮችን መታዘብ ይችላል፡፡ተጠርቦ ተቀርጾ ሃውልት የሆነ ድንጋይ አለ፡፡ ሃውልትለመሆን ተጠርቦ ቅርጽ ሳይወጣለት ልሙጥ ሆኖየቀረ አለ፡፡ ለሀውልትነት ተመርጦ ሳይጠረብሳይቀረጽ የቀረ አለ፡፡ በመንፈሳዊ ጉዞም እነዚህሦስቱ ነገሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ ለሰማያዊ ዋጋተመርጠው በብዙ ፈተና ተጠርበውና ተቀርጸውጉዞአቸውን የፈጸሙ አሉ፡፡ ተመርጠው ተጠርበውግን ገና ቅርጽ መያዝ ሲቀራቸው ባሉበት የቀሩ አሉ፡፡በሌላ በኩል ተመርጠው ከመጡ በኋላ ከዚያ ያለፈተግባር ላይ ያልዋሉም አሉ፡፡ የእነዚህ የሦስቱምየዘመን አቆጣጠራቸው ይለያያል፡፡ አንዱ በደረሰበትዓ.ም ሌሎቹ አልደረሱምና፡፡
በወንጌል ታሪኩ የተጠቀሰው የጠፋው ልጅ አባትልጁ ከጠፋበት ሀገር ሲመለስ «ይህ ልጄ ሞቶ ነበርህያው ሆኗል».ብሎ ነበር የተናገረው፡፡ ያ ልጅ እኮይንቀሳቀሳል፣ ይበላል፣ ይጠጣል ግን ሞቷል ተባለለምን; የሱ የዘመን አቆጣጠር ከአባቱ ቤት ሲጠፋመቁጠሩን አቁሞ ነበርና፡፡ በመንፈሳዊ ጉዞ የነበረውለውጥ ስላቆመ ሞተ ተባለ፡፡ ትልቁ ጥያቄ ማንተለወጠ ነው፡፡ ዘመን ተለወጠ; ሰው ተለወጠ;ወይስ ሁለቱም ተለወጡ; ዘመን ይለወጣል፡፡አይቀሬ ነው፡፡ የስነ ፍጥረት ስርዓት ሁሉየእግዚአብሔርን ህግ ሳያፋልስ ይኖራልና፡፡አስቸጋሪው ነገር እርሱ አይደለም፡፡ እስከ ዘመነምጽዓት ዘመን ይመጣል፣ ያልፋል፣ በሌላ ይተካል፡፡ሰው ተለወጠ; ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት ግንከባድ ነው፡፡ ይህን ጥያቄ ከባድ ያደረገው በሰውኑሮ ውስጥ ሦስት ዓይነት ለውጥ ስላለ ነው፡፡በመንፈስ መለወጥ፣
በአካል መለወጥ፣ በባሕላዊም ይሁን በዘመናዊመንገድ በሚገኝ እውቀት የሰው እውቀትይለወጣል፣ ያድጋል፣ ይሰፋል፣ ይጎለምሳል፡፡ወደደም ጠላም የሰው አካል የተፈጥሮውን ሂደትጠብቆ ይለወጣል፣ ጽንሱ ይወለዳል፣ ሕጻኑ ያድጋልወጣት ይሆናል፣ ወጣቱ ይጎለምሳል፣ ጎልማሳውያረጃል፣ አካላዊ ጸባዩም በዚያው ልክ ይለወጣል፡፡ትልቁ ፈተና መንፈሳዊ ለውጡስ የሚለው ላይሲደርስ ነው፡፡ መንፈሳዊ ለውጥ ከነዚህ ከሁለቱለውጦች የተለየ ነው፡፡ ተጋድሎ ከሥጋና ደም ጋርአይደለምና፡፡ የሰውየውን ታላቅ ጥረት፣ ሰማዕትነትእና የሃይማኖትን ጽናት የግድ ይላል፡፡ በዚህምየተነሳ በእውቀት ጎልምሰው፣ በዕድሜ አርጅተው፣በመንፈሳዊ ለውጥ ግን ገና ሕጻናት የሆኑ ወይምደግሞ በሕጸንነት እድሜ ላይ የጊዜ መቁጠሪያሰዓታቸውን ያቆሙ ብዙ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ ስለመንፈሳዊ ሕይወትና ስለ ሃይማኖት እጅግ ብዙየተማሩ በእውቀት ለሌሎች ሊተርፉ የሚችሉሌሎችን አስተምረው ለፍሬ ያበቁ ሰዎችበመንፈሳዊ ሕይወት ለውጣቸው ገና ወጣኒያንሆነው የሚገኙበት አጋጣሚ አለ፡፡ ስለዚህም ሌላየዘመን መለወጫ ከማክበራችን. አዲስ አመት ገባእያልን ዶሮና በግ ከማረዳችን. እንደምዕራባውያውኑ ወደ ኋላሩ (Count down)ከመቁጠራችን በፊት ለቀጣዩ ጥያቄ መልስእንፈልግ፡፡
ለውጥ በሌለው ሕይወት አቆጣጠር - ዛሬ ስንትዓመተ ምሕረት ነው ?
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
www.melakuezezew.info - ስንክሳር ድረ ገጽ
0 comments:
Post a Comment