• በቅርብ የተጻፉ

    Friday 13 November 2015

    ‹‹የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡››(ምሳ 10፡7)


    ክፍል ሁለት

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

    ከአብነት ተስፉ(AbinetZetewahido4@gmail.com)

    ውድ የዳረጎት አንባብያን ሆይ በቀደመው የመግቢያ ጽሑፋችን ጥቂት ለማለት ሞክሬያለሁ፡፡ አሁን ከዚያ የቀጠለውን እነሆብያለሁ፡፡ በመጀመሪያ እስቲ ‹‹መታሠቢያ ማለት ምንድ ነው?›› የሚለውን እንመልከት፡፡  መታሰቢያ የሚለው ቃል አሰበ ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን አስታወሰ፤ የሰራውን ስራ በህሊናው መረመረ፤አደነቀ፤ ከፍ ከፍ አደረገ፤ ህያው አደረገ ...ወዘተማለት ነው፡፡ ስለዚህ መታሰቢያ ማለት የአንድመጥፎም ሆነ ጥሩ ስራ እንዳይረሳ ማድረጊያ የማንኛውም ነገር መጠሪያ ነው፡፡ ስለዚህ የቅዱሳን (የፃድቃን) መታሰቢያ ማለት የቅዱሳንን ክብር ከፍከፍ ማድረጊያ፤ ስራዎቻቸውን ማስታወሻ፤ለዘለዓለም ህያው ማድረጊያ… ወዘተ ማለት ነው፡፡ይህንን ሁሉ ማድረግ መልካም እንደሆነ ጠቢቡ ሰለሞን በመጽሐፈ ምሳሌ 10፡7 ላይ ‹‹በረከትበጻድቅ ራስ ላይ ነው፡፡ የፃድቃን መታሰቢያ ምለበረከት ነው ይለናል፡፡››(ምሳ 10፡7)

    ታዲያ እንዴት እናስባቸው?

    ሌላው ወደ አዕምሮዋችን ጎራ የሚለው ጥያቄ ታዲያ ፃድቃን ‹‹እንዴት እናስባቸው?›› የሚለው ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም በልዩ ልዩ መልክ መሆን እንዳለበት በጠራ መልኩ ይነግረናል፡፡ ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ 10፡41 ላይ ‹‹ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ …›› ብሎ እንደተናገረ በተወለዱ በትተዓምር ባደረጉበት፣ ባረፉበት፣ ቃል ኪዳንበተቀበሉበት ቀን…ወዘተ በእነርሱ ስም በዓልበማድረግ፣ ለድሃዎች ምግብ፣ በመጠጥ እና ልብስ በመስጠት፣ ወይም በተለመደው ቃል በማዘከር ነው፡፡.ሌላው ደግሞ ቤቱ የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ፣ምስጋናው የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በእነርሱ ስም በመሰየም ነው፡፡ ለምሳሌ የቅዱስ ሚካኤል፣የቅድስት ድንግል ማርያም፣ የአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ...ወዘተ ብሎ በመሰየም ነው፡፡ በዚህም የሚሰዋው መስዋዕት የእግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ለክብራቸው መገለጫ ጽላቱን በእነርሱ ስም በመሰየም ስማቸውን ለዘላለም ህያው ማድረግ ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ የለየው፣ ያከበረው፣የቀደሰው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሆኖ ሳለነገር ግን ስለ ክብራቸው፣ ስለአዳኝነተቸው የዕምነትና የጠበሉን መጠሪያ በእነርሱ ስም በመሰየም ቤተክርስቲያን መታሰቢያ ታደርግላቸዋለች፡፡ ይህም የአቡነ ተክለሃይማኖት ዕምነት የኪዳነ ምህረት ጠበል ወዘተ… በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም ቅዱሳን በረድኤት ወደ ሰው ልጆች እየቀረቡ በአፀደ ሥጋ እንደነበሩበት ጊዜ ድውይ ይፈውሳሉ፣ ሽባ ይተረትራሉ፣ አጋንንትያወጣሉ፣ ለምፃም ያነፃሉ…ብቻ ልዩ ልዩ ድንቅ ተአምራትን ያደርጋሉ፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ክብር እንደመጋፋት የሚመስላቸው ደካማ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን ሰዎችራሱ እግዚአብሔር በነብዩ ኢሳይያስ አንደበት እንዲህ ይላቸዋል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።››(ኢሳ56፡4-5) ይላል፡፡ በእውኑ ከቤተክርስቲያን ውጪ የእግዚአብሔር ቤት የት ነው? ከስር ዝቅ ብሎ ራሱ ኢሳይያስ በቁጥር 7 ላይ ‹‹ቤቴ ጸሎት ቤት ይባላልና››  በእውኑ ከላይ ከተመለከትነው ውጪ መታሰቢያ መስጠትስ እንዴት ነው? በመሆኑም እግዚአብሔር እንኳ ከክብሩ ሲሰጥ ደግ ቸር ከሆነ፤ አንዳንዶች ተቃዋሚ መሆናቸው እስቲ ምን ይባላል?በነገራችን ላይ የዚህን አይነት መታሰቢያ ማድረግ በስጋቸው ለደከሙ የዘለዓለም መታሰቢያ ለሌላቸው ስጋዊ መልካም ነገርን ላደረጉ ሰዎችእንኳ ማደረግ የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ በሃገራችንበመዲናችን በአዲስ አበባ ውስጥ በታላላቅ ሰዎችስም ከተሰየሙ በርካታ ነገሮች መሃል በጥቂቱሃይሌ ገ/ስላሴ አውራ ጎዳና ፤ ቴዎድሮስ አደባባይ ፤ ዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ወዘተ… ይጠቀሳሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ለስጋቸው ደክመው ለሃገራችንመልካም ነገርን ስላደረጉ ከህዝቡ ዘንድ ለክብራቸው ይህ ከተደረገላቸው፤ ቅዱሳን ስለ እግዚአብሔር ብለው በበረሃ የቀን ሃሩሩን የሌትቁሩን ታግሰው፤ ሀብት ንብረታቸውን ጥለው፤እግዚአብሔርን ተከትልው በዋሻ በፍርክርክርታ ውስጥ በምናኔ ህይወት ተወስነው፤ በአላውያን ነገስታት ፊት ‹‹ወልድ ዋህድ›› ብለው ይህን ክብሩን ከመሰከሩለት ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህን ያህልክብር ቢቀበሉ ምን ይገርማል? እዚህ ላይ ‹‹የቴዎድሮስ አደባባይ›› ሲባል የቴዎድሮስ የግል አንጡራ ሀብት ለማለት ሳይሆን በህዝብ መሬት ላይስሙ እንደተጠራ ሁሉ፤ የቅድስት ድንግል ማርያምቤተክርስትያን ሲባልም ‹‹የእግዚያብሔር ያልሆነ የሷ ብቻ!!›› ለማለት ሳይሆን ስለ ክብሩዋ የተሰየመ የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ምክንያቱም የሚፈተተው ሥጋና ደም የጌታችንየኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ነው፡፡

    በቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ የቅዱሳን ስራዎቻቸውን ከትቦ በማኖር ለዘለዓለም ይዘከራሉ (ይታወሳሉ)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም በተለያዩ ቦታዎች ይህንን እውነት ይመሰክራል፡፡ ለምሳሌ የሐዋርያት ገድላችው በተዘገበበት የሐዋርያትሥራ፤ በራሱ ለሌሎች ቅዱሳን ሥራዎች በመጽሐፍ መልክ መጻፍ ምስክር ይሰጣል፡፡ ምክንያቱም በወንጌሉ በሐዋርያት አንቀጽ ለሁላችን የተዘገቡበርካታ ትእዛዛት አሉና ነው፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር በነብዩ ሚልክያሰ አንደበት እንዲህ ይላል ‹‹ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።››(ሚልክ 3፡16)  ታድያ በዚህ የመታሰቢያ መጽሐፍ(ገድል) ውስጥ ከቅዱሳን ክብር ይልቅ የእግዚአብሔርን ክብር እናገኛለን፡፡ ምክንያቱም ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፡፡›› (መዝ68፡35) ይለናልና ቅዱስ ዳዊት፡፡

    ሌላኛው በዚህ ክፍል ጽሑፋችን ውስጥ በመጨረሻ የምናየው በስብከታችን ውስጥቦታ መስጠት ነው ፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ እያለለምን በዐውደ ምህረታቹ ስለ ቅዱስት አርሴማ ቅዱስ ስራ ይዘከራል ለሚሉ ሰዎች መልስ የሚሆን ነው፡፡

     ለዚህም 3 ነገሮችን እናንሳ ፡፡

    1.ኛ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስብከት ስንመለከት ዝክረ ቅዱሳንየታከለበት ነው፡፡ ‹‹እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ፡፡››(ዮሐ 5፡35) ‹‹እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከልከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፡፡›› (ማቴ 11፡11) እያለ ስለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ያስተምር ነበር፡፡ ክርስቶስን አብነት ያደረገ ሁሉ ይህንፈለጉን ይከተላል፡፡

    2.ኛ አምላካችን መድኃኔዓለም ኢየሱስክርስቶስ እግሩን በእንባዋ ስለአጠበችውሽቶውን በራሱ ላይ ስላፈሰሰችለት ሴት ሲናገር‹‹እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለምሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያእንዲሆን ይነገራል።››(ማቴ 26፡13)›› ብላል፡፡ ታዲያ ይህቺ ሴት ጥቂት ነገር ስላደረገች ሥራዋ በዓለም ሁሉ ለመታሰቢያ ከተነገረእድሜ ዘምናቸውን ክርስቶስን የተከተሉ ፤ዓለምን ንቀው እግዚአብሔርን ብቻ የያዙ፤ ስለ ክርስቶስ መከራን የተቀበሉ ሰዎች እንዴትአብልጦ ስራቸው አይነገር? እርግጥ ነው በደንብ ይነገርላቸዋል(ይታወሳል )፡፡

    3.ኛ የክርስቶስ ፈለግ የተከተሉ የሐዋርያቱንትምህርት ብንመለከት እንኳን ዝክረ ቅዱሳን የታከለበት ነው ፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልዕክቱ በምዕረፍ 11 ላይከአቤል ጀምሮ በተለያ ዘመን ስለተነሱ ድንቅ ቅዱሳን እያነሳ የመዕልእክቱ ማጣፈጫ ቅመምአድርጒቸዋል፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ጰውሎስ ይህን የሚያደርገው የክርስቶስን ነገር ችላ ብሎሳይሆን የአምላኩን ፈለግ እየተከተለ ስለነበረ ነው፡፡ ታድያ እነዚህ ሰዎች ከቅዱስ ጳውሎስ ይበልጡ ይሆን? በአጠቃላይ ቅዱሳን ከላይ በተዘረዘሩት መንገድ እናስባቸው ዘንድ ቅዱስመጽሐፋችን ያዘናል፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስን ከልማድ የዘለለ እውቀት የሌላቸውሰዎች የእግዚያብሔርን ክብር ከፍ ከፍ ያደረጉ መስሏቸው አግዚአብሔርን ሲቃወሙ ማየት እጅግ ያስተዛዝባል፡፡ ለማንኛውም ታዲያ እናንተቅድስት አርሴማን  እንዴት ልትዘክሩ (ልታስታውሱ) አሰባችሁ? በእውኑ የእናታችን በረከት በሁላችን ይደርብን እያልኩኝ የዚህን ክፍል በዚሁ አበቃሁ፡፡ በቀጣይ ክፍል የመታሰቢያ (የዝክር) ጥቅም ምንድን ነው? ለሚለው በቂ ምላሽ ይዤ እቀርባለሁ፡፡ እስከዚያው ረድኤተ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!

     ወስብሐት ለእግዚአብሔር

    ወለወላዲቱ ድንግል

    ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን!!!!

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ‹‹የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡››(ምሳ 10፡7) Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top