• በቅርብ የተጻፉ

    Monday 9 November 2015

    ጰራቅሊጦስ



    ጰራቅሊጦስ በተለየ አካሉ መንፈስ ቅዱስየሚጠራበት የመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፡፡

     ጰራቅሊጦስ ማለት

    አጽናኝ  (መሰተፍሥሒ)

     የሚያስደስት (ከሳቲ)

     የሚገልጽ  (መስተሥርዪ) ኃጢአትንየሚያስተሰርይ የሚል ትርጓሜ አለው፡፡

    ከጌታችን ትንሣኤ ከሃምሳኛው ቀን ጀምሮእስከ ሰኔ አስራ ሰባት ድረስ ያለው ጊዜዘመነ ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡

    በዚህ ዘመን የሚዘመሩት መዝሙራትየመንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት መሰጠትንናየጌታችንንም ትንሣኤና ዕርገት የሚመለከቱናቸው፡፡

    እሥራኤላውያን የፋሲካን በግ ካደረጉ በኋላከግብጽ ባርነት ነጻ ወጥተዋል::

     ከግብጽ ባርነት እግዚአብሔር ነጻእንዳወጣቸው ለማዘከርም በየዓመቱየፋሲካን በዓል ያከብራሉ::

     ከዚህ በዓል ቀጥሎ ሰባት ሱባኤ ሲፈጸምማለትም በ50ኛው ቀን በዓለ ሰዊት / የእሸትበዓል / ያከብራሉ::

     መከር በደረሰ ጊዜ በመጀመሪያ ከሚወቁትእህል ለእግዚአብሔር መሥዋዕትየሚያቀርቡበት ነው፡፡ (ዘሌ.23፤1-39) 

     እነዚህንም በዓላት ለማክበር በዓለም ዙሪያተበትነው የሚኖሩት ሳይቀሩ ወደኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፡፡

    ሐዋርያት ዕርገቱን ዐይተው ነገረ ምጽአትንከመላእክትም ተረድተው ወደ ማደሪያቸውተመልሰው የተሰጣቸውን ተስፋ ይጠባበቁጀመር፡፡ የተሰጣቸው ተስፋ ‹‹ እነሆ አባቴየሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለው እናንተግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስበኢየሩሳሌም ቆዩ ›› ሉቃ 24፡49 የሚል ነበር፡፡

     ተስፋውም መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸውጊዜ ሰማያዊ ሃብትን እውቀትን ገንዘብታደርጋላችሁ በአራቱ ማዕዘንትመሰክሩልኛላችሁ የሚል ነው፡፡(የሐዋ.1፤8-12)

    ***ለምን በኢየሩሳሌም ጸንታችሁ ቆዩአላቸው ? ***ሉቃ 24፤49

    1.    ከሃይማኖት ከምግባር እንዳይወጡ፤

     መንፈስ ቅዱስ ከመቀበላቸው በፊትፈሪዎች የሚረሱ ነበሩና ፍርሃታቸው እስከመካድ እንዳያድርሳቸው ፡፡

    በኢየሩሳሌም ቆዩ ባይላቸው ኖሮ ሲገቡሲወጡ አይሁድ ያገኟቸውና መከራቢያጸኑባቸው ሃይማኖት መካድ ከምግባርመውጣት ይመጣልና ፡፡

    2.    ለመነኮሳት ለገዳማውያን (ለባህታውያን ) በገዳማቸው ጸንተው መኖርእንዳለባቸው ሲያስተምር ነው ፡፡ 

     ለጊዜው ለ120 ቤተሰብ ሲሆን ፍጻሜውለመነኮሳት ነው።  ኢየሩሳሌም የገዳምምሳሌ ናት፤  ርግብ የታቀፈችውን እንቁላልትታ በሔደች……. ዙረት ባበዛች ጊዜእንቁላሉ እንዳይፈለፈል እንደምታደርግ ሁሉባዕቱን ትቶ የሚሔድ መነኩሴ ፍሬአያፈራምና፡፡

    3.    በሃይማኖት መጽናት እንደሚገባለማጠየቅ ነው ፡፡

     ምሥጢረ ሥላሴ ምሥጢረ ሥጋዌምሥጢረ ጥምቀት ምሥጢረ ቁርባንምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ሁሉበኢየሩሳሌም ስለተገለጸ ኢየሩሳሌምበሃይማኖት ትመሰላለች።

     በኢየሩሳሌም በሃይማኖት ብትጸኑሐዋርያት ያገኙትን ክብር ታገኛላችሁ ሲልነው  አንድም ኢየሩሳሌም በቤተክርስቲያንትመሰላለች ሰባቱ ምሥጢራተቤተክርስቲያን ይፈጸምባታልናበቤተክርስቲያን ብትጸኑ ሐዋርያት ያገኙትንክብር ታገኛላችሁ ሲል ነው ፡፡

    4.    መንፈስ ቅዱስ ዝርው በሆነ ልቦናእንደማያድር ለማጠየቅ………. ልቡናውበሃይማኖት በትህትና በፍቅር በጸና ላይእንደሚያድር ለማጠየቅ

    ተናግሮ የማያስቀር ምሎ የማይከዳ ልዑልአምላክ ነውና በገባላቸው ቃል መሠረትሞትን ድል አድርጎ በተነሳ በ50ኛው ቀንባረገ በ10ኛው ቀን ለሐዋርያት ፀጋ መንፈስቅዱስ በእሳት አምሳል ሰደደላቸው ፡፡ 

    ከላይ እንደተጠቀሰው መቶ ሃያው ቤተሰብየሚባሉት

     12ቱሐዋርያት

     72ቱአርድእት

     36ቱቅዱሳት አንስት በማርቆስ እናት ቤትበጸሎት ላይ ሳሉ ጌታ ከሙታን ከተነሳበሃምሳኛው ባረገ በአስረኛው ቀን

    ተስፋው ተፈጸመ፡፡ ሐዋ.2፡1 ድንገት ከወደሰማይ እንደ ዐውሎ ነፋስ ድምጽ ያለነጎድጓድ ተሰማ ያሉበትን ቤት መላው፡፡

    ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ሆኖ ታያቸው፡፡በሁሉም አደረባቸው ኃይል የሚሆናቸውንሀብት እውቀት ገንዘብ አደረጉ፡፡ የማያልቅሃብቱን ጸጋውን ለመቶ ሃያው ቤተሰብአደላቸው ከዚህም በኋላ ‹‹ 5500 ዘመንሲፈጸም በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉየባህርይ ሕይወቴን መንፈስ ቅዱስንአሳድርበታለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ / 12ቱ ሐዋርያትና 36ቱቅዱሳት አንስት/ ራዕይያያሉ ጎበዛዞቻችሁም / 72ቱ አርድእት /ራዕይ ያያሉ›› ተብሎ በነቢዩ ኢዮኤልየተነገረው ቃል ተፈጸመ (ትን. ኢዮ 2፤28-32)

    ***እመቤታችን ለምን ተገኘች?***
        
    በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድላቸውእመቤታችን ከሐዋርያት መካከል ነበረች ፡፡

    በዛ የተገኘችው እንደ ሐዋርያትከፍርሃታቸው እንዳላቀቃቸው ፣ ምሥጢርንእንደገለጸላቸው በዓለም ሁሉ ቋንቋእንዲናገሩ እንዳደረጋቸው ለእመቤታችንምአስፈልጓት አይደለም ፡፡

    የሃይማኖት ምልክት ማረጋገጫ እሷየሌለችበት ምንም ነገር ስለሌለናስለማይጥም እንጂ እርሷማ የመንፈስቅዱስ ቤቱ ማደሪያው ነች እንጂ አዲስእንዲያድርባት አይደለም፡፡

    እመቤታችን ከሴት ሐረግ ስለምትገኝ ስለእመቤታችን የአቤል ምትክ ሴት ተወለደ ፣እንዲሁም ኖኅ ከእነ ቤተሰቡ ያልጠፋውበዘራቸው እመቤታችን ስላለች ነው፣በአስቴር ጸሎት እሥራኤላውያን የዳኑትእመቤታችን ስለምትገኝ ነው ፡፡ እመቤታችንበቃና ዘገሊላ ፣በእግረ መስቀሉ ፣የሌለችበት ቦታ ስለሌለ በዚህም ታላቅ ቀንከሐዋርያት መካከል ተገኝታለች ፡፡  

    በዓላቸው ‹‹በዓለ ሰዊትን›› ለማክበርበኢየሩሳሌም የተሰበሰቡ አይሁድና ወደአይሁድነት የተመለሱ የተለያዩ ሀገር ሰዎችድምጽን በሰሙ ጊዜ የሆነውን ለማለየትለማወቅ ሐዋርያት ወዳሉበት ተሰበሰቡ፡፡

     የጌታችን ደቀመዛሙርት በተሰጣቸውየመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮችሆኑ፤ ፍጹም እውቀት ተሰጣቸውከኃጢአትና ከእርጅና ታደሱ፡፡ በ72ቱቋንቋለየሀገሩ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ቸርነትአስተማሩ፡፡ ሐዋ.2፤7-12 ‹‹ ጉሽ የወይን ጠጅጠጥተው ሰክረው ነው ›› እያሉበሚያላግጡባቸው አይሁድ ፊት እነ ቅዱስጴጥሮስ ቆመው በማስተማር ሦስት ሺህሰዎችን አሳምነው አጠመቁ፡፡

    ዘመነ ጰራቅሊጦስ በተለይም በ50ኛው ቀንቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ የቤተክርስቲያንየልደት ቀን ›› ሲል ጠርቶታል፡፡ በጌታችንበመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደምየተመሰረተችው ቅድስት ቤተክርስቲያንበመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ተመልታ ለሰው ልጆችሁሉ የድህነት ጥሪን ማሰማት የጀመረችበትዕለት ስለሆነ ይህ ስም ተሰጥቷታል፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ባደረገውስብከት የሕዝቡ ልብ በቃለ እግዚአብሔርተሞልቶ ሦስት ሺየሚያህሉ በአንድ ቀንሰዎች ክርስትናን ተቀብለው በማመንተጠምቀዋል ሥራ 2፡37 -42

    ይህም የሆነው ግንቦት 18 እለት ነው ይህቀን ጥንተ ጰራቅሊጦስ ሲሆን በቅዱስዴሜጥሮስ ቀመር መሠረት ትንሣኤ ከዋለበኋላ በሃምሳኛው ቀን ወይም ዕርገት በዋለበ10ኛው ቀን እንዲውል ተወስኗል ፡፡ሐዋርያት መልካሙን የምሥራች ተስፋ መድረሱን  ቃል  ሥጋ  መዋሐዱን  መከራ ተቀብሎ የሞትን ሥልጣን ሽሮ ከሙታንተለይቶ በሥልጣኑ መነሳቱ በፍቅርናበድፍረት ይመሰክሩ ዘንድ ይህ ጸጋተሰጣቸው፡፡

    ***በዐረገ በ10ኛው ቀን ስለምን ፀጋመንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት ሰደደላቸው ***

    1.   ከ10ኛው ማዕርግ የገባን ነበርንና ወደቀድሞ ክብራችን እንደተመለስን ለማጠየቅ
    2.  10ቱን ትእዛዛት ብንጠብቅ ብንፈጽ ምጸጋ መንፈስ ቅዱስ እንደሚበዛልንለማጠየቅ
    3.  10 ቁጥር የምሉእነት የፍጹምነት ምሳሌ እንደሆነ ሁሉ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ እንዳደረባቸው ለማጠየቅ  ::   ዘፍ 31፡7 ፣ት.ዳን 1፡12

    ዛሬም ቢሆን ይህ ጸጋ እግዚአብሔርን እንደእግዚአብሔርነቱ በንጽህና በቅድስናለሚያመልኩት ይሰጣል፡፡ ኤፌ 4፡30

     ይህ ማለት ለሁሉም የተለያዩ ቋንቋዎችየመናገር ሃብት ይሰጣል ማለት አይደለም፡፡ሃብቱ ብዙ የሆነ መንፈስ ቅዱስ በሥላሴአንድነትና ሦስትነት አምነን የኢየሱስክርስቶስ የባህርይ አምላክነት ተገንዝበንየእመቤታችንን ዘለዓለማዊ ድንግልና፣የቅዱሳንን ክብር ተረድተን ስንጠመቅእንደፈቃዱ ለአንዱ ማስተማርን ለሌላው መዘመርን ለተቀረው እንደወደደ ይሰጣል፡፡1ኛ ቆሮ 12፡4 ይህም እያንዳንዱ ምዕመን በተሰጠው ጸጋ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግል ይረዳዋል፡፡ በጽርሐ ጽዮንበሐዋርያት ላይ የወረደው መንፈስ ቅዱስ ጸጋውን ሰላሙን ያድለን፡፡

    አሜን፡፡
    ወስብሐት ለእግዚአብሔር

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ጰራቅሊጦስ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top