• በቅርብ የተጻፉ

    Monday 9 November 2015

    ምሥጢረ ጥምቀት


    ምሥጢረ ጥምቀትጥምቀት ማለት ከውሃ ውስጥ መጥለቅ መነከር መጠመቅ ማለት ነው። ጥምቀት አጠመቀ ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን በገቢር መንከር መድፈቅ፣ አካልን ውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው ። ጥምቀት ሌሎችን ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመሳተፍ የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው። 

    እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር ሲሰራ ትንቢት ያስነግራል ወይም ምሳሌ ያስቀድማል። በብሉይ ኪዳንም ለሀዲስ ኪዳን የተመሰሉ ምሳሌዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ስለጥምቀት የተመሰሉ ምሳሌዎች 

    ኖህ ከጥፋት ወሃ ይድን ዘንድ መርከብ ሰራ ስለዚህ እርሱም ቤተሰቦቹም ወደ መርከቡ ገብተው የሰው ዘር ሁሉ ሲጠፋ ስምንት ሰዎች ብቻ ዳኑ። ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው። ኖህና ቤተሰቦቹ የምእመናን ፣ ባህሩ የጥምቀት ፣ መርከቡ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናቸው። ከመርከብ ወጭ የዳነ ሰው እንደሌለ በጥምቀት በር ያልገባ እና በቤተክርስቲያን ወስጥ ያልተገኘ አሁንም ድኅነት የለውም ሊኖረው አይችልም። ዘፍ 6፣1422 1ኛ ጴጥ 3፣20-21 ።ግዝረተ አብርሃም የጥምቀት ምሳሌ ነው (ሮሜ 6፣18 ኤፌ 4፣18 ቆላ 2፣19-21 ቆላ 2፣9-12 ።እስራኤላውያን ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው ዘፍ 14፣14 -22 1ኛቆሮ 10፣1-2።ኢዮብ በዮርዳኖስ ወንዝ መታጠቡንዕማን የተባለው የሶሪያ ንጉሥ በዮርዳኖስ ወንዝ ታጥቦ ከለምጽ በሽታ መዳኑ 2ኛ ነገ 5፣1-16።የጥምቀት አስፈላጊነት 
    ድህነት የሚገኘው በጥምቀት ነው በእምነት ብቻ አይደለም ማር፣10፣16 ሐዋ 2፣37 ሐዋ 8 ፣37።በጥምቀት ዳግም ልደት ይገኛል(ዮሐ3፣5-8 ዮሐ 3.3)ሥርየተ ኃጢአት ይገኛል ( ሐዋ 9፣15-16)የክርስቶስ የሞቱና የትንሳኤው ተባባሪ መሆን ነው (ሮሚእ 6፣3-8)አዲስ ህይወት ይገኛል (ሮሜ 6፣4)የቤተክርስትያን አባል ለመሆን

    የጥምቀት ስርዓት በ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ

    በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወንድ በተወለደ በአርባ ቀኑ ሴት በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የጥምቀት ስርአት ይፈጸምላቸዋል የህጽኑ ጤንነት የሚያሰጋ ከሆነ ከዚህ ቀን በፊት ሊፈጸም ይችላል። በችግርና በሌላ ምክንያት ከተጠቀሰው ቀን ቢዘገይ ቤ/ክ የመጡትን ወደኃላ አትመልስም ታጠምቃለች።በ 40 እና በ80 ቀን የሆነበት ምክንያት አዳም በተፈጠረ በ40 ቀን ሔዋን በተፈጠረች በ80 ቀን ገነት እንዲገቡ ስለተፈቀደላቸው ነው (ኩፋ 4፣9)። እንዲሁም በኦሪት ይደረግ የነበረው ሥርዓት ለሃዲስ ምሳሌ በመሆኑ(ዘሌ12፣12 1-8. ሉቃ 2፣22)። ልጆችም እንደየጾታቸው በ 40 እና በ 80 ቀን የጸጋ ልጅነት ያገኛሉና ነው።(ዘሌ 12፣1-8)። 
    ወላጆች ተጠማቂውን ህጻን ይዘው ወደ ቢተክርስቲያን ይመጣሉ። ቄሱ ውሃውን በብረት(በርሜል) አድርጎ ስርአተ ጸሎቱን ይጀምራል፣ መጸሀፈ ክርስትና ይደግማል። በጸሎቱ መግቢያ ላይ የክርስትና እናት ወይም አባት ለመሆን የመጡ የህጻኑን አውራ ጣት ይዘው ተጠማቂውን ሊለው የሚገባውን ሶስት ጊዚ “እክህደከ ሰይጣን” እያሉ ያወግዛሉ ትርጉሙም ሰይጣንን ክጄዋለሁ ማለት ነው። ስርዓተ ጸሎቱ ተገባዶ ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ ዛቲ ..” የሚለውን ጸሎት በዜማ ካዜመ በኋላ ጸሎተ ሃይማኖት ይደገማል። የሃይማኖት ጸሎትን ተጠማቂው፣ ተጠማቂው ህፃን ከሆነ የክርስትና አባት ወይም እናት የህጻኑን አውራ ጣት በመያዝ ሰለ ህጻኑ ፈንታ ይደግማሉ።
    ተጠማቂው በቅዱሳን ስም ለቤተክርስትያን ከተሰጠ በእለቱ የሚያገለግለው ዲያቆን ጸሎተ ሃይማኖትን እየደገመ የህጻኑን አውራ ጣት ይይዛል።ይህ ሲፈጸም ይተጠማቂው ልብስ ይወልቃል በምዕራብ ፣ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅ እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ እያለ ዲያቆኑ ተጠማቂውን በአራት አቅጣጫ እያሰገደ ያዞራል። በዚህ የስግደት ኡደት ጊዜ ካህኑም የተጠማቂውን ግንባር በመስቀል እያሻሸ “ስምከ ይኩን እገሌ” እያለ ስም በመሰየም ይባርከዋል።

    ይህም ሲፈጸም ውሃውን ብሩክ ብሎ ባርኮ “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ውልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ካለ በኋላ “አጠምቀከ በአብ አጠምቀከ በወልድ አጠምከከ በመንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያረገ ካህኑ ያጠምቃል። የክርስትና ስም አወጣጥም በ/ኢ/ኦ/ቤ/ክ ካህን የሚሰየመውን የእለት በአልን ምክንያት በማድረግ ነው። ለምሳሌ የጌታችን ፣የመቤታችን፣ እለት ከሆነ ገብረ መድኅን ኃ/ማርያም…የቅዱሳን መላእክት የፃድቃን ሰማእታት ከሆነ ወ/ሚካኤል ኃ/ጊዮርጊስ ወ.ዘ.ተ በሚል ስያሜ ይሰጠዋል።
    ስያሜው ጥምቀት ሲያበቃ ካህኑ (ዲያቆኑ) ለክርስትና እናቱ(አባቱ) ያስረክባሉ። ከልጅህ (ከልጅሽ) የማትለየውና በክርስትያናዊ ምግባርና በሐይማኖት የምታሳድገው የቃል ኪዳን ልጅህ (ልጅሽ) ነው እያለ ካህኑ ይመክረዋል። እርሱም እሺ እያለ ይቀበላል በዚህ ጊዜ 36 ቦታዎች ሜሮን ይቀባል ይህብረት ቀለማት ያለው ፈትል ተገምዶ በአንገቱ ላይ ይታሰራል ይህ በግእዝ ማዕተብ በአማርኛ ቡራኬ(ስጦታ) ይባላል። ቀለሙ ሶስት ዓይነት ነው። ነጭ ቀይ፣ ቢጫ፣ (ነጭ የአብ ቀይ የወልድ ቢጫ የመንፈስ ቅዱስ ሶስት የመሆኑ ምስጢር ስላሴ አንድ ሆኖ መገመዱ የአንድ አምላክ መሳሌ ነው። ህፃኑ ልብሱን ከመልበሱ በፊት ቄሱ ህፃኑን በሁለት እጃቸው ከፍ አርገው ይይዙታል “ንሳ መንፈስ ቅዱስ” እየተባለ እፍ ይባልበታል። ከዚህ በኋላ ተጠማቂው ሜሮን ተቀብቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ይቆርባል የጥምቀቱ ስርዐት የሚፈጸውመው ተጠማቂው ሲቆርብ ብቻ ነው። አለበለዚያ ጥምቀቱ ሙሉ አይሆንም ምክንያቱም የጥምቀቱ ማህተብ ስጋወ ደሙ ነው። 

    Calgary Hamere Nohe Saint Kidanemhret Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC)Canada

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ምሥጢረ ጥምቀት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top