• በቅርብ የተጻፉ

    Wednesday, 4 November 2015

    መምህር ግርማ ማነው? ሥልጣነ ክህነትስ አለውን?

    በቀድሞው ዳኛ ዘውዱ ታደሰ

    "መምህር ግርማ እውነት አጥማቂ ነውን ?

    እኔ መምህር የሚባለውን ሰው አቶ ነው የምለው ፤ ግርማን የማውቀው የቀድሞ ጦር ሰራዊት መቶ አለቃ ሆኖ በጡረተኝነት በመቂ ከተማ ነዋሪ እያለ ር ትዳርም የነበረውና 2 ልጆች እንዳሉትም አውቃለው። አቶ ግርማን የት እና እንዴትአወኩት? እኔ የምስራቅ ሸዋ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኜ በ1996 መቂ እኖር ነበር ፤ ከዛም ጋር ተያይዞ በቤተክርስቲያና ቅርብ ስለነበርኩ፤ ከምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አብነ ጎርጎሪዬስ ጋር የቀረበ ግንኘነት ስለ ነበረኝ ፡፡

    የዝዋይን  ሐመረ ኖህ መንፈሳዊ ኮሎጅ ሰበካ ጉባኤ ሆኜ ለ3 አመት መርቻለው በዚህ ጊዜ አቶ ግርማ የዘበኝነት (የጥበቃ ስራ ) ማስታወቂያ ስናወጣ ወታደር ስለሆነ ተፈትኖ አልፎ በእኔ ፊርማና ማህተም ቀጥሬዋለው፡፡ ይህ ግለሰብ እንደማንኛውም ተራ አማኝ ነው፡፡ እኔ ሳውቀው የክህነት ትምህርት ፈፅሞ የለውም፡፡ በጥበቃ ከሰራ በኋላ ቋሚ አድርጉኝ ደሞዝም ጨምሩልኝ ብሎ በደብዳቤ ወረቀት ለኔ ቢሮም በአካልም አናግሮኝ ታገስ አባታችን ይምጡና እንነግራቸዋለን ብዬው የተከበሩ ብፁዕ አባታችንም አባ ጎርጎሪዬስ ‹‹የልጆች አባት ነው ቋሚ አድርጉት ደሞዝ ግን አሁን አይጨመርልህም›› ብለው መልስ ሰጡ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ግርማ ስራውን ተወው ፡፡ ስራውን በመተው ሱዳን እንደሄደ ለስራ ከባለቤቱ አፍ ሰምቻለው ከ3 አመት በኋላ ወደ ኢትዮጰያ በመምጣት አባ ግርማ.መባሉን ሰማው ፡፡

    በጠቃላይ ይህ ሰው በሱዳን እፅ ወይም መተት እንደሚሰራ ግልፅ እና የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ስለሚታወቅ በምስራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አንድም ቦታ ላይ ሰርቶም አያውቅም፡፡ አሁን በመላው ኢትዮጵያ እንደተከለከለ አውቃለው፡፡ ይህ ሰው የሚሰራው ስራ ተራ የማታለል እና የውንብድና ስራ ነው ። አሁን አዲስ አበባ ሌላ ወጣት ሚስትም አግብቶ እንደሚኖር አውቃለው ፤ የመጀመርያ ሚስቱ በአሁን ሰአት ተለያይተው ሰው ቤት እንጀራ በመጋገር ነው የምትተዳደረው ፤ ይህንን ማወቅ የፈለገ በአካልም በስልክም ላገናኘው እችላለው ከአስመሳዮች እንጠቀቀ፡፡ መምህር ግርማ አታላይ ነው።"

    ትክክለኛ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣነ ክህነት እንደለሌለውም በተደጋጋሚ ከቤተ ክርስቲያን መወገዙ አንድ ማስረጃ ነው::

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: መምህር ግርማ ማነው? ሥልጣነ ክህነትስ አለውን? Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top