አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ ትውልዱም ከነገደ ሴም ነው አባቱ ታራ ይባላል የአዳም ሃያ አንደኛ ትውልድ ነው፡፡ ቤቱን ከተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ሰው በእንግድነት ሲቀበል ይኖር ነበር ፡፡ ሰይጣን ከዕለታት አንድ ቀን እራሱን በአብርሃም የተደበደበ አስመስሎ ከመንገድ ላይ በሰው አምሳል ቁጭ ብሎ እንግዶችን ወዴት ትሄዳላችሁ እያለ ይጠይቃቸው ጀመ ርቦን እንዲያበላን ጠምቶን እንዲያጠጣን ከአብርሃም ዘንድ ይሉታል፡፡ የድሮው አብርሃም መሰላችሁ እንዴ! እኔም እንደናንተ ርቦኝ ያበላኛል ጠምቶኛል ያጠጣኛል ብዬ ብሄድ እራሴን ደብድቦኝ አባረረኝ እያለ ሰዎችን ሁሉ ወደ አብርሃምም ያለ እንግዳ አህል አልበላም ውሃም አልጠጣም ብሎ ሰሦስት ቀን ቆየ በሦስተኛው ቀን በቀትር በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ አግዚያብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍተገለጡለት አይኑንም አነሣና አነሆ ሦስት ሰዎችን በፊቱ ቆመው አየ፡፡ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነስቶ ሮጦ ወደ ምድርም ሰገደ እንዲህም አለ ገሀሱ አጋዕዝትየ ቤተ ገብርክሙ ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ እረፊ አላቸው ደክሞናልና እዘለን አሉት አንዱን አዝሎ ሊገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ ገብተው ተገኝተዋል አብርሃምም ሦስት እንደሆኑ አውቆ ሣራን ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ወስደሽ አንድ እንጎቻ አድርገሽ ጋግሪው አላት ሣራም ጋግራ አቀረበች አብርሃምም ሥላሴን በእንግድነት ተቀበለ፡፡
ትምህርት
· አንግዶችንበቤታችን ለመቀበል ዘወትር መዘጋጀት
· አንዳንዶችሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋል (ዕብ 13÷1)
· አንግዶችንመቀበል ክእግዚያብሔር ዋጋ እንዳለው ማወቅ(ሮሜ 4÷37)
· አብርሃምአንግዳ ለመቀበል በረከትን አግኝቷአል መካን የነበረችው ሚስቱ ሣራም ልጅ ወለደች (ዘፍ 21÷1)
መልእክት
አባታችን አብርሃም ደግ አንግዶች ወደ ቤቱ ካልመጡ እህል የማይበላና ወኃ የማይጠጣ ሰው ስለነበረ አግዚአብሔር ባርኮታል ዘሩንም እንደምድር አሸዋ አብዝቶለታል፡፡ እኛም አንግዶችን በመቀበል ያለንን በማካፈል ወደ ኋላ እንዳንል ያጣነውን ፤የምናገኘው ተስፋ የቆረጠን ተስፋችን የሚቀጥለው አይሳካልንም ያልነው የሚሳካው፤ የተዘጋብን የሚከፈትልን በእምነት ስንኖርና እና እንደ አብርሃም እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ የምንጠብቀውን ተስፋ በዓይናችን የምናየው በእምነት እየኖር የእግዚብሔርን እንግዳ ስንቀበል ነው፡፡
የእግዚአብሔርን በረከትም እንዳያልፈን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን አሜን!!
0 comments:
Post a Comment