• በቅርብ የተጻፉ

    Friday 6 November 2015

    የዘመን አቆጣጠር (ባሕረ ሐሳብ) _ ክፍል አንድ

    ባሕረ ሐሳብ፡ ማለት ቁጥር ያለው ዘመንማለት ነው። ይኸውም በግዕዙ “ሐሰበ-ቆጠረ፤” ከሚለው ግስ የወጣ ዘመድ ዘር ነው። ባሕረ ሐሳብየሚያስተምረን በዓላትን እና አጽዋማትን (የጾምወቅቶችን) ለማውጣት፡- የመደመርን፥ የመቀነስንእና የማባዛትን ስሌት ብቻ ሳይሆን፥ ሐሳበ ፀሐይን፣ ሐሳበ ወርኅን፣ ሐሳበ ከዋክብትን፣ ሐሳበ አበቅቴን፣ ወዘተ… ጭምር ነው። ይህን ሁሉ አጠቃሎ የያዘእንደ ባሕርም የሰፋ በመሆኑ የሐሳብ (የቁጥር)ባሕር ተብሏል። የዘመን አቆጣጠር፡- ፩ኛ፡-ለማኅበራዊ ኑሮ ጥቅም፤ ፪ኛ፡- የሃይማኖትተግባሮችን ለማከናወን እንዲያገለግልተፈጥሮአዊውን የወቅቶች ክፍፍል እርስ በርሳቸውየማመቻቸት ጥበብ ነው። እንደ ባሕር አዝዋሪትምመንገዱ፥ ጥልቀቱና ስፋቱ፥ ረዥምና ሰፊ በመሆኑባሕረ ሐሳብ የሚለው ስያሜ ይስማማዋል።                                 

            በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር (የጊዜ ቀመር)አንድ ዓመት በአራት ወቅቶች የተከፈለ ዐሥራ ሦስትወራት አሉት። ፩ኛ፡- ከሰኔ ፳፮ - መስከረም ፳፭ክረምት ነው፥ ትርጉሙም የውኃ ዘመን ማለት ነው። ቅዱስ ያሬድ በድጓው፡- “ያርሁ ክረምተ በበዓመት፥ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት፤ በየዓመቱ ክረምትንያገባል፣ ደመናት ቃሉን ይሰሙታል፤” በማለት ይህንወቅት የሰጠን እግዚአብሔር መሆኑን ነግሮናል። ፪ኛ፡- ከመስከረም ፳፮ - ታኅሣሥ ፳፭ መፀው(መከር) ነው፤ በግዕዙ፡- “መፀወ - አበበ፣ አበባ ያዘ፣ አረገዘ፤” ማለት ስለሆነ፥ የአበባ ወር፥ የአበባ ወቅትነው። ቅዱስ ያሬድም መፀውን ከክረምት ጋርአጣምሮ፡- “ግሩም በሆነው ኃይልህ እንመካ ዘንድአንተ ዘመናትን ሠራህ፥ ክረምትን ለዝናማትመፀውን ለአበቦች ሰጠህ፤” ብሏል። ኩፋሌ፥፪፤ ኢዮብ፥፪፥፳፫፣ ኤር፥፭፥፳፬። ፫ኛ፡- ከታኅሣሥ ፳፮ -መጋቢት ፳፭ በጋ (ሐጋይ) ነው፤ የፀሐይ ሙቀትየሚበረታበት ስለ ሆነ ድርቅ የድርቅ ወራት ማለትነው። መዝ፥ ፸፭፥፲፯፣ ዘካ፥፲፬፥፲፣ ዘፍ፥ ፰፥፳፪። በመጽሐፈ ሲራክም ላይ፡- “በየጊዜያቸውናበየቁጥራቸው አዝመራንና ክረምትን በጋንለየ፤”የሚል አለ። ሲራ፥ ፴፮፥፱። ፬ኛ፡- ከመጋቢት ፳፮- ሰኔ ፳፭ ጸደይ (በልግ) ነው። በልግ ሆነ፥ ለመለመ ማለትነው። በልግ አብቃይ በሆነው የሀገራችንክፍል የበልግ አዝመራ የሚዘራበት፥ በልግ አብቃይባልሆነው ክፍል  ደግሞመሬቱ ለክረምት የዘርወቅት የሚዘጋጅበት ጊዜ ነው። ሦስቱ ወቅቶችእያንዳንዳቸው ዘጠና ዘጠና ቀናት ሲኖራቸውክረምት ግን ጳጉሜን ጨምሮ ዘጠና አምስት ቀናትንይዟል።                                              

                        የአሥራ ሦስቱ ወራት ስያሜናትርጉም፤                                                        

           ሁሉም የኢትዮጵያ ወራት ራሱን የቻለ ትርጉምአላቸው፥መነሻቸውም መድረሻቸውም ነገረእግዚአብሔር ነው፥እንደ ፈረንጆቹ ከጣዖት ጋርየተያያዘ አይደለም። ፩ኛ፡-መስከረም፡-“መስየ +ክረምት” የሁለት ቃላት ጽምረት ነው፤ ትርጉሙም፡-“ምሴተ ክረምት(የክረምት ምሽት፣የክረምት ማለቂያ)” ማለት ነው። በመስከረም ወርውስጥ የሚገኙት ዕለታት እያንዳንዳቸው፥የመዓልታቸው ርዝመት ፲፪ ሰዓት ሲሆን፥ የሌሊታቸው ርዝመት እኵል ፲፪ ሰዓት  ነው።፪ኛ፡-ጥቅምት፡- “ጠቀመ - ገነባ፤” ከሚለው ግስ የወጣ ነው። ገበሬው አዝመራውን በቡቃያነቱ ቀን ቀንከብቶች እንዳይሰማሩበት፥ ሌሊት ሌሊት ደግሞአራዊት እንዳይፈነጩበት ዙርያውን የሚያጥርበትናየሚገነባበት አንድም የታጠረውን ወይምየተገነባውን የሚያጠባብቅበት ወቅትነው።በጥቅምት ወር ውስጥ የሚገኙት ዕለታትእያንዳንዳቸው፥ የመዓልታቸው ርዝመት ፲ ሰዓት ከ፵ደቂቃ ሲሆን፥ የሌሊታቸው ርዝመት ፲፫ ሰዓት ከ፳ደቂቃ ነው። ፫ኛ፡- ኅዳር፡- “ኀደረ - አደረ፤” ከሚለውግስ የወጣ ነው። ይኸውም ገበሬው እግዚእብሔርለፍሬ ያበቃለትን አዝመራ፥ ቤቱን ትቶ፣ ከዱር አድሮየሚጠብቅበት ወቅት ስለሆነ ነው። በኅዳር ወርውስጥ የሚገኙት ዕለታት እያንዳንዳቸውየመዓልታቸው ርዝመት ፱ ሰዓት ከ፳ ደቂቃ ሲሆን፥ የሌሊታቸው ርዝመት ፲፬ ሰዓት ከ፵ ደቂቃ ነው።፬ኛ፡-  ታኅሣሥ፡-“ኀሠሠ - ፈለገ፤”  ከሚለው ግስየወጣ ነው። አዝመ ራው ተሰብስቦ ወደ ጎተራየሚገባበትና የሰው ፍላጐት የሚሟላበት ወር ነው። የሰውን ፍላጐት የሚያሟላው ደግሞ እግዚአብሔርነው። በታኅሣሥ ወር ውስጥ የሚገኙት ዕለታትእያንዳንዳቸው፥ የመዓልታ ቸው ርዝመት ፰ ሰዓትሲሆን፥ የሌሊታቸው ፲፮ ሰዓት ነው። ፭ኛ፡- ጥር፡- “ጠየረ - በረረ፣ ከነፈ፤” ከሚለው ግስ የወጣ ነው። ምሥጢ ሩም ምጥቀት፣ ርዝመት ማለት ነው። ይህም ከጥቅመ ሰናዖር (ከባቢሎን ግንብ) ጋርየተያያዘ ነው፤ ፭ሺ፬፻፴፫ ክንድ ከሁለት ስንዝርየሆነው የባቢሎን ግንብ ለአርባ ዓመታት ሲሠራቆይቶ ጥር ሰባት ቀን ሥላሴ አፍርሰውታል። ኩፋሌ፡፲፥፲፩፣ዘፍ፡፲፩፥፩። በጥር ውስጥ የሚገኙት ዕለታትእያንዳንዳቸው፥ የመዓልታ ቸው ርዝመት ፱ ሰዓትከ፳ ደቂቃ ሲሆን፥ የሌሊታቸው ርዝመት ፲፬ ሰዓትከ፵ ደቂቃ ነው። ፮ኛ፡-የካቲት፡-“ከተተ-ሰበሰበ፤”ከሚለው ግስ የወጣ ነው።“ ከቲት ብሎ መከትከት፣ ማድቀቅ፣ መውቃት፣ ማምረት፣ መሰብሰብ፤”ይላል። የመከር ጫፍ፥መካተቻ፥ የበልግ መባቻማለት ነው። በየ ካቲት ወር ውስጥ የሚገኙ ዕለታትእያንዳንዳቸው፥ የመዓልታቸውርዝመት ፲ ሰዓት ከ፵ደቂቃ ሲሆን፥የሌሊታቸው ርዝመት ፲፫ ሰዓት ከ፳ደቂቃ ነው። ፯ኛ፡-መጋቢት፡-“መገበ - መገበ፤”ከሚለው ግስ የወጣ ነው።በዚህ ወር የመዓልቱናየሌሊቱ ምግብና እንደ መስከረም እኵልይሆናል።በዚህን ጊዜ መዓልቱ ፲፪ ሰዓት ሌሊቱም፲፪ ሰዓት ነው። በሌሎቹ ግን ከላይ እንዳየነው ፥ ቀጥለንም እንደምናየው፥ መዓልቱ ወይም ሌሊቱይረዝማል፤ ለምሳሌ፡- በሀገራችን በገና ሰሞን  ቀኑቶሎ ይመሻል፥ ምክንያቱም መዓልቱ አጥሮ ሌሊቱስለሚረዝም ነው። ፰ኛ፡-ሚያዝያ፡-“መሐዘ-ጎለመሰ፥ ጎበዘ፥ አደገ፤” ከሚለው ግስ የወጣ ነው። ልጆችአድገው ለሚዜነት የሚበቁበትን ዕድሜያመለክታል። ሚዜ፡- የሙሽራ ወዳጅ፥ ባለሟል፥ ባልንጀራ፥አብሮ አደግ፥ እኩያ፥ አምሳያ፥ ጓደኛ ማለትነው። አንድም መሐዘ፡- ጎለመሰ፥ ጎበዘ፥ አደገ፥ ሚስት ፈለገ ማለት ነው። በሀገራችን ሚያዝያየሠርግ ወር ነው። በሚያዝያ ወር ውስጥ የሚገኙትዕለታት እያንዳንዳቸው፥ የመዓልታቸውርዝመት ፲፫ሰዓት ከ፳ ደቂቃ ሲሆን፥ የሌሊታቸት ርዝመት ፲ሰዓት ከ፵ ደቂቃ ነው። ፱ኛ፡- ግንቦት ፡-“ገቦ-ጐን፣ አጠገብ፤”ከሚለው ስም የወጣ ነው። ትርጉሙምገቦ ክረምት (የክረምት ጐን፣ የክረምትአጠገብ፣ለክረምት የቀረበ)ማለት ነው። በግንቦትወር ውስጥ የሚገኙት ዕለታት እያንዳንዳቸው፥ የመዓል ታቸው ርዝመት ፲፬ ሰዓት ከ፵ ደቂቃሲሆን፥የሌሊታቸው ርዝመት ፱ ሰዓት ከ፳ ደቂቃነው።፲ኛ፡-ሰኔ፡-“ሰነየ - አማረ፣ ተዋበ፤” ከሚለውግስ የወጣ ነው። ይህም፡-በብዙ ድካም ታርሶናተቆፍሮ የለሰለሰው የእርሻ መሬት ሙሉ በሙሉበዘር ተሸፍኖ ማማሩን እና መዋቡን የሚያመለክትነው። በሰኔ ወር ውስጥ የሚገኙት ዕለታትእያንዳንዳቸው፥ የመዓልታቸውርዝመት ፲፮ ሰዓትሲሆን፥ የሌሊታቸው ርዝመት ፰ሰዓት ነው። ፲፩ኛ፦ሐምሌ፡-“ሐመለ - ለመለመ፤” ከሚለው ግስየወጣ ነው። የሚያመለክተውም በወርኃ ሰኔ ተዘርቶየነበረው ዘር በቅሎ ቅጠል ማውጣቱን ነው። ትርጉሙም የቅጠል ወር ማለት ነው። በሐምሌ ወርውስጥ የሚገኙት ዕለታት እያንዳንዳቸው፥ የመዓልታቸው ርዝመት ፲፬ ሰዓት ከ፵ ደቂቃ ሲሆን፥ የሌሊታቸው ርዝመት ፱ ሰዓት ከ፳ ደቂቃ ነው። ፲፪ኛ፡-ነሐሴ፡-“ነሐሰ - ሠራ፣ገነባ፤”ከሚለው ግስየወጣ ነው። ናሕስ፡-ሲል ደርብ፥ ሰገነት፥ ፎቅ፥ የግንብ ጣራ፥ከበላይ ያለ ማለት ነው።ለልብስሲሆን ደግሞ የልብስ ዘርፍ፣ ጫፍ፣ ክፈፍ ማለትይሆናል። በመሆኑም ነሐሴ፡-ለዓመቱ ወራት ጫፍ፣ዘርፍ፣ክፈፍ ነው።በነሐሴ ወር ውስጥ የሚገኙትዕለታት እያንዳንዳቸው፥ የመዓልታቸው ርዝ መት ፲፫ሰዓት ከ፳ ደቂቃ ሲሆን፥ የሌሊታቸውርዝመት ፲ ሰዓት ከ፵ ደቂቃ ነው። ጳጉሜን ማለትደግሞ ትርፍ ማለት ነው።                                                                                                                     

                      የፈረንጆቹ የወራት ስያሜ የመጣውከየት ነው?                                                       

          የፈረንጆቹ የወራት ስያሜ የመጣው ከጣዖታትናከግለሰቦች ስም ነው። ለአብነት ጥቂቶቹንእንመለከታለን። ፩ኛ፡-january (ጃንዋሪ)-janu's Month(የበርአምላክ)ተብሎ ከሚታ መን ጣኦትየመጣ ነው።፪ኛ፡-February(ፌብሩዋሪ)-Februa's Month ስርየትን ይሰጣል ተብሎይታመንበት ከነበረ ጣዖት የመጣ ስም ነው። ፫ኛ፡-March(ማርች) - Mars Month የጦርነትአምላክ ተብሎ ከሚታመን ጣዖት የመጣ ስም ነው።4ኛ፡-April (አፕሪል) - Aphro dite's Monthየፍትወትና የውበት አምላክ ተብላ ከምትታመንጣዖት የመጣ ስም ነው።፭ኛ፡-june(ጁን)-Juno's Month ጋብቻን የምታሳካና ሴቶችንም ጥሩታደርጋለች ተብላ ትታመን ከነበ ረች ጣዖት ስምየመጣ ነው። ፮ኛ፡-July(ጁላይ) - Juliu's Monthየንጉሡ የጁሊየስ ቄሣር መታሰቢያ ነው። ፯ኛ፡-August(ኦገስት) - August's Month የንጉሡየአውግስጦስ ቄሣር መታ ሰቢያነው።                                                                                                                         

                    የሰባቱ ዕለታት ስያሜዎች፤                                                                                                                              

           የሀገራችን የሰባቱ ዕለታት ስያሜዎች፥ እግዚአብሔር በስድስቱ ዕለታት ሃያ ሁለቱንፍጥረታት ፈጥሮ በሰባተኛዋ ዕለት ከማረፉ ጋርየተያያዘ ነው። ዘፍ፥፩፥፩-፴፩።፩ኛ፡-እሑድ፡-“ አሐደ -አንድ አደረገ፥የመጀመሪያ ሆነ፤”ከሚለው ግስየወጣ ነው። በመሆኑም፡- እግዚአብሔር ፍጥረታትንአንድ ብሎ መፍጠር የጀመረባት ዕለት እሑድተብላለች። ፪ኛ፡-ሠኑይ(ሰኞ)፡- “ሠነየ - ሁለትአደረገ፤” ማለት ነው።ይህም ለፍጥረት ሁለተኛ ቀንማለት ነው። ፫ኛ፡-ሠሉስ (ማክሰኞ)፡- “ሠለሰ - ሦስትአደረገ፤”ከሚለው የወጣ ነው። ለፍጥረት ሦስተኛቀን ማለት ነው።፬ኛ፡-ረቡዕ፡- “ረብዐ - አራትአደረገ፤” ከሚለው የወጣ ነው። ለፍጥረት አራተኛቀን ማለት ነው። ፭ኛ፡- ሐሙስ፡-“ሐመሰ - አምስትአደረገ፤” ከሚለው የወጣ ነው። ለፍጥረት አምስተኛቀን ማለት ነው። ፮ኛ፡-ዓርብ፡- “ዓረበ - ተካተተ፤”ከሚለው የወጣ ነው።እግዚአብሔር ፍጥረታትንበዕለተ እሑድ መፍጠር ጀምሮ ያካተተው ወይምየፈጸመው በዕለተ ዓርብ በመሆኑ “ዓረበ”ከሚለው“ዓርብ”የሚለው ስም ወጥቷል። ፯ኛ፡-ቅዳሜ፡-“ቀደመ - ቀደመ፣ፊትሆነ፣ላቀ፣ጀመረ፤”ከሚለው የወጣ ነው። በአዲስኪዳን “ሰንበተ ክርስቲያን”ተብላ ከተሰየመችውከእሑ ድ አስቀድማ በዘመነ ኦሪት የነበረች “ሰንበተአይሁድ” በመሆኗ ቅዳሜ ተብላለች። ይኸውምቀዳሚት ሰንበት እንደ ማለት ነው።                                                           
                                     ቅዱስድሜጥሮስ፤                                                                                                     

           ቅዱስድሜጥሮስ አባቱ አርማስቆስይባላል፣ልዕልተ ወይን ከምትባል ከአጎቱ ልጅ ጋርበአንድ ቤት አድገዋል። የነበሩበት ዘመን አሕዛብየበዙበት፥ ክርስቲያኖች ግን እጅግ ያነሱበት ዘመንነበር፤ በዚህም ምክንያት ሕንፃ ሃይማኖት ፈርሶከአሕዛብ ወገን ከሚያገባ ይልቅ ሕንፃ ሥጋ  ፈርሶክርስቲያን ዘመዱን ቢያገባ ይሻላል ብለው የአጎቱንልጅ አጭተው ሠርግ አደ ረጉለት።በመሸም ጊዜሥርዓተ መርዓት ወመርዓዊ ያድርሱ ብለውትተዋቸው ሄዱ። ሙሽሪ ትም፡- “ይህን ያደረግኸውየእርሷ ዝምድና አይረባኝም፥ አይጠቅመኝም ብለህነው?” አለችው። እርሱም፡-“የወላጆቼን ፈቃድለመፈጸም ብዬ እንጂ ዝምድናሽን ንቄ አይደለም፥ አሁንስ ፈቃድሽ ከሆነ ለምን አንተወውም?” አላትናለመተው ተስማሙ። ከዚህም አያይዘው፡-“በገሃድየተለያየን እንደሆነ እኔን ለሌላ ያጋቡኛል፥ አንቺንምለሌላ ይድሩሻል፥ ስለዚህ የተጋባን መስለን አብረንእንኑር፤ ባንወልድ እንኳ መክነው ነው ይሉናል እንጂአይጠረጥሩንም፤”አላት። በአንድ አልጋ፥ በአንድምንጣፍ እየተኙ ለአርባ ስምንት ዓመታት በንጽሕናኖሩ። ቅዱስ ሚካኤል፡- ክንፉን አልብሷቸው አድሮጧት ጧት ሲሄድ በነጭ ርግብ አምሳል በግልጥያዩት ነበር።                                                                                                                                                   

           ቅዱስ ድሜጥሮስ ገበሬ ነበርና የወይንአትክልቱን ሲጐበኝ ያለወቅቱ አብቦ ያፈራ ወይንአግኝቶ ለልዕልተ ወይን ሰጣት። እርሷ ግን፡-“ይኸንንእኔ ልመገበው አይገባኝም፥ ይልቅስ በመሶበ ወርቅአድርገህ ለሊቀ ጳጳሱ ውሰድለትና ተመ ረቅ፤” አለችው። ሊቀ ጳጳሱ ዩልያኖስ አርጅቶ ስለነበር ከእርሱ በኋላ በቅዱስ ማርቆስ መንበርየሚተካውን እግዚአብሔር እንዲገ ልጽለት ከሕዝቡጋር ጾም ጸሎት ይዞ ነበር። መልአከ እግዚአብሔርምተገልጦ፡- “ያለወቅቱ ያፈራ የወይን ዘለላየሚያመጣልህ ከአንተ በኋላ የሚተካው እርሱነው፤” አለው። ይህንንም ለሕዝቡ ነገራቸው።በማግስቱም ወንጌል ዘርግቶ ሲያስተምር ቅዱስድሜ ጥሮስ በመድረሱ፡-“ያልኳችሁ ሰው ይህ ነው፤ አይሆንም ስለሚላችሁ ቢሆን በውድ፥ ካልሆነምበግድ ሹሙት፤” አላቸው። ቅዱስ ድሜጥሮስየሆነውን ሁሉ ሳያውቅ እጅ ነስቶ በቆመጊዜ፡-“የእግዚአብሔር ማደሪያ እንዴት ነህ?”አለው። እርሱም፡-“እግዚአብሔር ይመስገን፤” ብሎ ወይኑንአበረከተ፤ ሊቀ ጳጳሱም ድሜጥሮስን ባርኮት ዕለቱኑዐረፈ ።                                                                                   

          ቅዱስ ድሜጥሮስ ከቀብር በኋላ ለመሄድ ሲነሣሕዝቡ “አትሄድም፤”ብሎ ያዘው። “የተማርኩ ሰውአይደለሁም፥ በጋብቻ እንጂ በድንግልናአልኖርኩም፥ ሕጉን ሥርዓቱን አላውቅም፤”ቢላቸውም፡-“የአባታችን ቃል አይታበልም፤”ብለውአልሰሙትም። “እንግዲያውስ እናንተ አስተምሩኝ፤”ቢላቸው፡-“አባታችን አንቀጸ ብፁዓንን እናአንቀጸ አባግዕን (ማቴ፥፭ን እና ዮሐ፥፲ን)ተርጕሞያስተምረን ነበር፤” ብለው ነገሩት። መልሶም፡-“እንኳንስ ትርጓ ሜውንና ምሥጢሩንንባቡን እንኳ አላውቅምና መጽሐፉን አምጡ ልኝ፤”አላቸው። ሊያመጡለት በሄዱበት ቅጽበት የብሉይናየሐዲስ ትርጓሜ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለታል።                                                                                                                                                                                  

          ቅዱስ ድሜጥሮስ ቀድሶ በሚያቆርብበት ጊዜየሕዝቡ ኃጢአት ስለሚገለጥለት፡-“አንተ በቅተሃልቁረብ፥ አንተ ግን አልበ ቃህም ተመለስ፤” ይላቸውነበር። የበቁትን ብርሃን ለብሰው፥ መላእክትከብበዋቸው ያያቸዋል፤ ያልበቁትን ግን ጨለማለብሰው፥ የጨለማ መልእክተኞች ከብበዋቸውያያቸው፥ ንስሐ እንዲገቡም ይመክራቸው ነበር። እነርሱ ግን በጠላትነት ተነሥተ ውበት፡- “እርሱደግሞ ማን ሆኖ ነው የሚከለክለን? አግብቶ ሳለእንደ ድንግል ሊቀ ጳጳስ መሆኑ ሳያንሰው ቁርባንይከለክለናል?” እያሉ ያሙት ጀመር። ዓለም እንዲህነው፥ በመጀመሪያ፡- “ቅዱስ፥ ቅዱስ” እንዳላለ፥ድካሙ ሲነገረው ሰውን የሚከስበት ኃጢአትይፈልጋል። በዚህን ጊዜ መልአክተገልጦለት፡-“ሕዝቡ በሐሜት እየተጐዳ ነውናራስህን ግለጥላቸው፤” አለው። ቅዱስድሜጥሮስም ሕዝቡን ሰብስቦ ደመራ ካስደመረበኋላ በእሳቱ ላይ ቆሞ ጸለየ፤ እርሷንም ጠርቶየእሳቱን ፍም በእጁ እያፈሰ በቀሚሷ ካስያዛት በኋላሕዝቡን ሦስት ጊዜ ዞረች፤ ልብሷም አካሏምአልተቃጠለም። ከዚህ በኋላ በንጽሕና በድንግልናየመኖራቸውን ምሥጢር ነገራቸው። ሕዝቡምከእግሩ ስር ወድቀው፡-“ኃጢአታ ችንንአስተስርይልን፧” አሉት። እርሱም ይቅር ብሎ፥ ናዝዞአስተሰረ የላቸው። በዚህን ጊዜ ኃጢአታቸው እንደሸማ ተጠቅልሎ ከፊታቸው ሲወድቅ አይተውታል ።ከቅዱስ ማርቆስ ጀምሮ ሲቆጠር ፲፪ኛየእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስነው።                                                                              

                                     የቅዱስ ድሜጥሮስምኞት፤                  

           ቅዱስድሜጥሮስ፡- 1ኛ/የነነዌ ጾም፣ የዐቢይጾም እና የሐዋርያት ጾም መግቢያ ከሰኞ፤ 2ኛ/የደብረ ዘይት፣ የሆሣዕና፣ የትንሣኤ እናየጰራቅሊጦስ በዓል ከእሑድ፤ 3ኛ/ርክበ ካህናት እናጾመ ድኅነት ከረቡዕ ባይወጣ እያለ ይመኝ ነበር። መልአኩም መጥቶ፡- “በምኞት ብቻ ይፈጸማልን?ከመዓልቱ ሰባት ሱባዔ፣ ከሌሊቱ ደግሞ ሃያ ሦስትሱባዔ ግባና ይገለጽልሃል፣ ይህንንም በሠላሳበሠላሳ ገድፈህ /አጣፍተህ/ በተረፈው ውጤትታገኘዋለህ ብሎታል። የመዓልቱን ሱባዔ አሳጥሮየሌሊቱን ያስረዘመው ያለ ምክንያት አይደለም። ቅዱሱ፡- በመዓልት የተጣላ ሲያስታርቅ፣ የታመመሲጠይቅ፣የሞተ ሲቀብር፣ ሲፈርድ፣ ሲያስተምር፣ ቤተእግዚአብሔርን ሲያገለግል ስለሚውል ሰዓትያንሰዋል፤ በሌሊት ግን ይህ ሁሉ የለበትምና ለዚህነው። አንድ ሱባዔ ሰባት  ነው፣ በዚህ መሠረት የቀኑሰባት ሱባዔ በሰባት ሲባዛ አርባ ዘጠኝ ይሆናል ፣ ይህንንም በሠላሳ ስንገድፈው ወይም ስናጣፋውአሥራ ዘጠኝ ይቀራል። ይኸንን “መጥቅዕ” በለውብሎታል። “መጥቅዕ” ደወል ማለት ነው፣ ደወልሲደወል የሩቁም የቅርቡም እንደሚሰበሰብበመጥቅዕም በዓላትና አጽዋማት ይሰበሰባሉ። የሌሊቱን ሃያ ሦስት ሱባዔ ደግሞ በሰባት ስናባዛውአንድ መቶ ስድሳ አንድ ይሆናል፤ ይህንንም አምስትጊዜ በሠላሳ ስንገድፈው/ስናጣፋው/አሥራ አንድይቀራል፤ ይኸንን አበቅቴ በለው ብሎታል። ጥንተአበቅቴ የተባለው ይህ ነው። አበቅቴ ማለት፡- የወርሕጸጽ/ጉድለት/፣ ሠርቀ ሌሊት፣ ሠርቀ ወርኅ/የጨረቃ ምላትና ጉድ ለት/ የሚታወቅበትናየሚገለጽበት ነው። ሠርቅ ማለት፡- በቁሙ ሲተረጐም፥ መውጫ፣ መገለጫ፣ መባቻ፣ የወር መጀመሪያ ማለት ነው። ምንግዜም ቢሆን የመጥቅዕ እና የአበቅቴ ድምር ከሠላሳአይበልጥም ከሠላሳም አያንስም። ከዚህ በኋላቅዱስ ድሜጥሮስ የአጽዋማትና የበዓላት “ኢየዓርግእና ኢይወርድ”ተገልጾለት በሰባት አዕዋዳት አውዶ፣ በአንድ ዐቢይ ቀመር ወስኖ፣ በማኅተም አትሞ፡-በሮም፣ በሶርያ፣ በአንጾኪያ እና በኢየሩሳሌምለነበሩ ሊቃነ ጳጳሳት ልኰላቸዋል። እነርሱምሐዋርያት በዲድስቅልያ ካስተማሩት ጋር አንድ ሆኖ ቢያገኙት ተቀብለው አስተምረውታል። ሠለስቱ ምዕትም ጉባዔ ሠርተው አስተምረውታል። ቅዱስ ድሜጥሮስ ያረፈው ባሕረ ሐሳብን ከተናገረ በኋላነው።

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የዘመን አቆጣጠር (ባሕረ ሐሳብ) _ ክፍል አንድ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top