• በቅርብ የተጻፉ

    Friday 6 November 2015

    ‹‹ጾመ ነነዌ እና የኮብላዊው ነቢይ የዮናስ ተግባር›› በፖፕ ሺኖዳ ሶስተኛ እንደተጻ

    የነነዌ ጾም መቼምለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ከታላቁ ከጌታጾም በፊት  በእየአመቱ የሚጾም  ጾም  ነውናበደንብ ይታወቃል ይልቁን  አባቶቻችን እናቶቻችን‹‹ የነይነይ ጾም›› አስከማለት ደርሰው  ስምአውጥተውላታል፡፡ ስያሜው ከጾመ ነነዌ ወደነይነይ  የተቀየረው…በንባብ ተፋልሶ ይሁን ወይም ቶሎ ቶሎ ነይ ለማለት ተፈልጎ ….በእርግጥ አላውቅም፡፡ ወደ ዋናው አሳቤስገባ..የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሶስተኛመጽሀፍ የሆነውን ስለ ነቢዩ ዮናስ የተጻፈውን‹‹CONTEMPLATIONS ON THE BOOK OF JONAH THE PROPHET ›› የተባለውንመጽሀፍ ሳነብ ለወዳጆቼስ ትንሽ ባካፍል ብዬእንዲህ በውርስ ትርጉም አቀረብኩት፡፡

    መጽሀፍ ቅዱሱ ታሪኩን እንዲህ ብሎይጀምራል…..‹‹የእግዚአብሔርም ቃል ወደአማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲልመጣ።ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።ዮናስ ግንከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይኰበልልዘንድ ተነሣ ወደ ኢዮጴም ወረደ፥ ወደ ተርሴስምየምታልፍ መርከብ አገኘ ከእግዚአብሔርም ፊትኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።››ትንቢተ ዮናስ 1፡1

    1.  ‹‹ነቢዩ ዮናስ ራስ ወዳድ ነበር ›› 

    ወደ ነነዌ ሂድና ስበክ ሲባል እምቢ ያለውእንዲህ ብሎ አስቦ ነበር፡፡  ‹‹በአገሬ ሳለሁየተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅርባይ ፥ ታጋሽም ፥ ምሕረትህም የበዛ ፥ ከክፉውነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህአውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለልፈጥኜ ነበር።›› ትንቢተ ዮናስ 4፡3 እኔ ሄጄከተማዋ ትገለባበጣለች ብዬ ብሰብክ አንተመሐሪ ነህና አትቀጣቸውም ያኔ እኔ ደግሞሐሰተኛ ነቢይ ፤ቃሉ የማይፈጸም ተብዬእዋረዳለው ብሎ ራስ ወዳድ ሆኖ  ኮበለለ….

    2.  ነቢዩ ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት በመኮብለልጌታ ሲጠራው በዛፎች ስር እንደተሸሸገውየእግዚአብሔርነት ሁሉን አዋቂነትን እንደረሳውአዳም ሆነ

    በመዝ139፡7‹‹ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ?ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ ፥ በዚያአለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከባሕር መጨረሻም ብበርር ፥ በዚያ እጅህትመራኛለች ፥ ቀኝህም ትይዘኛለች። በውኑጨለማ ትሸፍነኛለች ብል ፥ ሌሊት በዙሪያዬብርሃን ትሆናለች ጨለማ በአንተ ዘንድአይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችናእንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።›› ተብሎቢጻፍም ቃሉን እንደማያውቅ ነቢይ ሆኖበመኮብለል የእግዚአብሔርን የገዢነት ክልልእንደማያውቅ ሰው ሆነ፡፡

    3.  መርከብ ላይ ለመሳፈር ዋጋ ከፍሎ ገባ

    በዚያን ዘመን መርከብ ላይ ለመሳፈር ብዙገንዘብ ይጠይቅ ነበር ዮናስም  ጌታን የምድር ብቻ ጌታ አድርጎ ከሱ በመኮብለል በባህር ላይለመሳፈር  ዋጋ ከፍሎ መርከብ ላይ ወጣ በዚህም ምክንያት በገንዘቡ ምክንያትንጽህናውን ቅድስናውን እንደሚያጣ ደካማ ሰውሆነ፡፡

    4.  ከዮናስ ክፋት በላይ የሚደነቀው የእግዚአብሔር ደግነት ዮናስን ተቀይሞ ዝምአላለውም የሱን ክፋት ለደግነት ተጠቀመው ……መርከበኞችም ከእሱ የተሻሉ ሆኑ

    ዮናስ ባለመታዘዙ ምክንያት መርከበኞቹ ዳኑ ፤ቀጥሎ ደግሞ በግድም ቢሆን ታዞ ነነዌእንዲድኑ ሆነ ፤  ፈጣሪ ነቢዩ ዮናስ አልታዘዝሲለው ግዑዙን ፍጥረታት አዘዘ ፤ ንፋሳትታዘዙት….‹‹እሳትና በረዶ አመዳይና ውርጭ ፥ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም…የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ›› መዝ 148፡8ተብሎ እንደተጻፈ ቃሉን የሚያደርገው አውሎንፋስ መጣ ፤ ‹‹እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይታላቅ ነፋስን አመጣ፥ በባሕርም ላይ ታላቅማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።››ትንቢተ ዮናስ 1፡4

    ነገር ግን ዮናስ በመርከቧ ከገባ በኋላ ምንምየኃጢአተኝነት ስሜት ሳይሰማው እንቅልፉንተኝቶ ስለ ነበር ይልቁን በሱ ምክንያት  መርከቧስትናወጥ አሱ ግን ምንም ያወቀው ነገርአልነበረም ፡፡ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበርእነዛ አህዛብ  መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱምወደ አምላኩ ጮኸ መርከቢቱምእንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃወደ ባሕር ጣሉት ፡፡በዚያን ሰዓት የማይጸልየውብቸኛው  ሰው የእግዚአብሔር ነቢይ ዮናስ ነበር፡፡እንዴት ከዚህ ሁሉ በደል በኋላ የሰላም እንቅልፍይልቁን ጥልቅ እንቅልፍ ሊተኛ ቻለ ቢባልምክንያቱ በራሱ ድርጊት ትክክል ነኝ ብሉስለሚያምን ነበር :: የመርከቡም አለቃ ወደእርሱ ቀርቦ። ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋእግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህአምላክህን ጥራ አለው።….አርሱምከእግዚአብሔር ሲኮበልል አግዚአብሔር ደግሞአህዛቡን አስነስቶ  ወደ አምላክህ ጸልይ አለው፡፡ነቢዩ ወደ ፈጣሪው እንዲጸልይ በአህዛቡተሰበከ፡፡

    ነገር ግን መርከቧ አልተረጋጋችም  እነሱየዕምነት ሰዎች ነበሩ ፤ ፈጣሪ የችግሩንምክንያት እንደሚገልጥላቸው አምነው ዕጣተጣጣሉ ዕጣው ለነቢዩ ዮናስ ላይ ወጣ፡፡ወዲያውም አልፈረዱበትም ምንም ክፉ ነገርአልተናገሩትም ራሱን እንዲከላከል በስርዓትእንዲህ ብለው ጠየቁት ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት።እርሱም፦ እኔ ዕብራዊ ነኝ በሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን እመልካለሁ እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው አውቀዋልና እጅግ ፈርተው። ይህ ያደረግኸው ምንድር ነው? አሉት።››ትንቢተ ዮናስ 1፡8-10

    11 ባሕሩንም ሞገዱ አጥብቆ ያናውጠው ነበርና። ባሕሩ ከእኛ ዘንድ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ? አሉት።

    12 እርሱም፦ ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው።

    ብዙ አማልክት የነበራቸው የሰማይና የምድርጌታ እሱ አገልጋዩ ሲኮበልል  እንዲህ አደርጎበድንቅ መለሰው ብለው ፈሩት፡፡ አወቁትም… ‹‹ባሕሩንም ሞገዱ አጥብቆ ያናውጠው ነበርና። ባሕሩ ከእኛ ዘንድ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ? አሉት።እርሱም፦ ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው።›› ትንቢተ ዮናስ  1፡11….አሱ ለብዙ ሺ የነነዌ ህዝብማሰብ ሲያቅተው መርከበኞቹ  ለአንድ ለሱተጨንቀው ባላቸው አቅም ሁሉ ጥረው አቃታቸው ፤ የሚገርም ጥረት ነበር አደገኛ ጥረትሕይወታቸውን ነበር የሰጡት ምክንቱም እሱንለማዳን በሚደርጉት ጥረት መርከቧ ልትሰበርትችል ይሆናል ብለው በመፍራት እሱን ወደባህር ለመጣል አልተሸቀዳደሙም ፤ ወደ ምድሩሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግአብዝቶ ይናወጥባቸው ነበርና አልቻሉምሲያቅታቸው….‹‹ስለዚህ ወደ እግዚአብሔርጮኸው። አቤቱ፥ እንደ ወደድህ አድርገሃልናእንለምንሃለን አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው ነፍስእንዳንጠፋ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳታደርግእንለምንሃለን አሉ።ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩጣሉት ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ።ሰዎችምእግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፥ ለእግዚአብሔርምመሥዋዕትን አቀረቡ፥ ስእለትንም ተሳሉ።››ትንቢተ ዮናስ   1፡14 ፡፡

     የሚስገርመው የነዚህ ሰዎች ንግግር ነበር ለዛሁሉ መከራ ችግር ሀብትና ንብረታቸውን ወደባህር ለመጣል ምክንያቱ ዮናስ ሆኖ….. በእጣየችግሩ ባለቤትን ሲያገኙ ሊፈርዱበትአልፈለጉም ለማትረፍ የአቅማቸውን ሁሉ ጣሩ ፤በመጨራሻም ሲያቅታቸው ‹‹የንጹሕም ደምበእኛ ላይ እንዳታደርግ እንለምንሃለን››ለውየዮናስን ደም ንጹህ ብለው ጠርተው ወደባህርጣሉት ፤ መርከቧም ጸጥ አለች ፤ እነሱምበፈጣሪ አመኑ ለሱም መሰዋዕት አቅራቢበመሆን ዳኑ ፤ መርከበኞቹ ይገርሙ ነበርመርከቧ እየተናወጠች የመርከቧን መናወጥችግር አውቀው በነውጡስ ሆነው እሱ ለማትረፍሞከሩ ፤ ማነው እንዲህ ሚያደርግ ????

    5.  ዮናስም ወደባህር ሲጣል አሳ አንበሪ ሆድለሶስት ቀን በመቆየት የጌታ ምሳሌ ሆነ

    ዮናስ ነነዌን ትቶ ተርሴስ የሄደው ከእግዚአብሔርበመኮብለል ነበር ፤ አሱ ሰብኮ ሕዝቡንየእግዚአብሔር ምህረት ከሚያድነው……በውጤቱም ክብሩን ከሚያጣ ውሸተኛከሚባል… ብሎ ሲሸሽ መርከቧ ተናውጻ ወደባሀር ሲጣል…ሕዝቡን ለማዳን  ክብሩን አዋርዶበሞቱ ሊያከብረን ለመጣው ለጌታ  ሞት እናትንሳዔ ምሳሌ ሆነ፡፡ ‹‹እርሱ ግን መልሶ እንዲህአላቸው፦ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክትአይሰጠውም። ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስትቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰውልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊትይኖራል።››ማቴ 12፡40

    6.  ዮናስን ሊያርመው…. አስተምሮ ሊልከውየወደደ ጌታ ባህር ውስጥ አሳ አንበሪንአዘጋጀለት

    መጽሀፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚነግረን ትልቁ አሳአንበሪ ዮናስን ዋጠው፡፡የአሳ አንበሪው ሆድ ሌላጊዜ የዋጠውን እንደሚፈጭ ያይደለጨጓራውም ሌላ ጊዜ  እንደሚያመነጨውዳጄስቲቭ እነዚያም ሳይሆን  ለሱም የሶስት ቀንቤት ሆነለት ፤ በዛም በእምነት ድንቅ የሆነ ጸሎትጀመረ እንዲህም አለ፦  በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።… በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።…..እኔ ግንበምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ የተሳልሁትንምእከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱምዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።››ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ  2

    7.   ዮናስ ነነዌ ገብቶ በጣም በሚያስገርምመልኩ አጭር የሆነ ስብከት ሰበከ

    ከአሳ አንበሪ ሆድ ከሶስት  ቀን በኋላ የተተፋውዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ በቀጥታ ሄደ..ነነዌ የሶስትቀን ያህል ጊዜ የምትወስድ ታላቅ ከተማነበረች…አሱም በሚያስገርም መልኩ  ብዙስብከት መስበክ ሲችል ስለንስሀ ማስተማርሲችል ወደ ከተማ የአንድ ቀን ያህል መንገድከገባ በኋላ አጭር ቃል ብቻ ተናገረ…‹‹በሦስትቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።›› ትንቢተ ዮናስ 3፡4

    8.   የነነዌ ሰዎች ታላቅ ጾም አወጁ

    ንጉሱ ታላቅ አዋጅ አወጣ  እኛ በበደልነው በደል ሕጻናት ሆኑ እንሰሳት መቀጣታቸው አይቀርምናሁሉም ይጹሙ በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ ፤የሚያስገርም የጾም አዋጅ  .. የጾም ትክክለኛትርጉም የታየበት..ንስሀ እና ጦም የተዋሀዱበትአዋጅ…..  ‹‹ንጉሱም ከዙፋኑ ተነሥቶመጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥በአመድም ላይ ተቀመጠ››  ትንቢተ ዮናስ  3፡1

    9.   ፈጣሪ ጦመ ንስሀቸውን ተቀበለ ዮናስተበሳጨ   በቅል ፤ በጸሀይ ፤ በንፋስአስተማረው  

    ‹‹እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውእንደተመለሱ ሥራቸውን አየ እግዚአብሔርምያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶአላደረገውም።››ትንቢተ ዮናስ  3፡10 ዮናስ ግንተበሳጨ ‹‹ አቤቱ፥ እለምንሃለሁ በአገሬ ሳለሁየተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅርባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉውነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህአውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለልፈጥኜ ነበር።››ትንቢተ ዮናስ  4፡2 ፈጣሪምየከተማውን መቃጠል ለማየት ተራራ ላይ የተቀመጠውን ዮናስን በዕለት በቅላ ከጸሀይሙቀት ኣሳርፋው  በዕለት በደረቀችው ቅልሲበሳጭ እንዲህ ብሎ አስተማረው……‹‹ አንተትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትምለደረቀችው ቅል አዝነሃል።እኔስ ቀኛቸውንናግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማለነነዌ አላዝንምን? አለው።››ትንቢተ ዮናስ  4፡10

    አባቶቻችን ስንጾም አለንስሀ  መጾምእንደማይገባን ለማሳየት ከታላቁ ጦመ ሁዳዴበፊት ንስሀ ጎልቶ የወጣበትን የነነዌን ጾም ለዝግጅት እንድንጾም አደረጉን

    ከጾሙ አንድንጠቀም የነነዌን ሰዎች የንስሀ ልብ ይስጠን!!!

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ‹‹ጾመ ነነዌ እና የኮብላዊው ነቢይ የዮናስ ተግባር›› በፖፕ ሺኖዳ ሶስተኛ እንደተጻ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top