• በቅርብ የተጻፉ

    Friday 6 November 2015

     በአንድ ቀን ውስጥ የተመደቡ የጸሎት ጊዜያት


    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ዓሃዱ አምላክ አሜን

    በ አንድ ቀን ውስጥ የተመደቡ የጸሎት ጊዜያት

    በኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተክርስትያን ስርዓት መሰረት በአንድ ቀን ውስጥ የተመደቡ የጸሎትጊዜያት ሲኖሩ እነርሱም ሰባት (፯)ናቸው። አንድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰውቢችል በ አንድ ቀን ዉስጥ  ሰባቱንም ጸሎታት ማድረስይኖርበታል፣ በስራ ወይም በተለያዩማህበራዊ ጉዳዮች ሳይመቸውቢቀር ቢያንስ በጸሎቱ ሠዓታትሚታሰቡትን ነገሮች አስቦ ማሳለፍይኖርበታል። ነገር ግንእናመሰግነው ዘንድ ለፈጠረንአምላክ በስራስ ቦታ ቢሆን የሁለትእና የሦስት ደቂቃ ጊዜ እነዴትእናጣለታለን ? እና ከቻልን አቡነዘበሰማያት ( አባታችን ሆይ )የምትለዋን አጭር ጸሎት ብናደርስይመረጣል። ያንንም እናደርግ ዘንድእግዚአብሄር ይርዳን !

    ከቀኑ የመጀመርያው ጸሎት ”የንግህ ጸሎት ” የሚባል ሲሆንእርሱም ከንጋቱ አንድ ( ፩) ሠዓትገደማ የሚጸለይ ጸሎት ነው። ይህንየንግህ ጸሎት ስንጸልይ፦ የለሊቱንጨለማ አርቀህ በሰላም የቀኑንብርሃን ያመጣህልን ወይምያሳየኸን አምላክ ተመስገንበማለት፣ የሁሉ አባት አዳምየተፈጠረበትን ሠዓት እና ጌታችንእና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስበዺላጦስ ፊት ቆሞየተመረመረበትን ሠዓት በማሰብእና በማስታወስ የሚጸለይ ጸሎትነው።

    ሁለተኛዉ ጸሎት ደግሞ ” የሦስትሠዓት” ጸሎት የሚባል ሲሆን ይህንጸሎት ስንጸልይ፦ የሁሉ እናት ሄዋንየተፈጠረችበት ሠዓት፣ ነብዩዳንኤል በምርኮ በሚኖርበትበባቢሎን ሳለ በእየሩሳለምአቅጣጫ ያለዉን መስኮቱን ከፍቶየጸለየበት ሠዓት፣ እመቤታችንቅድስት ድንግል ማርያምከመላዕኩ ከቅዱስ ገብርኤልሠማያዊ ብስራት የሰማችበትሠዓት፣ ጌታችን እና መድኃኒታችንኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊትየተገረፈበት ሥዓት እንዲሁምመንፈስ ቅዱስ በጵርሐ ፅዮንበሐዋርያት ላይ የወረደበት ሠዓትስለሆነ እነዚህን ድርጊቶች እናሰዓቶች በማሰብ የሦስት ሠዓቱንጸሎት እናደርሳለን።

    ሦስተኛዉ ጸሎት  ” የስድስትሠዓት ጸሎት”   የሚባል ሲሆን።በቀትር ከፀሀይ ሙቀት የተነሳሰውነት ሲዝል ሃሳብ ( አእምሮ )ሲበተን አጋንንት ስለሚሰለጥኑያንን የመናፍስት ጦር ለመከላከልበተለይም ጊዘው

    -ሄኖክ ቤተመቅደስ ያጠነበት

    -ይልቁንም ጌታችን እናመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስዓለምን ለማዳን ሲል በቀራንዮአደባባይ የተሰቀለበት ሠዓትስለሆነ ህማማተ መስቀሉንእያሰብን የምንጸልየው ጸሎት ነው።

    አራተኛው ጸሎት ደግሞ ” የዘጠኝሠዓት” ጸሎት ይባላል። ይህቺሠዓት መላዕክት የሰውን ምግባርእና ፀሎት የሚያሳርጉባት ከዚያምበላይ ጌታችን እና መድኃኒታችንኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሳለ  ጎኑን በጦር ተወግቶ ደሙንከማፍሰሱ በፊት ” ተፈፀመ” ብሎነፉሱን ከስጋው የለየባት ሠዓትስለሆነች፣ ይህንንም ስለ እኛ ሲልማድረጉን ( ስለ እኛ   ሲል ነፍሱንመስጠቱን እያሰብን ) የምንጸልየውጸሎት ነው።

    አምስተኛዉ ጸሎት ”የሰርክ ጸሎት ”ሲሆን ከ 11-12 ሠዓት ባለው ጊዜዉስጥ ይጸለያል። ሰው ሲሰራውሎ ዋጋዉን ወይም የእለትአበሉን የሚቀበለው በሰርክአንደመሆኑ ምዕመናንም ምግባረትሩፋታቸዉን ሲሰሩ ኖረውዋጋቸዉን ከፈጣሪያቸውየሚያገኙት በዕለተ ምፅዓትስለሆነ የሰርክ ጸሎት በጌታ ዳግምምጽሃት ይመሰላል። እንዲሁምጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ ህማማተ መስቀሉንጨርሶ ከተገነዘ በሗላ በስጋ ወደመቃበር የወረደበት ሠዓት ስለሆነያን የመለኮት ፍቅር በማሰብበጸሎት የምንጠመድበት ጊዜነው።

    ስድስተኛው ጸሎት ” የማታ ጸሎት”ይባላል። ይህም ጸሎት ከመኝታበፊት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይይጸለያል። ፈጣሪያችን በቸርነቱየቀኑን ድካም አሳልፎ የለሊቱንእረፍት ስላመጣልን እያመሰገንን፣ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ በምሽተ ሐሙስበጌቴሲማኒ በአትክልቱ ቦታስለጸለየው ጸሎት እና በዚያን ጊዜስለ እኛ ሲል በጭንቀት ከእኛየሞትን ፍርሃት አስዎግዶልንየዘለዓለም ደስታን እና ህይወትንያቀዳጀን መሆኑን በማሰብ ለእርሱምስጋናችንን ከማቅረብ ጋርየሚጸለይ ጸሎት ነው።

    ሰባተኛው እና የመጨረሻው ጸሎት”የእኩለ ለሊት” ጸሎት የሚባልሲሆን ከለሊቱ ስድስት (6) ሠዓትላይ የሚጸለይ የምስጋና ጸሎትነው።   ሠዓቱ ጳውሎስ እና ሲላስበእስርቤት ሣሉ ጸልየውበእግዚአብሔር ሀይልከእስራታቸው የተፈቱበት፣ ጌታችንእና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስየተወለደባት እንዲሁም ሞትን ድልነስቶ የተነሳባት ዳግመኛምበህያዋን እና በሙታን ለመፍረድየሚመጣባት ሠዓት ስለሆነች ይህን ሁሉ በማሰብ እናእግዚአብሔር ለእኛ ሲልያደረገዉን ነገር ሁሉ በማሰብየሚጸለይበት ሠዓት ነው።

    ይቆየን ወስብሃት ለእግዚሃብሔር

    ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖቴ 

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed:  በአንድ ቀን ውስጥ የተመደቡ የጸሎት ጊዜያት Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top