ብሂለ አበው
ò ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው፡፡
ቅዱስ ስራፕዮን
ò የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ ፡፡
መጽሐፈ ምክር
ò አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት ያርቀዋል፡፡
አረጋዊ መንፈሳዊ
ò ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ፡፡
ማር ይስሐቅ
ò ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል፡፡
አረጋዊ መንፈሳዊ
0 comments:
Post a Comment