• በቅርብ የተጻፉ

    Wednesday, 11 November 2015

    ቅዱስ ጊዮርጊስ

    የቅዱስ ጊዮርጊስ አባቱ መስፍን ሲሆን ሲሙም አንስጣስዮስ ይባላል አገሩም ቀጰዶቅያ ሲሆን እናቱም ቴዎብስታ ትባላለች እሱአም ከፍልስጤም አገር ናት ከዛም ትንሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ: 20 አመትም በሆነው ግዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉስ ዱድያኖስ ዘንድ ሄደ:ንጉሱም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲያመልኩ ሰዎችን ሲያስገድዳችው አገኘው:ይህንን አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዘነ በርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድሆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነጻ አወጣቸው:ከዛም በንጉስ ፊት ቆሞ በክብር ባለቤት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ:ንጉሱም አባበለው ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም:ለመስማት እንኩአን የሚያስጨንቅ ስቃይን አሰቃየው ጌታችን ግን ሁሌም ያጸናዋል ቁስሉንም ያድነዋል:3 ግዜ እንደሚሞት እሱም እንደሚያስነሳው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው:ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በአለም ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ:በተጋድሎ እና መከራ በመቀበል ሰባት አመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው: ንጉሱም ባለመታዘዙ እና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ስራየኛ አመጣና እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ ሞልቶ አስማቱን ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው:ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር ቅዱሱም ያንን ጽዋ በጌታችን ስም አማትቦ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም:ያ መሰርይም በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ወዲያው ሰማእት ሆኖ አረፈ:ያንንም ተአምር አይተው ብዙዎች ሰዎች በሰማእትነት ሞተው የህይወት አክሊል ተቀበሉ ቁጥራቸውም 30,700 ነፍሳት ናቸው:ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባው ነገስታት ፊት በቆመ ግዜ በዚያም የተቀመጡባቸው ወንበሮች ነበሩ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸው ወንበሮች እንዲበቅሉና እንዲያብቡ እንዲያፈሩም ታደርጋቸው ዘንድ ካንተ እንሻለን አሉት:በዚአን ግዜም ጸልዮ እንዳሉት አለመለመው ይህንን ድንቅ ስራ አይተው ቁጥር የሌላቸው ብዙ አህዛብ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ:ከዛም ቅዱሱን ወስደው በጎድጉአዳ ምጣድ ውስጥ አበሰሉት:አቃጥለው አሳርረውም ስጋውንንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት:ጌታችንም ነፍሱን ወደ ስጋው መልሱአት ደግሞ አስነሳው:ወደ ነገስታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማረ ቁትር የሌላቸው አህዛብ አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማእትነት ሞቱ:ነገስታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታስነሳ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናምናለን በርሱም እናምናለን አሉት ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጉአድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶችን ጎልማሶችንም አስነሳላቸው እነዛም በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማሩ የገሃነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው አረፉ: ከሃድያን ነገስታቱ ግን ሙታንን ያስነሳህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ ከዚአም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሳ ከአንዲት ደሃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እሱአም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሄርም መልኣክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ መኣድ አቀረበለት የዚያች መበለትም የቤቱአ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ ያችም መበለት በተመለሰች ግዜ የቤቱአ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ሲለማእዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደ እኔ መጣ አለች ቅዱሱም እኔ አምላክ አይደለውም የአምላክ ባርያ ነኝ እንጂ አላት እሱአም እንዲ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ችርነትህ እንድትደርሰኝ እለምንሃለው እውር ደንቆሮ ድዳ ጎባጣ የሆነ ልጅ አለኝ እና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለው ስለጌታችን እምነትም አስተማራትና መበስቀል ምልክት አማተበው ያን ግዜም ልጁ አየ ቅዱሱም በሌላ ግዜ እንዲሰማ እንዲናገር እና እንዲሄድ እንዲያገለግለኝም እኔ እሻለው አልት በዚአን ግዜ ንጉሱ በአገሩ መዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያችን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለሱአም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሱአ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቱአ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት ንጉሱም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አስገረፈው በመንኮራኩርም አበራዩት ሞቶም ከከተማ ውጩ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሳው ወደ ነገስታቱም ተመለሰ ንጉሱም አይቶ ደነገጠ ስለህይወቱም አደነቀ ከዚያም በሁአላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግስቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊሲም እየዘበተበት ነገ በጠዋት ለአምልክቶችህ መስዋትን አቀርባለው አንተም ህዝብ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሰዋ እንዲያዩ አለው:ንጉሱም እውነት የሚሰዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግስቱም እልፊኝ አስገብቶ አሳደረው ለጸሎትም ተነሳ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለእስክንድርያ ንግስት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጉምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሄር አለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ግዜ የሆነውን ሁሉ ያስረዳት ጀመር ትምህርቱም በልቡአ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች በማግስቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሰዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዋጅ ነጋሪ ዞረ የበቱአን ሚሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ እውነት መስሉአት እጅግ እያዘነች ልጁአን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች ቅዱስ ጊዮርጊስም ባያት ግዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዛም ልጁአን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሂድ ወደ እኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው ያን ግዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ አዘዘው ወደ ጣዎቱ ቦታ ሄዶ አዛዘው በጣዖቱ ያደረ እርኩስ መንፈስም ከማደሪአው ወቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳለበት መቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለውም ብሎ በህዝብ ሁሉ ፊት አመነ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋር አጠፋቸው ንጉሱም ከወገኖቹ ጋር አፈረ:ብስጭት እና ቁታንም እንደተመላ ወደ ንግስት ምስቱ ዘንድ ገባ እሱአም አምላካቸው ጽኑ እና ሃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጥላቸው አላልኩህምን አለችው ይህንንም ከሱአ ሰምቶ በርሱአ ላይ እጂግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለበት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ ከዚም በሁአላ ከከተማ ውጪ እንዲጎትቱአት እና በመጋዝም እንዲሰነጥኩአት አዘዘ የሰማእትነትንም አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበለች በዚያን ግዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስራ ነገስታቱ ሁሉም ደነገጡ ሃፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከርሱም እንድያርፍ ራሱን በስይፍ ይቆረጥ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉስ ዱድያኖስን መከሩት ያን ግዜም የክብር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ሰንድ አዘዘ ድል አድራጊ ጊዮርጊሲም እጂግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገስታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው ወዲያው እሳት ከሰማይ ወርዶ ከነሰራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገስታት አቃጠላቸው ከዚም በሁአል የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው በምድር መታሰቢያህን የሚያደርጉ ሁሉ እኔ ሃጥያቱን ሁሉ ደመሣለው በመከራም ውስጥ ሆኖ በባህርም ሆነ በየብስ,ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለው ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ ከዚ በሁአላ ከ7አመት ተጋድሎ በሁአላ ሚያዚያ 23 ቀን ራሱን ዘንበል አድሪጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግስተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሲጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሃገሩም ልዳም ወሰዱት ቤተ ክርስቲያንም ሰርተው በውስጡአ አኖሩት ከርሱም ቁጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጠ ለእግዚአብሄርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊዮርጊሲም በረከቱ ረድኤቱ ሃገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቦቹአን ከስጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቅልን!!!!!..................

    .ቸር ያቆየን!

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ቅዱስ ጊዮርጊስ Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top