• በቅርብ የተጻፉ

    Monday 9 November 2015

    የብሕትውና(የምንኩስና) ኑሮ - ክፍል 1


    1.አጀማመር

    1.1 በሕገ ልቡና

    የብሕትውና ኑሮ የተጀመረው ከሰው ልጅ ወደዚህችምድር መምጣት አንሥቶ ነው፡፡ ደቂቀ ሴት ከቃየልልጆች ኑሮና ግብር ተለይተው በደብር ቅዱስበንጽሕና በቅድስና ይኖሩ እንደነበር ቅዱስ መጽሐፍይነግረናል( ዘፍ.6÷1-3፤ ሄኖክ 2÷1-2)

    አባታችን ሄኖክም በዘመኑ ከነበሩት ግብረሰዶማውያን ርቆ፣ ሰዎችን ለጥፋት ውኃ ከዳረገውኃጢአት ተለይቶ፣ ንጹሕ እግዚአብሔር ንጽሕናንይሻል በማለት በሕገ ልቡና ተመርቶ በእግረ ገነትለሰባት ዓመታት በብሕትውና ከኖረ በኋላ በልዑልእግዚአብሔር ፈቃድ ከአካለ ሥጋ ወደ ብሔረሕያዋን መነጠቁን መጽሐፈ ሄኖክ ያስረዳል፡፡የመልከ ጼዴቅም የኑሮ ሥርዓት ይህንኑየባሕታውያን ሕይወት የተከተለ ነበር( ዘፍ.14÷17-24)፡፡

    1.2 በሕገ ኦሪት

    ይህ የብሕትውና ኑሮ ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪትተላልፎ አባታችን ኤልያስን የመሰለ መናኝለማስገኘት በቅቷል፡፡ የኤልያስንም ሕይወት ደቀመዝሙሩ ኤልሳዕ ተረክቦታል፡፡

    ኤልያስ ደቀመዝሙሩን ኤልሳዕን ተሰናብቶ በእሳት ሠረገላ ሲያርግ

    1.3 በዘመነ ሐዲስ

    መጥምቁ ዮሐንስ

    ወደ ዘመነ ሐዲስም ስንመጣ የዮሐንስ መጥምቁሕይወት የዚህ ተከታይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ቅዱስዮሐንስ የ3ዐ ዓመት ወጣት ሆኖ እስኪገለጥድረስበጨው ባሕር አጠገብ በሚገኘው የቁምራን ገዳምየኖረ ሲሆን በኋላም የግመል ፀጉር ለብሶ የበረሃአንበጣ እየበላ በሄኖም ሸለቆ በመኖር በዮርዳኖስወንዝ ሕዝቡን በንስሐ ጥምቀት ያጠምቃቸው ነበር(ማር.1÷1-11)፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስስለ ሐዲስ ኪዳኑ ባሕታዊ ስለ መጥምቁ ቅዱስዮሐንስ ‹‹እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ››በማለት መስክሮለታል ( ዮሐ.5÷35)፡፡

    የቁምራን ገዳም

    መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ

    መጥምቁ ዮሐንስ

    ልዑለ ባሕርይኢየሱስክርስቶስምበ3ዐ ዘመኑበፈለገዮርዳኖስበዕደ ዮሐንስከተጠመቀበኋላ ወደቆሮንቶስገዳምበመግባትየምናኔን እናየብሕትውናንኑሮ አጽንቶ አስተምሮናል፡፡ ዛሬ አሠረፍኖቱን የተከተሉት አባቶቻችን እንደሚያደርጉት ሁሉበነዚያ 4ዐ ቀናት ወደ በረሃ ወርዶ ከአራዊት ጋር ኖረ( ማር.1÷13)፡፡ ከዲያብሎስ ተፈትኖ ድልበማድረግም ድል የምናደርግበትን ኃይል ሰጠን፡፡መድኃኒታችን ወዶ ፈቅዶ አርአያ ምሳሌ ይሆነንዘንድ በገዳመ ቆሮንቶስ ዲያብሎስን ድል ባደረገውጊዜ መላእክት አገለገሉት፡፡ በዚህም እኛ እሱንብንመስለው ዲያብሎስንም ድል ብንነሣውኑሮአችን ከመላእክት ጋር እንደሚሆንአስተማረን(ማር.1÷13፣ ማቴ 1÷11)፡፡

    በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱ መድኃኒታችንን‹‹መጋባት አይጠቅምምን›› ብለው በጠየቁት ጊዜእንዲህ በሚል ቃል አስተምሯቸውነበር፡፡ «ይህ ነገርለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም፡፡ በእናትማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፡፡ ስለመንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦችአሉ፡፡ ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው» (ማቴ.19÷10-10)፡፡

    ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን የሰለቡጃንደረቦች የተባሉት ሁሉ እያላቸው፣ ሁሉን ማድረግእየቻሉ ነገር ግን ይህንን ዓለም ንቀውመድኃኒታቸውን መስለው፣ ድምፀ አራዊትን ግርማሌሊትን ታግሠው፣ የእሾህ አክሊሉ ምሳሌ የሆነውንቆብ ደፍተው፣ ምድረ በዳ ወርደው ከአራዊት ጋርእየኖሩ (ማር.1÷13) ከዲያብሎስ ጋር የሚጋደሉትየሃይማኖት አርበኞች ናቸው፡

    ጃንደረብነት ሦስት ዓይነት መሆኑን ጌታችንገልጦልናል፡፡ በተወለዱ ጊዜ በችግር ምክንያትጃንደረቦች (ስልቦች) የሆኑ አሉ፡፡ በሌላ በኩልደግሞ በአገራችን አንዳንድ ቦታዎች፣በመካከለኛውና ደቡባዊው አፍሪካ በአብዛኛውእንደሚታወቀው የማኮላሸት ተግባርየሚፈፀምባቸው አሉ፡፡ ሳይፈልጉ በሰዎችአስገዳጅነት የሚሰለቡ እንዳሉ ሁሉ ሥልጣን ሽተውማዕረግ ፈልገው ጃንደረባ የሚሆኑም አሉ፡፡

    የቁምራን ገዳም

    ሦስተኛዎቹ ግን «ሁሉን ትተህ ተከተለኝ» ያለውንቃል ሰምተው፣ ያላቸውን ሁሉ ለመንግሥተሰማያትጌታ ለቅዱስ እግዚአብሔር ሲሉ ርግፍ አድርገውየተከተሉት፤ ከዚህ ዓለም ግብር ርቀው የዘወትርሥራቸው ጸሎትና መዝሙር፤ ቅዳሴና ስግደት የሆነምድራውያን መላእክት ናቸው፡፡ ጌታችን ይህንንጉዳይ ለሀብታሙ ጎልማሳ ጥያቄ በሰጠው መልስላይ አጠናክሮ አብራርቶ አስተምሮናል፡፡

    ባለጸጋው ‹‹የዘላለምን ሕይወት እወርስ ዘንድ ምንላድርግ?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ ጌታ «ትእዛዛትንጠብቅ» በማለት የወጣንያንን ትምህርትአስተማረው፡፡ ጎልማሳው ግን ‹‹ይህን ሁሉማከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ ደግሞስ የሚጐድለኝምንድነው?›› በማለት ጠለቅ ብሎ ጠየቀ፡፡ በዚህጊዜ ‹‹ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሽጠህለድኾች ስጥና ተከተለኝ›› ሲል አስተማረው፡፡ጐልማሳው ግን ይህን መሸከም አቅቶት ለንብረቱሳስቶ እያዘነ ሄደ (ማቴ.19፣16-212)፡፡ ለዚህ ነበርጌታችን ‹‹ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው›› በማለትያስተማረው፡፡

    አባቶቻችን መነኮሳትና ባሕታውያን በረሃየወረዱት፣ሁሉን ሽጠው፣ለድኾች መጽውተውየመነኑት ይህንን ጌታ ለፍፁማን የሰጠውንትምህርት መሠረት አድርገው ነው፡፡

    1.4 በመጀመርያዎቹ  ክርስቲያኖች

    መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ

    ይህኑሮበመጀመሪያው መ/ክ/ዘመን በነበሩ ክርስቲያኖችዘንድ የተለመደ እንደነበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስለዕብራውያን በላከው መልእክቱ ፍንጭ ሰጥቶናል፡፡‹‹ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ የበግና የፍየልሌጦ ለብሰው ዞሩ፡፡ ዓለም አልተገባቸውምናበምድረ በዳና በተራራ፣ በዋሻና በምድር ጉድጓድ(ግበበ ምድር) ተቅበዘበዙ›› ሲል (ዕብ 11÷37)፡፡ዛሬም በየበረሃው የፍየል ሌጦ ለብሰው አበውየሚጋደሉት የእነዚህን ክርስቲያኖች አርአያአንሥተው ነው፡፡

    ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የትዳርን ነገርበተናገረበት አንቀጹ «ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆንእወዳለሁ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔርለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፡፡ አንዱ እንደዚህሁለተኛውም እንደዚያ» በማለት የክርስቲያኖች የኑሮሥርዓት ሁለት ዓይነት መሆኑን አስተምሮናል(1ቆሮ.7÷7)፡፡ እነዚህም የትዳር እናየብሕትውና(ምንኩስና) ሕይወት ናቸው፡፡የብሕትውና (ምንኩስና) ኑሮ ከጥንት ከዘመነ አበውጀምሮ የመጣ፣ ጌታችን ያጸናው፣ ሐዋርያት የሰበኩትመጽሐፍ ቅዱስዊ ትምህርት እንጂ «ብዙ ተባዙ»ከሚለው አንቀጽ ጋር የሚጋጭ ሰው ሠራሽ ሥርዓትአይደለም፡፡

    2. የሥርዓተ ምንኩስና ታሪክ

    ይቀጥላል - ይቆየን

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር

    ዋቢ

    1.    ትንሣኤ ቁ.99/1978

    2.    ገድለ አባ ሊባኖስ

    3.    ገድለ አባ ዮሐንስ

    4.    ዜና መንዝ

    5.    የአንኰበር መሳፍንት የታሪክ መጽሐፍ

    6.    ትንሣኤ ቁ.11/79

    7.    ትንሣኤ ቁ.22/80

    8.    Conti Rossini, steria PL.XLIV

    9.    ሉሌ መላኩ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አ.አ1986

    10. አባ ጎርጎርዮስ፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለምመድረክ

    11. አባ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንታሪ

    ሐመር መጽሔት

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: የብሕትውና(የምንኩስና) ኑሮ - ክፍል 1 Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top