አስተበቊዓክሙ ከመ ትትወከፍዋ ለሃይማኖትእንተ ተውህበት ሎሙ ለቅዱሳን፡፡ ይሁ. 1፥ 3
በመምህር ጽጌ
ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ስለ ተገለጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድሆነብኝ:: የሃይማኖት ስር መሠረቱ በሰብአዊ ፍጡር ምርመር የተገኘ፣ በስነ መለኮት ምሁራን አስተያየት ተሰጥቶበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፣ እየተመረመረ ሲወርዱ ሲዋረደ እኛ ዘንድ የደረሰየእምነት ዕቃ አይደለም፡፡ ወይም ጥላ እሸትቀቢዎች እንደሚያሰራጩት ውስጡን ሳናውቀውከውጪ አገር በአደራ የመጣልን የታሸገ ፓስታ አይደለም፡፡ “ሃይማኖትሰ፣ ጥይቅት፣ ይእቲ፣ ለዘይሴፈዋ” ይላታልና ዕብ. 11፥1፡፡ ይህን ለመረዳት እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን፡፡ በማስተዋል እየፃፍኩ ነው እናንተምአስተውላችሁ አሜን! በሉ፡፡ ይህ ማለት ሳይገባችሁ እንደ መፈክር በሚያስተጋባ ድምፅ በአሜንታ አጅቡኝ ማለቴ አይደለም፡፡ በማስተዋል አሜን! አላችሁ? እሺ ስለ ሃይማኖት እያወራን ነው፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 8 ና9፤ ከሊቃውንትም ኤጲፋንዮስና ዲዮስቆሮስበቅዳሴአቸው ስለ ጥበብ ርቀትና ምጥቀት ሲፅፉ፡አይቴ ብሔራ ለጥበብ፣ አይቴ ማህደራ ለጥበብ፣ አይቴ ደወላ ለጥበብ፣ ወአይቴ ተረክበ አሰረ ፍኖታ፣ ወመኑ አደወ ባሕረ ወተሳየጣ በወርቅ ቀይሕ“የጥበብ አገሯ ወዴት ነው፣ ማደርያዋ የት ነው፣አድራሻዋስ ወዴት ነው፣ ኮቴዋስ የት ተገኘ፣ ባሕርንተሻግሮ በቀይ ዕንቊ የገዛትስ ማንነው?” ብለው ፅፈዋል፡፡ በጥያቄ እንጀምርና ሐዋርያው በገለጠውመሠረት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ብቻ የተገለጠች ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ፃድቃን፣ ሰማዕታት የሞቱላት፣የተሰውላት፣ የተጋደሉላት ሃይማኖት መገኛዋ የትነው? መቼ ተፈጠረች? ከየትስ መጣች? መልካም ይህን ጥያቄ ለመመለስ የዓለም ሊቃውንት የተለያ የመላምልት ሰንዝረው አልፈዋል፡፡ መላእክትሲፈጠሩ፣ አልያም አዳም ሲፈጠር ተፈጥራ በፍልስጥኤም ምድር ወይም ከመካከለኛ ምስራቅ እንደተገኘችና ከዚያም በንግድ ልውውጥ እንደመጣች፤ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐሳቦችእንደምታውጠነጥኑ ይታወቃል፡፡ ግምታችሁ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ ባይኖረውም የብዙ ሰዎች ሐሳብ ስለ ሆነ በኢምሁራን ሳምባ መተንፈሳችሁን ታስታውቃላችሁ፡፡ ሃይማኖት በእጅ ብልጫ ሳይሆንጥቂት ሰዎች ብቻ በሚገቡባት በጣም በጠበበች በር ነው የምትገኘው ማቴ.7፥14፡፡
አንድ ነገር ላስታውሳችሁ፡፡ ተዘከሩ ቃለ ዘነገሩክሙቀዲሙ ሐዋርያቲሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ “በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት የተነገረውንቃል አስቡ” ይሁ.1፡17፡፡ ይህ የምጽፍላችሁ ጽሑፍ የሐዋርያት ወይም የኋላ ሊቃውንት አስተምህሮነው? ወይስ ልብ ወለድ? ወይስ ዘመን ያመጣው? ብላችሁ መጠርጠረና መመርመር አለባችሁ፡፡ ሃይማኖት በየቀኑ፣ በየዘመኑ መልክዋን፣ ባህልዋንእየለወጠች፣ አስተምህሮዋን እየቀያየጠች፣ የምትገለጥ የሆነች ግራ የምታጋባ ነገር አይደለችም፡፡ ወደ ጥያቄው ልመልሳችሁ፡፡ ሃይማኖት እንተ እምኀበ አብ ተፈጥረት፣ ኀበ ወልድ ታበፅሕ፣ ወኀበ መንፈስ ቅዱስ ትትፌፀም “ሃይማኖትስ በአብ ዘንድ የነበረች፣ ወደ ወልድየምታደርስ፣ በመንፈስ ቅዱስ የተፈፀመች ወይም የመገለጥዋን ፍፃሜ በመንፈስ ቅዱስ ያገኘችናት”፡፡ አዎን ሃይማኖት በእግዚአብሔር አብ ህሊና የነበረች፣ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስክርስቶስ መወለድ (ምስጢረ ሥጋዌ) ጠርታ ጎልታ የታወቀች፣ በበዓለ ፶ በርደተ መንፈስ ቅዱስአማካኝነት በፅርሐ ጽዮን በሐዋርያት ጉባኤ የፀደቀች፣ ሙሉ በሙሉ የተደመደመች ናት እንጂ በበራልኝ፣ ተገልጠልኝ፣ ነገረኝ፣ ተነገረኝ የተገኘች፣በሥጋዊ ደማዊ ፍልስፍና የተዋቀረች፣ የሰብአዊሐሳብ ጥርቅም አይደለችም፡፡ ጥንት በአምላክህሊና የነበረች፣ አሁን ያለች፣ ደግሞ ያለ መበረዝ ያለ መከለስ በፍፅምና ለዘለዓለም የምትኖር ናት፡፡አሜን! የሃይማኖት መገኛ ማንም ማን ሊያየውናሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ያለ እግዚአብሐር እንጂ(1ጢሞ. 6፥16) በየስኪሪኑ(ሰሌዳ) የሚታየው ነጪ አውሮፓዊወይም ጥቁር አፍርካዊ ፈዋሽና ሰባኪ ነኝ ባዩ አይደለም፡፡ ሃይማኖት የተሰበከችው የተሐድሶአራማጆች ከተነሱበት ከ16-20ኛ ክ/ዘ ጀምሮም አይደለም፡፡ ሃይማኖት የተሰበከችልን በለቤቱ ራሱ ጌታችን ባስተማራቸውና በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው ከብልየት በታደሱ መከራን እየተቀበሉ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በሰይፍና በስለትያለፉ ዓለም ያልተገባቻቸው ሐዋርያት ነው ዕብ.11፥37፡፡ የሃይማኖት መሠረት ክርስቶስ ነው 1ቆሮ.3፥11፡፡ ዛሬ በዚህ ርዕስ ለመጻፍ የተነሳሁበት የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡ ምናልባት ስታነቡ “እምንት እንጂ ሃይማኖት የለንም እምንት እንጂ ሃይማኖት አያፀድቅም” የሚትል አረማዊት አስተሳሰብ ከጎረቤት የቀላወጣችሁት ወሬ ካለች ለቅዱሳንአንድ ጊዜ ፈፅሞ የተገለጠ ሃይማኖት የሚለውን ይሁ.1፥3 በማስዋል አንብቡና የሃይማኖት ምንነት ተረዱ፡፡ አዎን መጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ልዩ በሆነ እንግዳ ትምህርት አትወስዱ ይለናል ዕብ. 13፥9፡፡ልብ በሉ የሃይማኖት መሠረት ከሌለን “እንግዳ በሆነ ትምህርት ልንወስድ እንችላለን” እንግዳ ሃይማኖት ነባር አይደለም፣ ከእግዚአብሔር ጋር አልነበረም፣ አይታወቅም፣ ለሰውም ለአገሩም በዳነው፣ አዲስ ነው፣ የሰው ሥርዓት የሰው ንድፈ ሐሳብነው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹በሐዋርያት ቃል ቀድሞየተነገረውን አሳቡ ያልኩት›› በእርግጥ በሐዋርያት ዘመን እንዲሁም በዘመነ ሊቃውንትም በዓይነቱ ልዩየሆነ እንግዳ ትምህርት ተከስቶ ነበር፡፡ እንደ አሁኑ በየጓደው ባይሆንም፡፡ በዚህም ሐዋሪያትም ሆኑ ሊቃውንት በየጊዜው ለተነሱ የሐሰት አስተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውሳኔና ቀኖና ይሰጡ ነበር፡፡“ወሰኑ ወሠርዑ ሃይማኖተ” እንዲል፡፡ ሃይማኖታዊ ድንበር እንዳይጣስ በተለይ ስህተትን ለመቃወምከታወቁ የጥንት ሲኖዶሶች (ጉባኤዎች) ሶስቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. የሐዋርያት የእምነት አቋም (ፀሎት ሃይማኖትዘሐዋርያት)
2. የሶስት መቶ ሊቃውንት (ፀሎት ሃይማኖትዘኒቅያ)
3. የአትናቴዎስ የእምነት መግለጫ (ፀሎት ሃይማኖት ዘአፍራቂያ/ዘአፍሪካ/)
እነዚህ ሁሉ በሊቃውን ታይተው ውሳኔተሰጥቶባቸዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያላቸው መሆኑን በተባረኩ አባቶቻችን ተረጋግጠዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሔዋን አዳምን ሳታማክር ዕፀ በለስ በልታ አብልታ እንደበላችው፣ስታ እንዳስተችው፣ ሰዎች ከሃይማኖት አስተማሪዎቻችን ሳይማከሩ፣ ሳይማሩ፣ በሐሰተኞች አስተማሪዎች ከየመንገዱ እየተጠለፉ ነው፡፡ ሐዋርያው “ክፉዎች ሰዎትና አታላዮች ኢያሳቱናእየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ አንተ ግን በተማርህበትና በተረደህበት ፀንተህ ኑር” 2ጢሞ.3፥13-16 እንዳለው ባለንበት ሃይማኖት ፀንቶመኖሩና መማሩ መወያየቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህየሃይማኖት መበጧጠስ ያፈራው ለመፅሐፍ ቅዱስካለ መታዘዝ የተነሳ ነው፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ በ3፥1ላይ እንዲህ ፅፏል ’’ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃለችሁና” አስተማሪዎች ሲበዙሐዋርያው እንዳለው በዓይነቱ ልዩ የሆነ ትምህርት መቀረፅ አይቀሬ ነው፡፡ የሰውን ቀልብ ሊሰብየምችል ቀለል ያለ “ፓልሲ” እንበለው? ለምሳሌ ማሕተብ እንደ ኮተት፣ ፆምን መፆም እንደ ኩነኔ መቁጠር፣ ፀሎት መፀለይ ፕሮክራሲ እንደማብዛት፣ የመለእክተን ስም መጥራት ሰይጣን እንደ መጥራትወዘተ የመሳሰሉትን ያስተምራሉ፡፡
በመሠረቱ የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዎች በሙሉመጽሓፍ ቅዱሳዊ ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለን፡፡ በእውነቱ ይህ ዓይነቱውንብድና በምዕመናን ላይ ገሃነማዊ ፍርድማስከተል ነው፡፡ “ህየንተ ቡራኬ መርገመ ወህየንተስርየት ኃጢአት እሳተ ገሃነም” በቡራኬ ፈንታመርገምን በኃጢአት ስርየትም ፈንታ ገሃነምእሳትን” ማለት እንጂ ይለናል፡፡ አንድ አንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በስመ ክርስትናየሚጠሩ በመሠረታዊ የክርስትና እምነት ማለትምበሐምስቱ አእማደ ምሥጢርና በሰብአቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ካለመግባባት የተነሳየተለያዩ በቁጥር አየናሩ እየጨመሩ ከ33,000በላይ እንዳሉ ይጠቁማሉ:: ከ33,000 በላይ ይቅርናበዓለም ሁለት ሃይማኖቶች ቢኖሩ እንኳ አንዱ ሐሰትነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “አሃቲ ሃይማኖት” ሃይማኖትአንዲት ናት ይላት የለም አፌ. 4፥6፡፡ ይህ የሆበትምክንያት ከ16-20ኛ ክ.ዘ. በተነሱ የተሃድሶ አራማጆች መጽሐፍ ቅዱስን ከተጻፈበት ዓለማናመንፈስ ውጪ በማውጣት እንደበራላቸው፣እንደሻቸው፣ ከተሰመረለት መለኮታዊ መስመርውጪ በተመርጐም ልጓም እንደ ሌለውእንዳልተገራ ፈረስ በአስተምህሮ ሲደናበሩ ለዚህክፍፍል ደርሰዋል፡፡ አዲሱ የእምነት እንቅስቃሴእውነት ከሆነ ለምን ለ33 ሺ ተከፈፈል? ለምንበአንድ አስተምህሮ አይስማውም? ይህን የቤትሥራ ሰጥቻችአለሁ፡፡ ክርስቶስ የመጣው እኮበሃይማኖት አንድ ያደርገን ዘንድ ነው፡፡ ሊለየን፣ ሊለያየን፤ ሊበትነን፣ ሊበታትነን አይደለም፡፡ አንድባለ ቅኔ “መምህረ ኮነ በበደወሉ፣ ፊደላተ ዘኈለቈ ኩሉ”ትርጉሙ “ፊደላትን የቈ ጠረ ሁሉ በየአጥቢያው አስተማሪ ሆነ” ብለው ሐዜኔታቸውን በቅኔ ገለፁ፡፡ እውነት ነው፡፡ ሳይማሩ ማስተማር፣ሳይሰበኩ መስበክ፣ ሳይጠመቁ ማጥመቅ ከሁሉየሚገርመው የዘፈን ከሴቶቻቸው እንኳ ተሸጦሳያልቁ፣ ለስድስት ወር እንኳ በወጉ ሰይማሩ ፓስተር፣ ሳይመገቡ መጋቢ ተብለው መጠራቱ ነው፡፡ ለነገሩማ እነሱ ምን ወግ አላቸው? ይህበእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ነው፡፡ አስተውሉ”ይሴርዎን እግዚአብሔር ለከናፍሩ ጒሕሉት፣ወለልሳን እንተ ተዓቢ ነቢበ፣ እለ ይብሉ ናዓቢልሳናቲነ ወከናፍሪነኒ ኃቤነ እሙንቱ፣ መኑ ውእቱእግዚእነ “የሽንገላ ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔርያጠፋቸዋል፣ ታላቅ ነገርንም የምትናገረው ምላስ፣ምላሳቸን እናበረታለን ከንፈራችን የእኛ ነው፣ ጌታችንማነው የሚሉትን?” መዝ. 12፥3-4፡፡ ሁሉም በአንድየመጽሐፍ ቅዱስ መለከታዊ መመሪያ የሚመሩቢሆኑ ኑሮ ወደ እንዲህ ዓይነቱ አሳፋሪ መበታተንአይገቡም ነበር፡፡ በተለይ በአሁን ባልንበትበመጨረሻ ዘመን ሐሰተኞች አስተማሪዎችሐሰተኞች ነቢያት 2ጴጥ.2፥1 ማቴ. 24፥11ሐሰተኞች ክርስትያኖች እንደ ሚነሱ መንፈስ ቅዱስበግልጥ ነገሮናል 2ጢሞ. 3፥1-3፡፡ እግዚአብሐርምሥጢሩን አስቀድሞ ለባርያዎቹ ሳይነግር አንዳችአያደርሳም” አሞ. 3፥7፡፡ እስከ መጨረሻ በእምነቱየሚፀና ግን እርሱ ይድናል ማቴ. 24፥12፡፡
በመጀመሪያ በእግዚአበሔር በነበረች፣ ወደ ወልድወደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስበምታደርሰው፣ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተገለጠችሃይማኖት ፀንታችሁ ትጋዳሉ ዘንድ እግዚአብሔርፅናቱን፣ አእምሮውን፣ ለብዎውን ይሰጣችሁ፡፡ ነፋስበነፈሰ፣ ማዕበል በተነሳ፣ ጎርፍ በጎረፈ፣ ጊዜመልህቅ እንደሌላት መርከብ ወደያና ወዲህእንዳንገለባበጠን እምነታችን በዓለቱ በክርስቶስላይ መመስረት አለበት፡፡ በእውነተኛ ቃሉ ላይመተከል አለብን ማቴ.7፥24-27፡፡
ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ
0 comments:
Post a Comment